ለተፀነሰው ልጄ

Wednesday, 02 May 2018 12:40

እንደምነህ ሙጬ

      እንዴት ነህ የኔ ልጅ?

ሰምቼ ነበረ የእናት ሆድ ከዓለም

      እጅግ እንደሚልቅ

            ለአንተም እንደሚበጅ፣

ከዘጠኝ ወር በላይ

      አይኖርም አሉ

            ቢኖርማ ኑሮ አስቀርህ ነበረ፣

ግዴለም ከሆነ ይገባህ ይሆናል በዋለ ባደረ፣

እኔ ’ምልህ ልጄ!

      ይቺ የኛ ዓለም

            ለአንተ አትበጅህም፣

አውቃለሁ ጉዳዩን

      እንደእርሳስ አድርጌ

            እኔ ብቀርጽህም፣

አስርቱን ትዕዛዛት

      በልቦናህ ደብተር

            በማይለቅ ቀለም አጽፍልሃለሁ፣

“በሀሰት አትመስክር”

      ብዬ እነግርሃለሁ፣

በሀሰት መስክረው

      ሲጠቀሙ እያየሁ፤

ሀብታቸው ሲሞላ ኑሯቸው ሲቃና

            በውል እየቃኘሁ።

“አትመስክር” እያልኩኝ እማጸንሃለሁ፣

“አትግደል” እላለሁ ሲገድሉ እያየሁኝ፣

“አትስረቅ” ብልህም ሲዘርፉ አያለሁኝ፣

“አታመንዝር” ስልህ ማመንዘር በርክቶ፣

ሥልጣንና ገንዘብ ቀበቶ አስፈትቶ፣

ግን እነግርሃለሁ!

      ትዕዛዛቱን ሁሉ አስጨብጥሃለሁ፣

ምን አለፋህ ልጄ!

      እኔን ያስጨነቀኝ ሐሳብ የሆነብኝ፣

የቱን ነው የምነግርህ?

      እንዴት ነው የምታምነኝ?

እኩይ ያሉት ሁሉ

      ሰናይ ሁኖ ሲገኝ፣

እውነት ልነግርህ ነው

      ወይስ ላስመስልህ?

በቃ ግዴለኝም

      መምጣትህ ካልቀረ

      ዘርህን ትመርጣለህ።

ያው እንደ ዘመንህ

      ከሐበሻ ማንነት አንዱን ትሆናለህ!!

                የሐበሻ ቁጣ - በሀቢብ መሐመድ

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
128 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 431 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us