የጭንቀት መወጫ ጎጆ

Wednesday, 02 May 2018 12:43

 

የዩታህ ዩኒቨርስቲ በጭንቀት ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ጭንቀታቸውን በፈለጉት መንገድ ሊያስወግዱበት የሚችሉትን ጎጆ አዘጋጅቶላቸዋል። በዩኒቨርስቲው የሚማሩ ተማሪዎች በሚሰጧቸው የቤት ስራዎች፣ የቡድን ስራዎች ወይም በፈተና እና በተለያዩ ምክንያቶች ጭንቀት ውስጥ ሲገቡ ያለ ምንም ፍራቻ ራሳቸውን ነፃ የሚያወጡበት ገለልተኛ ጎጆ ነው ያዘጋጀላቸው። በዚህ ጎጆ ውስጥ በተለያዩ የእንስሳት ቅርፅ የተሰሩ አሻንጉሊቶች ያሉ ሲሆን፤ የተጨነቁት ተማሪዎችም እነዚህን አሻንጉሊቶች፣ በማነቅ፣ በመደብደብ፣ በመጭመቅ፣ በመንከስ እና ሌላም የተቻላቸውን ነገር ሁሉ በማድረግ ንዴታቸውን መወጣት ይችላሉ። በዚህ የጭንቀት መወጫ ጎጆ ውስጥ ለሚጠቀሙ ተማሪዎችም ዩኒቨርስቲው ያስቀመጠላቸው ህግ አለ። የመጀመሪያው ህግ ማንኛውም ተማሪ ወደ ክፍሉ ሲገባ አስቀድሞ ማንኳኳት ይኖርበታል። በአንድ ጊዜ በጎጆው ውስጥ መስተናገድ የሚችለው አንድ ተማሪ ብቻ ሲሆኑ፣ በጎጆው ውስጥ መቆየት የሚፈቀድለትም እስከ አስር ደቂቃ ብቻ ነው። በመጨረሻም ተማሪው ቆይታውን አጠናቆ ሲወጣ የክፍሉን መብራት ሳይዘነጋ ማጥፋት ይኖርበታል። ይህ ጎጆ ተማሪው ሰው አየኝ ሰማኝ ሳይል በነፃነት ንዴቱን በመወጣት በጤናማ አእምሮ ወደ እለት ተግባሩ እንዲመለስ ያግዘዋል ተብሎ የተዘጋጀ መሆኑን የጎጆው ባለሞያ ኒሞ ሚለር ገልጿል ሲል ያስነበበው ኦዲቲ ሴንትራል ነው።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
165 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 390 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us