የዓለም መጨረሻ

Wednesday, 09 May 2018 13:17

 

አንድ ወጣት ተማሪ

የሰማይ የምድሩን ጠያቂ መርማሪ

ትልቅ ባህታዊን ጫካ ውስጥ አግኝቶ

ነፍሱ ስለጓጓ ጥበብን ተጠምቶ

ዓለምን የናቁ እኝህን ባለ እድሜ

ንገሩኝ አላቸው ስለዓለም ፍጻሜ

      እኚህ ባህታዊም በጽሞና አስበው

      የለሆሳስ ጸሎት ጥቂት አነብንበው

      ነገሩት በብዙ ለትጉው ወጣት

      ምድር እንደምታልፍ በሰው ልጅ ኃጢአት

      ዓለም በሰው ክፋት ማቅ እንደለበሰ

      በአዳም ልጆች በደል ጽዋ እንደፈሰሰ

      የዚህ ዓለም ነገር ቀኑ እንደደረሰ

      የእውቀትን ተራራ ለሚቧጥጥ ተሜ

      መናኙ ገለጡ የዓለምን ፍጻሜ

ይህን ሲናገሩ ዝሆኖች ሰሙና

እጅግ ተሸበሩ ባደመጡት ዜና

እነሱም ሲያወሩ

መጭውን ሲመክሩ

ኮከብ አስቆጥረው

በኩምቢ ተንብየው

እርጥብ ዛፍ ገንድሰው

ዱካቸውን አይተው

ዓለም በሰው ክፋት ታልፋለች መባሉ

ስህተት እንደሆነ ተግባቡ በሙሉ

ዝሆኖችም አሉ “ዓለም የሚጠፋው” 

በዝሆኖች ጥጋብ በእኛው ምክንያት ነው

      ከዝሆን እግር ስር የሚርመሰመሱ

      የሳር፣ የእህል ቅንጣት የሚያመላልሱ

      ዝሆኖችን ሰምተው ጉንዳኖች በተራ

      የዓለሙ ፍጻሜ እነሱን አስፈራ

      በሁሉ እንዲታወቅ በሁሉ እንዲሰማ

      ስብሰባ ተጠርቶ በጉንዳን ፓርላማ

      ዓለም የሚጠፋው በሰው ወይ በዝሆን

      በይፋ አስማማቸው ፈጽሞ እንደማይሆን

የዚህ ዓለም ማብቂያ የፍጻሜው ስራ

በጉንዳን ጦርነት መሆኑም ተወራ።

ጽሞና እና ጩኸት

በሰሎሞን ሞገስ (ፋሲል)

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
133 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 531 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us