ታማኙ ውሻ

Wednesday, 09 May 2018 13:20

 

ዢንግዞንግ የ15 ዓመት ውሻ ነው። ይህ ውሻ የዛሬ ስምንት ዓመት ገደማ በአንድ ግለሰብ አሳዳጊነት ተወሰደ። አሳዳጊው በቻይናዋ ዡንግዚንግ ግዛት ነዋሪ ሲሆን፤ ስራውን ሲከውን ውሎ ከ12 ሰዓታት ቆይታ በኋላ ነው ወደ ቤቱ የሚመለሰው። የሚገርመው ነገር ታድያ ውሻውም አሳዳጊው ወደቤቱ ሳይመለስ ወደቤት አለመግባቱ ነው። አሳዳጊው ለሥራ ከቤቱ ሲወጣ ተከትሎ የሚወጣው ውሻው፤ ለ12 ሰዓታት በሊዚባ ባቡር ጣቢያ ይጠብቀዋል። አሳዳሪው እስከሚመጣ ድረስም ሌላ ሰው የሚሰጠውን አንዳች ነገር ቅምስ አያደርግም። ይህን የታማኝነት ድርጊት ውሻው የሚተገብረው በየዕለቱ ሲሆን፣ ላለፉት ስምንት ዓመታትም ያለምንም ማቋረጥ ተግባራዊ ሲያደርገው ቆይቷል። በጣቢያው የሚተላለፉ በሺዎች የሚቆጠሩ መንገደኞች ቢተረማመሱም እርሱ ግን ምንም እንደማይመስለው የተነገረለት ቡቺ፣ ልክ አሳዳጊውን ሲያይ ግን በደስታ እና በፈገግታ ከተኛበት እንደሚነሳ ያስተዋሉት ተናግረዋል። ውሻው ይሄን ተግባሩን በየዕለቱ የሚተገብረው ማንም ሳያስታውሰው እና ሳያሳየው በራሱ ተነሳሽነት መሆኑም ተገልጿል። በዚህ ድርጊቱ እውቅናን ያተረፈው ይህን ውሻ ለመጐብኘት በርካቶች ወደ ባቡር ጣቢያው እየጐረፉ መሆናቸው ተገልጿል።

ውሻ ከሌሎች እንስሳት ሁሉ ታማኝ እንስሳ መሆኑ በተደጋጋሚ ሲገለፅ ይሰማል። ከዚህ በፊት ካፒቴን የተባለ ውሻ የአሳዳሪው መቃብር ላይ ለአስር ዓመታት ሲተኛ መቆየቱ እንዲሁም የአሳዳጊውን ሆስፒታል መግባት ተከትሎ አሳዳጊው ህይወቱ እስከሚያልፍ ድረስ ለአራት ወራት በሆስፒታል በራፍ ላይ ሲጠብቅ የቆየው ውሻ ታሪክ የሚታወስ ነው ሲል የኦዲቲ ሴንትራል ዘገባ አመልክቷል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
138 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 974 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us