ጥገኝነት ጥያቄ

Wednesday, 23 May 2018 14:04

“የተወለድሁት መሀል ፒያሳ ነው፤” አለኝ፤ እና ምን አባህ ላድርግህ ልለው አሰኝቶኝ ነበር፤ ግን ከፈቃዴ ውጭ ጆሮዬን ሰጠሁት።

“አባቴ በጊዜው በአዲስ አበባ ከሚኖሩ ጥቂት ስመ ጥር ሰዎች አንዱ ነበር፤ እንዲያውም የፒያሳው ብርሃን ተብሎ ይጠራ ነበር።”

“ሊቅ ነበሩ ማለት ነው!”

“ኖ! የፒያሳው ብርሃን የተባለው ላምባ ሻጭ ስለነበር ነው!”

“ገባኝ!”

“የሆነ ጊዜ ላይ አባቴ ሀብታ ሆነ! ግን የኑሮ ነገር አልሆነለትም፤ መጠጣት፣ ሴት መተኛት፣ መደባደብ ሆነ ሥራው። አባቴ አጭር እና ቅንዝረኛ ስለነበረ ሰዎች ስንዝሮነቱን እና ቅንዝረኛነቱን አስተባብሮ የሚገልፅ ስም ሰጡት - ቅንዝሮ ብለው ጠሩት። የድሮ ቅጽል ስሙ ተረሳ። አንድ ቀን በሚጠጣበት ቤት ውስጥ በተፈጠረ አምባጓሮ በድንጋይ ተፈንክቶ ሞተ፤ አብሮ አደግ ጓደኛውም በእለቱ አብሮት ሞተ። አየህ፣ ጓደኛ መስተዋት ነው የተባለው ተረት እና ምሳሌ እውነትነቱ የገባኝ ያኔ ነው። አዎ! ጓደኛ መስተዋት ነው፣ ከሚወረወር ድንጋይ አያስጥልህም!

“የአባቴ ጓደኛ መቼም በጣም ሊቅ ነበር። “አንድ ሊቅ ከሞተ አንድ ቤተ መፃሕፍት ተቃጠለ ማለት ነው” ሲባል ሳትሰማ አትቀርም። አባዬ ግን ከመጠጣት በቀር ምንም አያውቅም። ምን ታደርገዋለህ! አንድ ቤተ መፃህፍት ሲቃጠል ከጎኑ ያለ ጠጅ ቤት አብሮ መቃጠሉ አይቀርም። ደከመህ መሰል?”

“ኧረ እየሰማሁህ ነው!”

“አባዬ ከሞተ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እማማ ታማ ሆስፒታል ገባች። ወደ ውጭ አገር ሄዳ እንድትታከም ተወሰነ። ከዚያ፣ አሜሪካ ለሕክምና በሄደችበት በዚያው የፖለቲካ ጥገኝነት ጠየቀች።

“የፖለቲካ ጥገኝነት እንዴት ተሰጣቸው?”

“Well, ሆስፒታል ውስጥ እያለች የኢትዮጵያ ሕመምተኞች አብዮታዊ ፓርቲ የሚባል ድርጅት አቋቁማ ነበር። ትዝ ይለኛል፣ ልጠይቃት በሄድሁ ቁጥር እሷ ያነቃቻቸው ህመምተኞች መድኃኒት መድኃኒት በሚሸት ክፍላቸው ውስጥ ተሰብስበው፣

“እንደ ቼጉቬራ፣ እንደ ቼጉቬራ፣”

“እንደ ቼጉቬራ፣ እንደ ቼጉቬራ፣”

በማለት በታላቅ ወኔ ይዘምሩ ነበር። አየህ ቼጉቬራም በህይወት ዘመኑ ሙሉ የአስም ህመምተኛ ነበር!”

መውጣትና መግባት - በዕወቅቱ ስዩም

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
90 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 146 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us