ማን ነው የነብር እጣት?

Wednesday, 23 May 2018 14:22

 

አይበገሬ ለፈተና… የብረት ቆሎ ፎጠና

ወጣት… ቋጥኝ የሚንድ ደማሚት ዕቶን እሳት

የቆመውን የሚያጋድም

የተጋደመውን የሚያቆም የለውጥ ፍላት

   ወጣት … የነብር ጣት

   ፈተናን የሚፈትን

   ቋጠሮን የሚፈታ ድድርን የሚበትን

   ድንጋይን የሚያቀልጥ እቶን እሳት

ወጣት - የነብር ጣት

የልውጣ አልውጣ ሀይል እምቃት

   ወይንስ! ወጣት

   ቅቤ የማይንድ የበረዶ ትኩሳት?

   ከሰንበት፣ ሰንበት፣ የሎሽን፣

   የክሬም፣ ውልውላት

የጄል፣ የቀለም፣ ልቅልቃት

የጸጉር ግርጣት ጉንጉናት

የሰበር ሰካ እርምጃ - የትከሻ ውዝውዛት

የሚዶ፣ የቡርሽ፣ የመስታውት፣ ባላባት

የእጅ በኪስ ኩራት

በውኑ ይኸም ወጣት? የነብር ጣት?

   ሰኞ፣ ማክሰኞ፣ ሮብ፣ ሐሙስ፣ አርብ ሰንበታት

   ከመጾው እስከ ጥቢ - ከበጋ እስከ ክረምት

   ከጧት እስከ ማታ - ከመአልት እስከ ሌሊት

   መዘነጫ፣ መሽቀርቀሪያ፣ መወዝወዣ፣ መጎለቻ፣

   መጀበኛ - መፈረሻ - ከበርቻቻ

ይሄም ወጣት - የነብር ጣት?

ሰርክ ከአዘቦት - ሁሌም እረፍት

ከስክሪን፣ ከዲሽ ጋር -ፍጥጣት

ግብ የለሽ - በሌላው ግብ የሚያቅራራ

ስለ ሰው ገድል - የሚያወራ

ይሄም ወጣት? የነብር ጣት?

ግዙፍ ሆኖ - ግዝፈቱን ያላመነ

ቋያ ቃቄ -ወኔውን ያደፈነ

ለሽምግልናው- ጉልበቱን የከዘነ

ይሄም ወጣት? የቋያ እሳት?

ማጣት - የነብር ጣት

ስልሞውን ፈጥርቆት

አሻ!

            ዋኔዋ - በአስናቀ አካልነህ

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
76 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us