የማይታመኑ እውነታዎች

Wednesday, 06 June 2018 13:57

 

·                     በ2011 ዓ.ም ኤሚ ዴቪሰን የተባለች ሴት አንድ ምንም የማይታይ ስእልን በ10ሺህ ዶላር ገዝታለች።

·                     ሳዳም ሁሴን ዘቢባ እና ንጉሱ የሚል የፍቅር ልብ ወለድ ደራሲ ነው። ይህ መፅሐፍ እ.ኤ.አ. በ2000 ዓ.ም በስውር ኢራቅ ውስጥ ታትሟል።

·                     በታይዋን አንድ ምግብ ቤት ምግብ ማቅረቢያዎቹ በመፅደጃ ቤት ሳህን ቅርፅ የተሰሩ ናቸው።

·                     ልዑል ቻርልስ እና ዊሊያም ሁልጊዜም በረራ ሲያደርጉ የሚጓዙት በተለያየ አውሮፕላን ነው። ምክንያቱም አደጋ ቢፈጠር አንደኛቸው እንኳን ለመትረፍ ነው።

·                     በጨካኝነቱ የሚታወቀው አዶልፍ ሂትለር፣ አሉሮ ፎቢያ የሚባል የድመት ፍራቻ አለበት። ታላቁ አሌክሳንደር፣ ናፖሊዮን እና ሙሶሎኒም የዚሁ የድመት ፍራቻ ተጠቂዎች ናቸው።

·                     ቻርልስ ዳርዊን በምርምር ያገኛቸውን የእንስሳ ዝርያዎች ሁሉ ይመገብ ነበር።

·                     የዓለማችን ሰፊ ቤተሰብ ያለው ሰው ህንዳዊው ዚዮና ቻና ነው። ይህ ሰው 39 ሚስቶች ያሉት ሲሆን፤ 94 ልጆች፣ 14 የልጅ ሚስቶች እንዲሁም 33 የልጅ ልጆች አሉት። ቤተሰቡም ባክትዋንግ በተባለች ከተማ ውስጥ ባለ መቶ ክፍል እና ባለ አራት ፎቅ ቤት ውስጥ ይኖራል።

·                     ብራድ ፒት ሰባት ዓመታትን በቲቤት በሚባለው ፊልም ላይ በነበረው ድርሻ ምክንያት ወደ ቻይና እንዳይገባ እገዳ ተጥሎበት ነበር፡፤

·                     ዬሬታ የተባለ አንድ ግለሰብ ለሚስቱ መታሰቢያ የሚሆን የጊታር ቅርፅ ለመስራት 2ሺህ ያህል ዛፎችን ተክሎ ነበር።

·                     በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን ይሁዳን ሆነው ሲተውኑ የነበሩ ሁለት ተዋናዮች በትወና ላይ ሳሉ ህይወታቸውን አጥተዋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
184 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 821 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us