ድንበር ያቋረጠችው እርጉዝ ላም በሞት ልትቀጣ ነው

Wednesday, 06 June 2018 13:59

 

ሕግ ሕግ ነው የሚለው አባባል እውነተኛነት እየተስተዋለ ነው ያሰኛል የሰሞኑ የኦዲቲ ሴንትራል ዘገባ። አንዲት እርጉዝ ላም ሀገር አማን ብላ ከአሳዳሪዎቿ በማምለጥ ወደ ጎረቤት ሀገር በማምራቷ የሞት ቅጣት ሊጣልባት ነው። ቡልጋሪያዊቷ ላም ሳታውቅ ድንበር አቋርጣ ወደ ሰርቢያ ትገባለች። ከአሳዳሪዋ አምልጣ ወደ ሰርቢያ የገባቸው ይህች ላም፣ አሳዳሪዎቿ ከሁለት ሳምንታት ፍለጋ በኋላ ያለችበትን ቢደርሱባትም ወደቤታቸው ይዘዋት መመለስ ግን አልቻሉም። ፔንካ የተባችው ይህች ላም ድንበር አቋርጣ የገባችበት ሰርቢያ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገር ባለመሆኗ ህጋዊ የይለፍ ወረቀት ሳትይዝ ወደ ሀገሯ መመለስ አትችልም። ይልቁንም በህገ ወጥ መንገድ ድንበር በማቋረጧ በሞት እንድትቀጣ ተፍረዶባታል።

የሰርቢያ እንስሳት ህክምና ተቋም የላሟን ጤንነት በማረጋገጥ ወደ ሀገሯ መመለስ እንደምትችል ቢገልጽም የድንበር ጠባቂዎች ግን አሻፈረን ብለዋል። ጠባቂዎቹ እንዳሉትም በአውሮፓ ህብረት ሀገራት የጋራ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ላሟ ወደ ቡልጋሪያ ለመመለስ የይለፍ ወረቀት ያስፈልጋታል። ላሚቷ ይህን ወረቀት ስላልያዘችም ህገ ወጥ በመሆኗ በሞት እንድትቀጣ ተወስኖበታል። ላሟ ልትወልድ ቀናት የቀሯት ብትሆንም ህጉ ተፈፃሚ ይሆን ዘንድ በሞት እንድትቀጣ ተወስኖባታል ተብሏል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
149 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1011 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us