ጉዞ ከካርቶን ጋር

Wednesday, 20 June 2018 12:47

 

አምስቱ ጓደኛሞች በሩሲያ እየተካሄደ ያለውን የዓለም ዋንጫ በጋራ ለመመልከት ቃል የተግባቡት ከ6 ዓመታት በፊት ነበር። እነዚህ ብራዚላዊያን ይሄንን ምኞታቸውን እውን ለማድረግ ገንዘብ መቆጠብም ጀምረዋል። ጊዜው ሲደርስም በሀገራቸው ባንዲራ ቀለም ባጌጠ ተሽከርካሪ ወደ ሩሲያ ለመጓዝ ዝግጅታቸውን አጠናቀቁ። በዚህ መሀል ግን አንደኛው ጓደኛቸው ያልተጠበቀ መርዶን አረዳቸው። ሚስቱ ጉዞውን እንዳልፈቀደችለት እና በቃሉ መገኘት አለመቻሉን አስረዳቸው። ሚስት ብትለመን፣ ብትባል ብትሰራ አሻፈረኝ አለች። በዘህን ጊዜ ጓደኞቹ ከአንድ ስምምነት ላይ ደረሱ። በጉዞው ላይ ባልተሳፈተው ጓደኛው ቁመት ልክ እና መልክ በካርቶን ቅርጽ አውጥተው በሚጓዙበት አውቶቢስ ላይ ከመካከላቸው አስቀመጡ። በዚህ ብቻ አላበቁም። ቅርፁን “ሚስቴ እንድሄድ አልፈቀደችልኝም” የሚል ፅሁፍን አሰፈሩበት። ከጎኑም የውሃ ኮዳ አስቀመጠው በህይወት ያለ ለማስመሰል ሞክረዋል። በጓደኛቸው ሚስት ውሳኔ ቢበሳጩም በራሳቸው ፈጠራ ራሳቸውን ማፅናናት ችለዋል ሲል ያስነበበው ኤቢሲ ኒውስ ነው።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
88 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1016 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us