አስገራሚ እውነታዎች

Wednesday, 27 June 2018 12:42

 

-    የሌሊት ወፍ ልጇን የምትወልደው በእንጨት ቁልቁል ተዘቅዝቃ በመሰቀል ሲሆን፤ ልጇንም በክንፏ መሬት ከማረፉ በፊት ትይዘዋለች።

-    ንብ ልክ እንደ ሰው ልጅ ሁሉ በግብረ ስጋ ግንኙነት በሚተላለፉ በሽታዎች ትያዛለች።

-    ድመት የጣፋጭን ቃና የሚለይ የሰውነት ክፍል ስለሌላት ስኳርን አታጣጥምም

-    በ1924 አንድ የላብራዶር ዜጋ የሀገሪቱን ገዢ ድመት በመግደሉ በሞት ተቀጥቷል።

-    በ18ኛው ክፍል ዘመን በእንግሊዝ የነበሩ ቁማር አጫዋቾች ፖሊስ ሲመጣ የመጫወቻ ኳሱን የሚውጥ ሰው ይቀጥሩ ነበር።

-    ካላማ በተባለው የቺሊ በረሃ ላይ እስከ አሁን ድረስ ዝናብ ዘንቦ አያውቅም።

-    የኢንዲያና የኒቨርስቲ በዓመት አንድ ኢንች ያህል ይሰምጣል።

-    በቤታችን ውስጥ ከሚገኙ ቆሻሻ ነገሮች መካከል አብዛኞቹ ከሞቱ ሴሎች የሚመጡ ናቸው።

-    በአንድ ሰው ቆዳ ላይ የሚገኙት ህይወት ያላቸው ነገሮች በምድራችን ላይ ካሉ የሰው ልጆች ቁጥር በላይ ነው።

-    ህፃናት ሲወለዱ የጉልበት ሎሚ የሌላቸው ሲሆን፣ ሎሚው የሚፈጠረው ከሁለት እስከ ስድስት ዓመት ባለው እድሜ ውስጥ ነው።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
52 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us