ሌብነት የሌለበት ብቸኛዋ ከተማ

Wednesday, 27 June 2018 12:45

 

ሌብነት በየጊዜው መልኩን እየቀያየረ ሲመጣ እንሰማለን፤ እናያለን እንጂ ሌብነት የሌለበት ነገር አለ ብለን የምንገምት አይመስለኝም። ዩሮኒውስ ግን የዓለማችን ሌብነት የሌለባትን ከተማ ሰሞኑን ይፋ አድርጓል። ይህች ከተማ አቤንታል የምትባል ሲሆን፤ የምትገኘውም በምዕራብ ሮማኒያ ነው። በዚህች ሀገር ላይ በብዛት የሚኖሩትም የቼክ ጎሳዎች ናቸው። በዚች ከተማ ፖሊስ ጣቢያ የሚባል ነገር የለም። ለነገሩ አስፈላጊም አይደለም። ህዝቦቿም እርስ በርሳቸው የሚከባበሩ እና አንዳቸው የሌላኛውን ንብረት የማይነኩ ናቸው። ህዝቡ ሰላማዊ ህይወትን የሚመራ እና ወንጀልም የማይፈፅምበት ከተማ ነው።

ከወንጀሎች አንዱ የሆነው ሌብነትን ስናይ ደግሞ በዚህች ከተማ በፍፁም የለም። አንድ ሰው ዳቦ መግዛት ሲፈልግ ገንዘቡን እና የሚፈልገውን መጠን ጽፎ በቦርሳ አድርጎ ጎዳና ላይ በማስቀመጥ ወደፈለገበት ይሄዳል። ዳቦ አከፋፋዩም ገንዘቡን ወስዶ የታዘዘውን ያህል ዳቦ እና ገንዘቡም መልስ ካለው መልሱን በአንደ ላይ አድርጎ በመብራት ፖል ወይም በግለሰብ አጥር ላይ ይሰቅለዋል። ያን ቦርሳ ባለቤቱ መጥቶ እስከሚወስደው ድረስ ማንም የሚጠብቀው ሰው ባይኖርም ከባለቤቱ ውጪ ንክች የሚያደርገው ግን የለም። በዚህ መልኩ እየኖሩ ታዲያ ላለፉት ሀያ ዓመታት አንድም ሰው ገንዘቤ ጠፋብኝ፣ ዳቦው አልደረሰኝም ወይም ሌላ ስርቆሽ ተፈጸመብኝ ብሎ አላመለከተም።

ይህች ከተማ እ.ኤ.አ. ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ ነው በዚህ ዝናዋ የምትታወቀው። ዝናዋ ከሌብነት የነፃች ከተማ በመሆኗ ብቻ አይደለም። ይልቁንም ህዝቡ እርስ በርሱ የሚከባበር ሲሆን፤ አንዱ የሌላውን ንብረት ያለፈቃድ በፍፁም አይነካም። አንድ ሰው ወደ ሰው ቤት ሲያመራ በር ላይ ቆሞ የባለቤቱን ስም ይጠራል። ከቤቱ ውስጥ ሰው ወጥቶ እንዲገባ ከጋበዘው ብቻ ነው ወደ ውስጥ የሚዘልቀው። ከውስጥ ምላሽ የሚሰጠው ሰው ከሌለ ግን ወደመጣበት ይመለሳል። በከተማ የጋራጅ ባለቤት የሆነ አንድ ግለሰብ እንደገለፀውም ጋራጁ ሁልጊዜም ክፍት እንደሆነ ገልጾ ያለምንም ጥበቃ ውሎ እንደሚያድር እና ማንም ሰርቆት እንደማያውቅ ገልጿል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
123 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1027 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us