ባትቀልጥማ!

Wednesday, 04 July 2018 12:47

 

እቴጌ ጣይቱ ጀግና ልብ የነበራቸውን ያህል ለምለም ማህፀን አልነበራቸውም። መካን ነበሩ። ይሁንና አንጥረኞች ከብሩም ከነሐሱም የሕፃን አሻንጉሊት እየሠሩ ያመጡላቸዋል። አንድ ወቅት አንድ የአናጢነት ሙያ የነበረው ሰው ከሰም የተሠራች ማለፊያ ሕፃን አምጥቶ ይመለከታሉ። በመሃሉ አለቃ ይገባሉ።

“ደስ ይበልዎ አለቃ ልጅ ወለድሁ” አሉ እቴጌ።

“እንኳን አብሮ ደስ አለን” አሉ አለቃ። “ይቺ ሕፃን ደስ አትልም? በተለይ ዓይኗ?” ይላሉ እቴጌ።

“በኃይል እንጅ” አለቃ። “ብቻ” የእቴጌ ልጅ ሆና በዓይንማ አትታማም አሉ አለቃ መልሰው ለቅኔው መንገድ ሲያስተካክሉ።

“ብቻ ምን?” አለቃ! የእርስዎ ነገር አያልቅብዎ - እኮ “ብቻ ምን” እቴጌ ጠየቁ

“ብቻማ የንጉሠ ነገሥት ልጅ ነችና ስድ አደግ ሆና እንዳትቀልጥብዎ ብዬ ነው እንጅ አሉ” አለቃ።

ሙሻዙር - በመርስዔ ሐዘን አበባ¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
25 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us