ሚስታችሁን አትዳሩ

Wednesday, 04 July 2018 12:48

 

ትዳር አለሽ ወይ አንቺ የሃያ አንድ እርጉዝ

ጥሪሽ በዝቶብናል ትወልጂ ይሆን ንጉስ

      ውል የለሽ አንቺ ሴት ምጥሽም ቢከፋ

ተስፋ እናድርግ ወይ ሆድሽ ስለገፋ

ልጅ እዳ እንዳይሆን ቤታችን የሚያስከፋ

      ለሰርግም ለለቅሶም ጥሩንባ ይነፋል

      እድርተኛው ነፍሴ መቼ አርፎ ያውቃል

      ያልቆረጠ ቁርጠት ሲያስከፋው ይኖራል።

            ተራራ የፈሩ እታች የሰፈሩ

            በጎርፍ ሲጠረጉ ስንት ቀን አፈሩ

            ድፍረት ላይጋሩ ፍርሃት ተበደሩ   

            የቆሙበት መሬት ሸሻቸው አፈሩ

      ጠይቆ የመጣ!

      እጅ ያውጣ (2x)

      እጅ ያውጣ (2x)

      እነማን ነበሩ?

            መንደሩ ጭር ብሏል ሰው የለም ባገሩ

            ትዳር ፈተው ፈተው ሚስታቸው የዳሩ

            ነውር ተረስቷል ተሰብሯል ድንበሩ

ሞትን ሞት ይሙተው - በፈይሳ ተመስገን¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
35 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us