80 ሺህ ጊዜ ውድቅ የሆነው የጋብቻ ጥያቄ

Wednesday, 04 July 2018 12:50

 

ቻይናዊው ወጣት ውሃ አጣጩን ለማግኘት ያደረገው ጥረት እጅጉን ፈታኝ ሆኖበታል። ኒዩ ዢያንግፊንግ የተባለው የ31 ዓመት ወጣት ብታምኑም ባታምኑም 80 ሺህ ጊዜ የጋብቻ ጥያቄ አቅርቦ አንዱም ሳይሳካለት ቀርቷል። ኦዲቲ ሴንትራል እንዳስነበበው ወጣቱ ላለፉት ስምንት አመታት የህይወት ዘመን አጣማሪውን ፍለጋ እግሩ እስከሚነቃ ቢኳትንም፤ እስካሁን ግን አልተሳካለትም። ወላጅ አባቱ ከአመታት በፊት መሞታቸውን የገለፀው ኒዩ፣ የምትስማማውን ሚስት አግብቶ በእድሜ የገፉ እናቱን ለማስደሰት እና ቤተሰብ ለመመስረት ያደረገው እልህ አስጨራሽ ጥረት ዛሬም አልተሳካለትም። ኒዩ በ2013 ጀምሮ በቤጂንግ ጐዳና ላይ ሚስት እንደሚፈልግ የሚገልፅ ምልክት እና የማኅበራዊ ሚዲያ መገኛውን በማንገብ ወዲያ ወዲህ ይዘዋወር ነበር። አሁን ግን ያንን ዘዴ ትቶ የተለያዩ የመቀጣጠሪያ ድረ ገጾችን በመጐብኘት በርካታ ሴቶችን ለጋብቻ ጠይቋል። ያም ቢሆን፤ ውጤት ሊያስገኝለት አልቻለም።

ኒዩ እንደሚለው ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ 80 ሺህ ጊዜ የጋብቻ ጥያቄ አቅርቦ ሁሉም ውድቅ ሆኖበታል። በእነዚህ ዓመታት ውስጥ 60 ሺህ የጋብቻ የፅሁፍ መልዕክቶችን ለኢንተርኔት ቀጥታ-ለሴቶች የላከ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ጥያቄውን እንደማይቀበሉት ሲገልፁለት፤ ሌሎች መልስም አልሰጡትም። በቤጂንግ ጐዳና ላይ እየተዘዋወረ የጋብቻ ጥያቄ ባቀረበባቸው ጊዜያት ውስጥም ቢያንስ ከ20 ሺህ እስከ 30 ሺህ ለሆኑ ሴቶች ጥያቄውን እንዳቀረበ ገልጿል። ከእነዚህ ሁሉ ሴቶች መካከል አንዷም ልታገባው ፈቃደኛ አልሆነችም። ኒዩ በእነዚህ ሁሉ ዓመታት እና ሙከራዎች ሚስት ማግኘት ላለመቻሉ የራሱ የሆነ ምክንያት ሰጥቷል። ቁመቱ አጭር እና መልኩም የማይስብ መሆኑ ሚስት እንዳሳጣው ነው የሚናገረው። የዘመኑ ሴቶች ረጅምና መልከመልካም የሆነ እንዲሁም ጣፋጭ ቃላትን መደርደር የሚወድ እና ከፍተኛ ደመወዝ እና በከተማ ውስጥ ቤት ያለው ወንድ ነው የሚፈልጉት ያለው ኒዩ፤ እርሱ ግን ከእነዚህ ሁሉ ነገሮች አንዱም እንደሌለው ገልጿል። ሴቷን ለማስደመም እና ወደራሱ ለመሳብ ሲልም ያልሆነውን ነኝ ብሎ ሀሰት የመናገር ፍላጐት እንደሌለው ሲናገር፣ ሌሎች ግን ኒዩ የአጠያየቅ ስልት ባለማወቁ እና ፍቅርን በግዳጅ ማግኘት መፈለጉ ለዚህ እንደዳረገው እየጠቀሱ ይገኛሉ።¾

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
77 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 949 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us