ሜርኩሪና እንጨት ሰባሪው

Wednesday, 11 July 2018 13:08

 

የጥንት ግሪኮች ሜርኩሪ የሚባል አምላክ ነበራቸው። ይህም አምላክ በነበረበት ጊዜ አንድ እንጨት ሰባሪ ድሃ ሰው ይኖር ነበር። ይህም ሰው ጥልቅ ውሃ አጠገብ ከበቀለ ዛፍ ላይ ወጥቶ በምሳር ሲቆርጥ ሳያስበው ምሣሩ እጥልቁ ውሃ ውስጥ ወደቀበት። በዚህ ጊዜ፣ “ምሣሬ! ምሣሬ! እንጨት እየቆረጥኩ በመሸጥ ራሴንና ቤተሰቤን የምመግብበት ምሣሬ ጥልቅ ውሃ ውስጥ ገባችብኝ!” ብሎ ምርር ብሎ አዘነ። ምርር ብሎ ሲያዝንም ሜርኩሪ የተባለው የግሪክ አምላክ ሰማና ለምን እንደሚያዝን ጠየቀው። እንጨት ሰባሪውም ብዙ ልጆች እንዳሉትና ልጆቹን የሚመግብበት ምሣር በድንገት እንደወደቀችበት ነገረው።

ሜርኩሪ ይህን ሲሰማ አዘነና ወደ ውሃ ውስጥ ጠልቆ በመግባት አንድ የወርቅ ምሣር አመጣለት። እንጨት ሰባሪውም “ይህ የኔ አይደለም ጌታዬ” አለው።

ሜርኩሪ ለሁለተኛ ጊዜ ጠልቆ በመግባት አንድ ክብር የተሰራ መጥረቢያ አመጣለት። እንጨት ሰባሪውም “ይህም የኔ አይደለም ጌታዬ” ሲል መለሰለት።

ሜርኩሪ ለሦስተኛ ጉዜ ጠለቀና የራሱን መጥረቢያ ሲያመጣለት “በጣም አመሰግናለሁ ጌታዬ የኔ ንብረት ይኸው ነው” በማለት እጅግ ደስ እያለው ተቀበለው።

ሜርኩሪም የሰውየውን እውነተኛነት ሲያይ “በል ሁለቱንም ውሰዳቸው” በማለት የወርቁንና የብሩን መጥረቢያ ጨምሮ ሰጠው።

እንጨት ሰባሪው የወርቁንና የብሩን መጥረቢያ ይዞ እንደተመለሰም ሜርኩሪ በደግነቱ እንደሰጠው ለወዳጁ ነገረው።

ወዳጁም በመደሰት ፋንታ በውስጡ የምቀኝነት ስሜት አደረበት። ብዙም ሳይቆይ አሮጌ መጥረቢያውን ይዞ ወደ ተባለው ስፍራ ሄደ። እዚያ እንደደረሰም ዛፉ ላይ ወጣና እንጨት የሚቆርጥ መስሎ መጥረቢያውን ጣለው። ቀጥሎም “ኡ! ኡ! መጥረቢያዬን! መጥረቢያዬን! መጥረቢያዬን! ጣልኩ” እያለ መጮህ ጀመረ።

በዚህ ጊዜ ሜርኩሪ መጣና “ለምን ትጮሀለህ?” ሲል ጠየቀው። ሰውየውም “ይኸውና እንጨት ቆርጬ የምሸጥባት ያማረች መጥረቢያ ነበረችኝ። እሷም ውሃ ውስጥ ገባችብኝ። ከእንግዲህ ልጆቼን በምን እንጨት ቆርጬ አሳድጋቸዋለሁ” አለ።

ሜርኩሪ ወደ ውሃ ውስጥ ገብቶ አንድ በጣም ያማረ የወርቅና የብረት መጥረቢያ አወጣና “መጥረቢያህ የቱ ነው? የወርቁ ነው ወይስ የብረቱ?” ሲል ጠየቀው።

እንጨት ቆራጬም በጣም ስግብግብ ስለነበር “አዎን! እሱ ነው! የወርቁ ነው!” አለው።

ሜርኩሪ የሰውየውን መስገብገብና ሸፍጠኛ መሆን ተናደደና “ለዚህ እንኳንስ የወርቅ የብረትም አይገባውም” አለና ሁለቱንም ወደ ውሃው ወርውሮ ተሰወረበት ይባላል።

የራስ ያልሆነ ነገር ለማግኘት መሞከር የራስን ማጣት ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ ትዝብት ላይም ሊጥል እንደሚችል አባቶች ሲያስተምሩ ልብ ብለን ልናደምጣቸው ይገባል።   

የኤዞፕ ተረቶች - ተሸመ ብርሃኑ - እንደገና እንደተረከው

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
89 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1000 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us