እግር ኳስ ያፈረሰው የ14 ዓመት ትዳር

Wednesday, 11 July 2018 13:13

 

እግር ኳስ የአብዛኛው የዘመናችን ትውልድ የልብ ትርታ እየሆነ መጥቷል። አሁን አሁን እንደምንመለከተውም ሰዎችን በቡድን እየከፋፈለ ለከፍተኛ ፀብ እና ውዝግብም እየዳረገ ይገኛል። ከሰሞኑ በመካሄድ ላይ ያለው የ2018ቱ ዓለም ዋንጫም 14 አመታትን ያስቆጠረውን ትዳር አፍርሷል ይለናል የስካይ ኒውስ ዘገባ። ነገሩ እንዲህ ነው። የ40 ዓመቱ አርሰን እና የ37 ዓመቷ ላድሚይላ ሁለቱም ቅልጥ ያሉ የእግር ኳስ አፍቃሪዎች ናቸው። ጥንዶቹ የሚደግፉት የሀገራቸውን ተቀናቃኝ ቡድን ነው። ትዳር ለመመስረት የበቁትም እ.ኤ.አ. በ2002 በተካሄደው የዓለም ዋንጫ ወቅት ኳስ ለመመልከት በተገኙበት ስፍራ በተጠነሰሰ ፍቅር ነበር። ትዳራቸው ለ14 ዓመታት በሰላም የዘለቀ ቢሆንም፤ የ2018ቱ ዓለም ዋንጫ ግን የግንኙነታቸውን ክር በጥሶታል።

ባል እንደገለፀው ከሆነ ከባለቤቱ ጋር ብዙ ጊዜ በሊዮኔል ሜሲ እና በሮናልዶ ጉዳይ ይበሻሸቃሉ። ባል የሜሲ አድናቂ ሲሆን፣ ሚስት ደግሞ ስለ ሮናልዶ አውርታ የማትጠግብ ናት። የሰሞኑ የዓለም ዋንጫ እየተካሄደ ባለበት ወቅትም ሚስት እንደተለመደው ሜሲ ጨዋታ የማይችል መሆኑን አያነሳች ባሏን ማብሸቅ ትጀምራለች። ባል ለረጅም ጊዜ ማስቱን ቢታገሳትም እርሷ ግን ረገብ ልትል አልቻለችም። በሚስቱ ድርጊት አንጀቱ ያረረው ባልም፤ ሚስቱን በጥፊ ከመታት በኋላ እሷ ስለምታደንቀው ሮናልዶ እና የእግር ኳስ ክለብ መጥፎነታቸውን ይገልፁልኛል ያላቸውን ቃላት ሁሉ ይናገራታል። ይሄም አልበቃ ብሎት በቀጣዩ ቀን በከተማዋ ወደሚገኘው ፍርድ ቤት በማምራት ጋብቻውን ማፍረሱን የሚገልፅ የፍቺ ማመልከቻ አስገብቶ ከሚስቱ ጋር ተፋቷል። ኳስ የጠነሰሰው ትዳርም በ14 ዓመቱ በኳስ ፈርሷል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
87 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1019 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us