“እንዲያውም አልተቀበረችም”

Wednesday, 18 July 2018 16:19

 

እጅግ የሚዋደዱ ባልንጀራሞች ነበሩ። ያንደኛው እናት ሞቱና ሌላኛው ሳይቀብር በመቅረቱ ሲሸሸግ አንድ ቀን በመንገድ ላይ ይገናኛሉ። መውጫ ቀዳዳ የሌለበት ቦታ ስለነበረ ፊት ለፊት መጋፈጡን ተያያዘው።

 

“እማማ የሞተችለት ሰው በዝቶ ጋቢህን ይዤ ብጐትትህ አልሰማኽኝም። ከዚያም ወዲህ በጠና ታምሜ አሁን ሲሻለኝ ወዳንተ እየመጣሁ ሳለ በድንገት ተገናኘን” አለው አፉ እየተንቀጠቀጠ። ባልንጀራውም አለመምጣቱን በሚገባ ይረዳ ነበርና “ለመሆኑ የትኛው ቤተክርስቲያን ነበር የተቀበረችው?” ይለዋል።

 

“እንዴ! የተቀበረችውማ እናቲቱ ማርያም ነው” አለ በደመነፍስ።

 

“ኧኧ! እናቲቱ ማርያም?”

 

“አይ ልጅቱ ማርያም”

 

“ኧ! ልጅቱ ማርያም?” ብሎ ቢያጣድፈው “እንዲያውም አልተቀበረችም” ብሎ ሮጠ።  

 

ሙሻዙር - በመርሳዔ ሀዘን አበበ¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
32 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 91 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us