የመቃጠል ውድድር ተጀምሯል

Wednesday, 18 July 2018 16:21

በቻይናዋ ሁናን ግዛት ለ15 ቀናት የሚቆይ የሚጥሚጣ ቃሪያ መመገብ ፌስቲቫል በመካሄድ ላይ ይገኛል። ቻይና ዴይሊ እንዳስነበበው ፌስቲቫሉ በየዓመቱ ከፈረንጆቹ ሐምሌ አጋማሽ እስከ ነሐሴ መጀመሪያ የሚከናወን ሲሆን፤ በፌስቲቫሉ ላይም ጠንካራ ሚጥሚጣ ደፋሪ ነን ያሉ ተወዳዳሪዎች የሚጥሚጣ ቃሪያ ቀርቦላቸው በመመገብ ይወዳደራሉ። ተወዳዳሪዎች (ለውድድር የሚቀርቡት ሰዎች) እያንዳንዳቸው 50 ሚጥሚጣ ቃሪያዎች የሚቀርቡላቸው ሲሆን፤ እነዚህን ሚጥሚጣዎች ቀድሞ በልቶ የጨረሰ ሰውም አሸናፊ ይሆናል ተብሏል። ለተወዳዳሪዎች የሚቀርቡት ሚጥሚጣ ቃሪያዎች የቀሉ እና የማቃጠል ደረጃቸውም ከፍተኛ መሆኑ በምርምር የተረጋገጠ መሆናቸው ተገልጿል። በዘንድሮው ፌስቲቫልም አስር ተወዳዳሪዎች ለፍልሚያ የቀረቡ ሲሆን፤ ለውድድሩ የቀረቡት ሚጥሚጣ ቃሪያዎችም የማቃጠል ደረጃቸው በመለኪያ መሣሪያው ከ30 ሺህ እስከ 50 ሺህ ባለው መካከል የሚገኙ መሆኑ ተገልጿል። በውድድሩ ወቅት የተለየ ችግር የተከሰተበትን ተወዳዳሪ ለመርዳት በማሰብም በፌስቲቫሉ ስፍራ ዶክተሮች እንዲገኙ ተደርጓል። ተወዳዳሪዎቹ በእንባ እየታጠቡ ሚጥሚጣዎቹን ሲያዳሽቁ ታይተዋል። በየዕለቱ አስር አስር ተወዳዳሪዎች እንደሚኖሩ የተገለፀ ሲሆን፤ ፌስቲቫሉ እስከ ነሐሴ መጀመሪያ እንደሚዘልቅም ተነግሯል።¾

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
63 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 93 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us