እናመሰግናለን!!

Wednesday, 11 January 2017 14:14

በወልድያ ከተማ የተገነባው የ“ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ ስታዲየምና የስፖርት ማዕከልቅዳሜጥር 6 ቀን 2009 . ተመርቆ ንብረትነቱ በይፋ ለወልድያ አስተዳደርና ሕዝብ ይተላለፋል። የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አልአሙዲ ይህን ታላቅ የሕዝብ ፕሮጀክት ጎን በመቆም ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ አውጥተው በፋይናንስና በቴክኒክ ረገድ ያደረጉት ድጋፍ የወልድያ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚረሳው አይደለም። ስታዲየሙ ወልድያ ቢገነባም ሐብቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጭምር በመሆኑ ያኮራል። ሼህ ሙሐመድ ለዚህ ታላቅ ሥራቸው እናመሰግናቸዋለን።

ፕሮጀክቱን በሙያ ረገድ በመምራትና በአጭር ጊዜ ውስጥ ሀገራዊ አቅም ጭምር በመፍጠር ለውጤት እንዲበቃ ያላሰለሰ ጥረት ያደረጉት የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር እና የፕሮጀክቱ ዋና መሪ የሆኑትን ዶ/ር አረጋ ይርዳውን  እናመሰግናቸዋለን።

በተጨማሪም በግንባታው ሒደት በቀጥታም በተዘዋዋሪም የተሳተፉ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ አባል ኩባንያዎችና ሠራተኞቻቸው ይህንን የመሰለ ስታዲየም ግንባታ ላይ አሻራቸውን በማሳረፋቸው እናመሰግናቸዋለን።

የአማራ ክልል መንግሥት፣ የሰሜን ወሎ ዞን፣ የወልድያ ከተማ አስተዳደር ከምንም በላይ ደግሞ የወልድያ ከተማ ሕዝብ አቅሙ የፈቀደውን ሁሉ በማድረግ ፕሮጀክቱን እንዲሳካ ላደረጉት ርብርብ እናመሰግናቸዋለን።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
251 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us