ኢህአዴግ “አውራ ፓርቲ ነኝ” እያለ፤ ሲደክመው እያረፈና ሲያረጅ እየታደሰ በገዢነት ሊቀጥል አይችልም

Friday, 12 January 2018 17:01

በኢትዮጵያ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ በስልጣን ላይ የቆየው ኢህአዴግ በፈተና ውስጥ ነው። ፓርቲው የገጠመውን ፈተና ለመወጣት በበርካታ ፓርቲያዊ ስብሰባዎች በማድረግ ላይ ተጠምዷል። ኢህአዴግ በዚህ አይነት ፈተና ውስጥ የገባው ከባድ ህዝባዊ ተቃውሞ ከገጠመው በኋላ ነው። ፓርቲው አሁን ባለው ቁመና ሲታይ ራሱን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር እያስተካከለ የመሄድ ችግር እንዳለበት የሚያሳዩ በርካታ ማሳያዎች አሉ። ለምሳሌ፤ የሕግ የበላይነት አለመኖር፣ የኔትወርክ መረብ አባዜ፣ ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን በአደባባይ መጣስ የመሳሰሉ ናቸው። እነዚህም ሁኔታዎች ኢህአዴግ እንደ ፓርቲ ብሎም እንደ መንግስት ከባድ ፈተና ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል። ምርጫ 97 ተከትሎ ፓርቲው የወሰዳቸው በርካታ እርምጃዎች ዛሬም መልሰው ጠልፈው ለመጣል እያንገዳገዱት ይገኛሉ። በፓርቲው ውስጥ ሊፈተሹ ከሚገባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች መካከል አንደኛው ፓርቲው ራሱን የሚያይበት መነፅርና ይሄንንም ተከትሎ በተግባር የሚሄድበት የፖለቲካ መስመር ነው።

 አሁን ባለው ራስን የማደስ ሂደት ውስጥ ሊፈትሻቸው ከሚገቡ በርካታ ጉዳዮች አንዱ የአውራ ፓርቲ አስተሳሰቡ ነው። በድርጅቱ የቅርብ ታሪክ መሰረት የኢህአዴግ መለያ ባህሪያት ተደርገው ከሚነሱት ጉዳዮች መካከል አንዱ ፓርቲው ለራሱየአውራ ፓርቲነትስያሜን መስጠቱ ነው።

 በዚህ የፓርቲ ፅንሰ ሀሳብ መሰረት አንድ ፓርቲ አውራ ፓርቲ ከሆነ በተግባር ለመድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲ ያለው አተያይ ያን ያህል ገንቢ ሆኖ አይታይም።አወራ ፓርቲ ነኝብሎ ራሱን የሰየመ አንድ ፓርቲ በሀገር ፖለቲካ ውስጥ ለራሱ ያለው አተያይ ፍፁም የገዘፈ ነው።

 በአንፃሩ ሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎችን የሚመለከተው ለብሄራዊ ዲሞክራሲ ሊኖራቸው በሚችለው በጎ ግብዓት ሳይሆን በስልጣን ባላንጣነት መነፅር ብቻ ነው። አውራ ፓርቲ እንደ ኮሚኒስት ፓርቲ ራሱን ብቸኛ የሀገር ወኪልነት በመቁጠር የሌሎች ዜጎችን በፓርቲ ተደራጅቶ የመታገል ተግባርን በህግ ደንግጎ ክልከላ የሚያደርግበት ሁኔታ የለም። ይህ ብቻ ሳይሆን ተፎካካሪ ፓርቲዎቹ ህልውና እንዲኖራቸው የህግ ድጋፍ ሲሰጣቸውም ይታያል።

ሆኖም ተፎካካሪ ፓርቲዎች የፖለቲካ ሜዳው ተመቻችቶላቸው ወደ ገዢነት ሥልጣን እንዳይመጡ ግን በተግባር አምርሮ ይታገላቸዋል። የፖለቲካ ሜዳ መደላድል እንዳይፈጠርላቸው ያደርጋል። በማንኛውም አጋጣሚ መንግስታዊ ሥልጣን ሊይዙ ይችላሉ ብሎ ያሰባቸውን ተፎካካሪዎች  በሀሳብ ቀርቦ ከመወያየትና በውድድሩ ሜዳ ከመፎካከር ይልቅ በባላንጣነት ፈርጆ በጥብቅ ይታገላቸዋል። አውራ ፓርቲ ራሱን እንደብቸኛ የሀገር ባላደራስለሚቆጥር የሌሎችን ተፎካካሪ ፓርቲዎች አስተሳሰብና አቋም ያለርህራሄ ይፈርጃል ፤ይታገላልም።

 ፓርቲው ራሱን እያገዘፈ የሚሄደው ሌሎችን በማቀጨጭ ነው። ዋርካ ሥር ያሉ ሌሎች ዛፎች ዋርካው አርጅቶ እስካልተገነደሰ ድረስ በቂ ምግብና አየር አግኝተው እንደማያድጉ ሁሉ በአውራ ፓርቲ ገዢ ፓርቲ ሥር በሚተዳደር ሀገር ውስጥ ያሉ ተፎካካሪ ፓርቲዎችም እጣ ፈንታ ይህ ነው። ኢህአዴግአውራ ፓርቲ ነኝብሎ ራሱን እስከሰየመ ድረስ ፓርቲው የሚፈተሸውና የሚታየውም በዚሁ የአውራ ፓርቲ ትርጓሜና ባህሪ ነው።

 ኢህአዴግ በሚሊዮን ይቆጠራሉ በሚላቸው በአባላቱ ብዛት፣ የወጣትና ሴቶች ሊግ እያለ በሚጠራቸው አደረጃጀቶች ራሱን አግዝፎ ሲታይ፤ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በአንፃሩ ይህ ነው የሚባሉ ፅህፈት ቤቶች እንደዚሁም ደጋፊዎቻቸውንና አባላቶቸውን ሊያደራጁ የሚችሉበት ድርጅታዊ መዋቅር እንኳን የላቸውም። ቀላል የማይባሉት ፓርቲዎች የምርጫ ሰሞን ብቅ ብለው በምርጫው ማግስት ደብዛቸው የሚጠፋ ነው።

ከዚህም ባለፈ ኢህአዴግ የሚፈልገው በፖለቲካ መስመር ልዩነት በነጠረ አቋም የሚታገለው ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲ ሳይሆን ታማኝ ፓርቲ (Lolayl Party) መሆኑን በተግባር እያሳየ ነው። አሁን በኢትዮጵያ እየተከሰተ ያለው ችግር በሀገሪቱ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት መዳበርን የግድ የሚል ሆኖ እየታየ ነው። ለዚህ መፍትሄ የሚሆነው ደግሞ ገዢው ፓርቲ ከሁሉም በፊት ራሱን ከሰቀለበት የአውራ ፓርቲነት ማማ ማውረድ ሲችል ነው። ፓርቲው በፖለቲካ ፕሮግራሙ ቅኝት ብቻ ሳይሆን በህገመንግስቱ የመድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲ መርህ ሊመራ ይገባል። ዜጋና ህዝብ በፓርቲ አደረጃጀትና በልዩ ልዩ አደረጃጀቶች እየተደራጀ መታገል፣ አማራጭ ሀሳቦችን ማቅረብና የመንግስት ስልጣንን ጭምር ሊይዝ የሚችልበት እድል ካልተፈጠረ ውጤቱ የቀውስ አዙሪት ነው።

ኢህአዴግአውራ ፓርቲ ነኝበሚል አስተሳሰብ በስልጣን ማማ ላይ ተኮፍሶ ሲደክመው እያረፈና ሲያረጅ እየታደሰ በገዢነት መቀጠል እንደሚችል አድርጎ ከማሰብ አስተሳሰብ መውጣት አለበት።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
101 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 927 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us