“ስበበኛ” ፊልም ቅዳሜ በሁሉም የግል ሲኒማ ቤቶች ይመረቃል

Saturday, 12 October 2013 15:00

በኤ.ቢ. ፊልም ፕሮዳክሽን የተሰራውና በዳይሬክተር ፍፁም ካሳሁን ዳይሬክት የተደረገው “ስበበኛ” የተሰኘ አዲስ ኮሜዲ ፊልም የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 2 ቀን 2006 ዓ.ም በሁሉም የግል ሲኒማ ቤቶች ተመርቆ ለዕይታ ይበቃል።

ከዚህ ቀደም “ስስት” እና “አላዳንኩሽም” በተሰኙት ፊልሞቹ የሚታወቀው ዳይሬክተሩ ፍፁም ካሳሁን ይህን “ስበበኛ” የተሰኘ ፊልም ለመስራት የ1 ዓመት ጊዜን እንደወሰደበት ታውቋል።

“ስበበኛ” ፊልም ላይ የጊዮርጊስ እና የቡና ክለብ አስጨፋሪዎቹን ይድነቃቸው አሸናፊ (አቸኖን) እና አዳነ ሽጉጤን ጨምሮ ዮሐንስ ተረፈ፣ ዳዊት አባተ፣ ፅናት አስቻለውንና ሌሎችንም ወጣትና አንጋፋ ተዋንያን ተሳትፈውበታል።

ኤ.ቢ.ፊልም ፕሮዳክሽን ለበርካታ ፊልሞችና ድራማዎች አዳዲስ ተዋንያንን በማብቃት የሚታወቅ የፊልም ፕሮዳክሽን እንደሆነም አዘጋጆቹ ተናግረዋል።

Last modified on Saturday, 12 October 2013 15:01
ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
17082 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us