ኢትዮጵያዊቷ የግራሚ ሽልማት ዕጩ

Wednesday, 08 October 2014 12:55

በጥበቡ በለጠ

 

በአሜሪካ ውስጥ አድገውና ወደ ሙዚቃው ዓለም ገብተው ትልልቅ ስምና ዝና እያፈሩ ከሚገኙት ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መካከል አንዷ ድምፃዊት ወይኗ ትጠቀሳለች። ወይኗ ገና በልጅነቷ ወደ አሜሪካ አቅንታ ከዚያም በተፈጥሮ ዝንባሌዋ ወደ ሙዚቃው በማዘንበል ታዋቂ ድምጻዊት በመሆን የተለያዩ ሥራዎችን ለሕዝብ አቅርባለች። የተለያዩ የአሜሪካ ቴሌቭዥን ጣቢያዎችና ሌሎች የመገናኛ ብዙሃንም ወይኗ ከጥቁር የአሜሪካ ድምፃዊያን ተርታ በማስቀመጥ ወደፊትም ተስፋ የሚጣልባት ወጣት ከያኒት እንደሆነች ዘግበዋል።

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ወይኗ በሙዚቃ ሥራዎቿ ለአሜሪካ የግራሚ ሽልማት ዕጩ ሆናም የተመረጠች ከያኒት ነች። ይህች ወጣት ሙዚቃን ከማቀንቀን ውጪም የግጥም ፀሐፊና የዜማ ፈጣሪም መሆኗ ተዘግቧል። ከሰሞኑም በወጣው ‘Essence Magazine’ ተብሎ የሚታወቀው መፅሔት ስለዚህች ከያኒት ሲዘግብ የአፍሪካን የሬጌ ሰዓት ድምፅ የምታሰማ ሙዚቀኛ መሆኗን ያስረዳል። እንደ መፅሔቱ ዘገባ በዓለም ላይ እጅግ ታዋቂ የሆነው አይነስውሩ ሙዚቀኛ ስቲቭ ዎንደር ስለ ኢትዮጵያዊቷ ወይኗ ሲናገር ድንቅዬ /Incredible/ ብሏታል በማለት ገልጿል።

ይህች ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ከሰሞኑ ደግሞ በሂፕ ሆፕ ሙዚቃ ዓለምአቀፍ ዝናን እያተረፈች ከመጣችው /Akua Natu/ ጋር በመሆን በመጪው ጥቅምት ወር ኒውዮርክ ውስጥ ትልቅ የሙዚቃ ኮንሰርት ሊያቀርቡ እንደሆነ ተገልጿል።

በኒውዮርክ እና በሌሎች ከተሞችም ቢል ቦርድ ተሰርቶላቸውም ሰፊ የማስታወቂያ ሽፋን እንደተሰጣቸውም ተዘግቧል።

Akua Natu፡- The Journey Aflame በተሰኘው አልበሟ በዩናይትድ ስቴትስ ባሉ የኮሌጅ ሬዲዮ ጣቢያዎች ምርጫ አንደኛ የወጣ እንደሆነም ተገልጿል።

ሁለቱ ወጣት አቀንቃኞች በተለይ የጥቁር አሜሪካዊያንን ሕይወት፣ ኑሮዋቸውን፣ የሚፈፅምባቸውን የቀለምና የዘር መድልዎ በተመለከተ መሠረታዊ ጭብጣቸው እንደሚያተኩር ተፅፏል።

እ.ኤ.አ. October 23 ቀን 2014 ዓ.ም በኒውዮርክ ከተማ Davis Rubenstein Atrium Lincoln በተሰኘው ማዕከል ውስጥ ያቀነቅናሉ።

ይምረጡ
(2 ሰዎች መርጠዋል)
11494 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us