የሶሻሊስቶቹ እና የኮሚኒስቶቹ አስተሳሰቦች ፍፃሜ

Wednesday, 08 October 2014 13:00

የሌሊን ሀውልት ከ25 ዓመታት በኋላ ወደቀ። የኮሚኒዝም ፍልስፍና እና አስተሰሰብ ውስጥ የሩሲያን አብዮት በመምራትና ታላቋን ሶቭየት ህብረት በመምራት ትልቅ ተፅዕኖ ፈጣሪ የነበረው ብላድሚር ኤሊንች ሌኒን በሶሻሊስት ዓለም አስተምህሮቱና ፍልስፍናው ተቀባይነት ኖሮት ለበርካታ ዓመታት ቆይቷል።

ታላቋ ሶቭየት ህብረት ከዛሬ 25 ዓመታት በፊት ኃይሏና አንድነቷ ተላቆ ብትንትን ስትል የሌሊን እና የሌሎችም የኮሚኒዝም ፍልስፍና አብሮ ከሰመ። ሶሻሊዝም /ሕብረተሰባዊነትም/ ፋሽኑ ያለፈበት ፍልስፍና ነው ተብሎ ከብዙዎች አእምሮና አስተሳሰብ ተሸረሸረ። የሶሻሊዝሙ ዓለም በለውጥ ተናጠ። በዚህ ጊዜ በየሀገሩ በሶሻሊስት መሪዎች አማካይነት የቆሙ የሌሊን፣ የማርክስና የኤንግልስ ሀውልቶች መፈራረስ ጀመሩ።

በኛም ሀገር እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ የቀድሞው የሀገሪቱ አምባገነን መሪ ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያም አገር ጥለው ሲወጡ በአመራራቸው የተበሳጨው የአዲስ አበባ ህዝብ እየተንደረደረ ወደ ሌኒን ሀውልት ሮጦ በመሔድ ሀውልቱን ከቆመበት ቦታ አውርዶታል።

ከዛሬ 25 ዓመታት በፊት የነ ሌኒንን ሀውልት በተለያዩ ሀገሮች ውስጥ ማፍረስ የተለመደ ነበር። በቅርቡ ደግሞ የሩሲያ ወዳጅ የነበረችው ዩክሬን ወደ ከፋ ግጭት ውስጥ ከመግባቷም በተጨማሪ የዓለምን ኃያላን መንግስታት ትኩረት ስባ የልዩነት ግጭት የቆሰቆሰች ሆናለች። በየጊዜው ከሚፈጠረው የአፍቃሬ ሩሲያ እና የነፃይቱ ዩክሬን አስተሳሰብ አራማጆች በሚፈጥሯቸው ግጭቶች አያሌዎች ህይወታቸው አልፏል።

ትናንትና ደግሞ በዩክሬኗ ትልቋ ሁለተኛ ከተማ ውስጥ ማለትም ‘Kharkiv’s’ ውስጥ በተለይ የሌሊን ሀውልት ዙሪያ የተሰበሰቡት ሰላማዊ ሰልፈኞች በመጨረሻም ለበርካታ ዓመታት የቆመውን ይህንኑ ሀውልት አፍርሰው ጥለውታል።

በቢቢሲ ዜና ላይ እንደተገለፀው የዩክሬን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር Arsen Avakov በቲውተር ገለፃቸውላይ እንደፃፉት፣ የሌሊን የሶሻሊዝም ፍልስፍና ያመጣብን ነገር ችግርን ነው። ስለዚህ እንፈልግህም የሚል ሃሳብ ሰንዝረዋል።

አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ደግሞ የሌሊን ሀውልት መፍረስ የሶሻሊስቱና የኮሚኒስቱ አስተሳሰብ ባህልና እምነት የመጨረሻው ግብዐተ መሬት መጠናቀቂያው እንደሆነ ያወሳሉ። የሌኒንን ሀውልት መፍረሱን የሚቃወሙ ሰዎች በመጥፋታቸውም የኮሚኒዝም ባህል ዛሬ ከሰዎች አእምሮ ውስጥ ተኖ ተጠፍቷል ተብሏል።

    በቀደመው ዘመን የዚህን የሶሻሊስቱን እና የኮሚኒስቱን አስተሳሰብ ከሰዎችና ከማህበረሰቦች ባህልና እሴት ውስጥ በመክተት እንደ ራሱ የተፈጥሮ ባህል እንዲያደርገው ብዙ ጥረት ተደርጎ ነበር። ዛሬም ድረስ እንደ ስርዓተ ትምህርት ይህ አስተሳሰብ በሚሰጥባት ሩሲያ ፍልስፍናው የመጨረሻው ሞቱ ላይ ነው እየተባለም ነው። ‘ኮሚኒዝም በሶሻሊዝም ውስጥ ይወለዳል’ የሚለው ፍልስፍናው አስተሳሰቡ ካለ ወላጅም፣ ካለ ልጅም መቅረቱ አሳሳቢ ነው ተብሏል።

ይምረጡ
(9 ሰዎች መርጠዋል)
17892 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 822 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us