ኢትዮጵያዊውን ያገቡት ቀዳማዊት እመቤት ሲነፋረቁ ዋሉ

Thursday, 16 October 2014 14:24

በጥበቡ በለጠ    

 

ባሳለፍነው ሳምንት የአሜሪካ ጋዜጠኞች ለረጅም ጊዜ ሲሰሩት የነበረው የምርመራ ጋዜጠኝነት አንድ ያልተለመደ ምዕራፍ ላይ ደርሷል። ካሜራዎቻቸውን፣ የድምፅ መቅረጫዎቻቸውን ይዘው ለወራት በየስርቻው እየገቡ ምስጢር ሲጎረጉሩ የቆዩት እነዚህ ጋዜጠኞች በመጨረሻም ተመርማሪዋ ራሳቸው አደባባይ ላይ ወጥተው ድብቅ ምስጢራቸውን በተለይም ከአንድ ኢትዮጵያዊ ጋር ያደረጉትን ወይም የፈፀሙትን ስህተት ይፋ አውጥተዋል።

ሴትየዋ የኦሪገን ግዛት ቀዳማዊት እመቤት ናቸው። በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ በመሆን ይታወቃሉ፡ የሰብዓዊ መብቶች ላይ እና በማህበረሰባዊ ጉዳዮች ላይ ስምና ዝናቸው ጎልቶ የሚነገርላቸው ሆነዋል። እኚህ ሴት የኦሪገን ግዛት ቀዳማዊት እመቤት ሲልቪያ ሄይስ ይባላሉ።

በሳምንቱ መገባደጃ ላይ አያሌ ጋዜጠኞች በታደሙበት አዳራሽ ውስጥ ቀዳማዊት እመቤቲቱ ሲልቪያ ሄይስ የቀድሞ ምስጢራቸውን ዘረገፉት።

ሲልቪያ ከ12 ዓመታት በፊት ሲያትል አካባቢ በሚገኘው ኤቨር ግሪን ኮሌጅ ውስጥ ይማሩ ነበር። በዚህ ጊዜ አንድ ሰው ከአንድ ኢትዮጵያዊ የ17 ዓመት ወጣት ከሆነ ልጅ ጋር ያስተዋውቃቸዋል።

ያ ኢትዮጵያዊ በአሜሪካ ውስጥ የመኖሪያ ፈቃድ የለውም። ለመኖርና ለመማር ብሎም የተሻለ ሰው ለመሆን ዜግነት ካላቸው ሴቶች ጋር መጋባት አለበት። በዚህ አጋጣሚ ሲልቪያን ይጠይቃታል። ሲልቪያ ደግሞ በወቅቱ የገንዘብ ችግር ነበረባት። አምስት ሺ ዶላር ክፈለኝ ትለዋለች። ይከፍላታል። ሲልቪያ እና ኢትዮጵያዊው ወጣት እ.ኤ.አ. በ1997 ዓ.ም ተጋቡ።

ኢትዮጵያዊው ወጣትም የመኖሪያ ወረቀት አገኘ። ትምህርቱንም ተምሮ ጨረሰ። በኋላ ደግሞ እ.ኤ.አ. በ2002 ዓ.ም ይህ ኢትዮጵያዊ ወጣት እና የአሁኗ ቀዳማዊት እመቤት የድሮዋ የኢትዮጵያዊው ሚስት ህጋዊ ፍቺ ፈፀሙ። ተለያዩ።

ከዚያ በኋላ በመጣው የህይወት ጉዞ ውስጥ የሲልቪያ ሄይስ እንቅስቃሴ ተቀየረ። ፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ ሆነች። ስለ ሰብዓዊ መብቶችና ስለ አሜሪካ መንግስት ህግና ስርዓት ቋሚ አክቲቪስት በመሆን ታዋቂ ሆነች። የአሜሪካንን ሕግና ደንብ በማስከበር እንደ እርሷም ሽንጡን ገትሮ የሚከራከር ጠፋ።

በመጨረሻም የኦሪገን ግዛት ገዢ ከሆኑት ከጆን ኪትዝሀበር ጋር ይተዋወቃሉ። ቀጥሎም ጋብቻ ይፈፅማሉ። አብረውም መኖር ይጀምራሉ። ነገር ግን ሲልቪያ ሄይን ከኢትዮጵያዊው ጋር የፈፀመችውን የቀድሞ ጋብቻ አልተናገረችም ነበር።

የጋዜጠኞቹ የምርመራ ስራ እየገፋ ሲመጣ ቀዳማዊት እመቤቲቱ አደባባይ ወጥተው አሜሪካንን እና ባለቤታቸውን ይቅርታ ጠየቁ። የሰራሁት ስራ ወንጀል ነው። መኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት የሚፈልግን ስደተኛ ለአምስት ሺ ዶላር ብዬ አግብቸዋለሁ። የአሜሪካንን ህግና ደንብ አላከበርኩም። ከዚህም በላይ ባለቤቴን ጆንን ዋሽቸዋሁ እያሉ ተንሰቀሰቁ ተነፋረቁ።

የኦሪገንን ግዛት ህዝብ ይቅርታ ጠየቁ። ከኢትዮጵያዊው ወጣት ጋር ጋብቻ መፈፀማቸው ትክክል እንዳልነበር ይፋ አደረጉ። የሚጣልብኝን ቅጣት ሁሉ እቀበላሁ ብለዋል።

የአሜሪካ መንግሥት መረጃ እንደሚያመለክተውና ባለፈው ሀሙስ በወጣው ጥቆማ መሠረት የቀዳማዊቷ እመቤት የሲልቪያ የቀድሞ ባል ኢትዮጵያዊው ወጣት አብርሃም ቢ እንደሚባል ጠቅሶ፣ አሁን የሚኖረው ዋሽንግተን ውስጥ እንደሆነም ይገልጻል።

ቀዳማዊት እመቤቲቱ እንደገለፁት ደግሞ እ.ኤ.አ ከ2002 ዓ.ም በኋላ ከዚህ ኢትዮጵያዊ የቀድሞ ባላቸው ጋር ተገናኝተን አናውቅም ብለዋል።

      በአሜሪካ ውስጥ የተለያዩ የጋብቻ ባህሎች እየተስፋፉ ነው። የወረቀት ጋብቻ፣ የቪዛ ጋብቻ፣ የትምህርት ጋብቻ እና ሌሎችም አይነቶች የጥቅማ ጥቅም ጋብቻዎች እየመጡ ነው ተብሏል።

ይምረጡ
(4 ሰዎች መርጠዋል)
17496 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 714 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us