“የአማርኛ ፊደላትን ስለማሻሻል” በሚል ርዕስ የተካሄደው ውይይት በውዝግብ ተጠናቀቀ

Thursday, 03 October 2013 19:19

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋ እና ስነ-ልሳን መምህር በሆኑት ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ ጥናታዊ ፅሁፍ ላይ ተመስርቶ ባሳለፍነው እሁድ መስከረም 12 ቀን 2006 ዓ.ም በብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መፃሃፍት አዳራሽ በርካታ ታዳሚያን በተገኙበት የተካሄደው ውይይት እልባት ሳያገኝ በውዝግብ ተጠናቀቀ።

 

“የአማርኛ ፊደላትን ስለማሻሻል” በሚለው የዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ ጥናት ውስጥ የሆሄያትን ድግግሞሽና የማጥበቅና የማላላትን ጉዳይ ተከትሎ በተነሳው ሰፊ ውይይት የበርካቶች ኀሳብ የተንሸራሸረ ሲሆን፤ ጥናት አቅራቢው፣ “የሞክሼ ፊደላት መብዛትና ጠብቀውና ላልተው የሚነበቡ ፊደላት መኖር ለአማርኛ ቋንቋ የፅሁፍ ችግር ፈጥሯል” የሚል ሀሳብ ከመሰንዘራቸውም በተጨማሪ ተደጋጋሚ ድምፅ ያላቸው ሆሄያት ቢወገዱና በነጠላ ቢቀመጡ እንደሚሻልና በመጥበቅና መላላቱም ላይ ምልክት ኖሮ የማያሻማ አነባበብ ቢፈጠር መልካም ነው የሚል ሀሳባቸውን አቅርበዋል።

 

በመድረኩ የተገኘው አብዛኛው የውይይቱ ተሳታፊ ግን ሆሄያቱ ቢገደፉ፣ ታሪክ ይጠፋል፣ ሃብትነታቸውና ቅርስነታቸውን እናጣለን እንዲሁም ያለፉትን መዛግብት ለማገላበጥ እንዳንችል እንቅፋት ይሆንብናል የሚል ሀሳብ አቅርቧል። ውይይቱ በሚውዚክ ሜይ ዴይ አስተናጋጅነት የተካሄደ ሲሆን፤ ያልተቋጨው ውይይትም በብራና ሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ሊቀጥል እንደሚችል አዘጋጆቹ ቃል ገብተዋል።

Last modified on Monday, 07 October 2013 09:57
ይምረጡ
(3 ሰዎች መርጠዋል)
16705 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us