ጀማይካ፣ እስራኤልና ኢትዮጵያ ሲጣመሩ

Wednesday, 11 June 2014 13:41

በጥበቡ በለጠ

 

 

ሙዚቃ ታሪክን፣ ባህልን፣ ፍቅርን እና ልዩ ልዩ ገጠመኞችን በመግለፅ የምታገለግል የጥበብ መንገድ ናት ይላሉ ሰሞኑን አንድ ታሪካዊ የሙዚቃ አልበም ያሳተሙ ሶስት ትውልዶች። አንደኛው ትውልድ የኢትዮጵያ፣ ሌላኛው ደግሞ የጀማይካ ሊሆን ሶስተኛው ደግሞ እስራኤላዊ ናቸው። ሶስቱ በጥምረት አንድ አልበም አወጡ። እንዴት ሶስትም አንድም ሆኑ ብላችሁ መጠየቃችሁ አይቀርም።

ሙዚቀኞቹ ታሪካቸው ሲተርኩት እንዲህ ይላሉ። እ.ኤ.አ. April 26 ቀን 1966 ዓ.ም የኢትዮጵያው ንጉሡ ነገስት ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ጀማይካን ጎበኙ። በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ራስ ተፈራዊያን በየአደባባዩ ወጥተው ተቀበሏቸው። እጅግ ደስተኞች ሆነው ሲደሰቱ ሲጨፍሩ ሲዘፍኑ ቆዩ። ንጉሡ ወደ ጀማይካ የመጡበትን ዓመትም እንደ ታሪካዊ ቀን በየዓመቱ ያከብሩታል።

ከንጉሡ ጉብኝት በኋላም ራስ ተፈሪያዊኑ ቅድስት ሀገር ወደሚሏት ኢትዮጵያ መጡ። መሬት ጀመሩ። ከ18 ዓመት በኋላ ደግሞ ሌላ የዚህ ተቃራኒ የሆነ ሌላ ክስተት ተፈጠረ። ክስተቱ ደግሞ በርካታ ኢትዮጵያዊያን እና ቤተ -እስራኤላዊን ቅድስት ሀገር ብለው ወደሚጠሯት እስራኤል ተጓዙ። ለጀማይካዎቹ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ናት። ብቻ ይህ አስተሳሰብ ከመከራከሪያ አልቆ የፍልስፍና ሀሳብ ማመንጫም ሆነ።

ታዲያ ከዚህ ሁሉ ፍልስፍና በኋላ የመጡት አዲሶቹ ትውልዶች አንድ ሃሳብ አመጡ። ለምን በጋራ ሆነን ይህን ሁሉ ታሪካችንን የሚዘክር ሙዚቃ አንሰራም ብለው Ethiopian Reggae በሚል ርዕስ ከእስራኤል፣ ከጀማይካ እና ከኢትዮጵያ የተውጣጡ ሙዚቀኞች አንድ አልበም አሳተሙ።

ከሙዚቀኞች አንዱ የሆነው ያሎ ሲናገር፣ ከኢትዮጵያዊ የተወለድኩት ጎንደር ሲሆን፣ ከጎንደር ተነስተን ረጅም ኪሎ ሜትሮች ተጓዝን። ወደ ኢትዮጵያ የኔ ቤተሰብ ወይም የዘር ሀረግ የመጣው የዛሬ ሶስት ሺ ዓመታት ግድም ነው። እኛ ይሁዲዎች ነን። ኢትዮጵያ ውስጥ ረጅም ዘመን የዛፍ ሀገረጋችን ቆይቷል። ስለዚህም ‘የኢትዮጵያን ጂው’ እየተባለን ነው የምንጠራው።

ጎንደር ውስጥ ኑሯቸውን የድህነት እንደነበር አስታውሳለሁ። የተመጣጠነ ምግብ እንደ ልብ ማግኘትም ከባድ ነው። የ1977 ዓ.ም የኢትዮጵያ ድርቅ ሲከሰት መኖርም ስላለብን አካባቢያችንን ጥለን ተሰደድን። እኔ የዚያን ጊዜ የአራት ዓመት ልጅ ነበርኩ። ረጅሙን የበረሃ ጉዞ ጀመርነው። በዚያ ጉዞ ላይ አባቴ እኔን ማጅራቱ ላይ ተሸክሞኝ ነገር የሚጓዘው። ታዲያ እዚያ ማጅራቱ ላይ ሆኜ እየዘፈንኩ እንደምሔድ አስታውሳለሁ። በረሃውን፣ ችግሩን፣ መከራውን በነፃነት እየዘፈንኩበት እጓዝ ነበር።

ከዚያ ሁሉ ጉዞ በኋላ ሱዳን ገባን። ሱዳን ደግሞ የስደተኞች መጠለያ ውስጥ ለበርካታ ወራት ተቀመጥን። ታዲያ አንድ ቀን ምሽት ላይ ትልልቅ መኪናዎች መጡና ከስደተኛው ካምፕ አውጥተውን ወደ ሌላ ስፍራ ሲወስዱን አደሩ። እዚያ እንደደረስን አውሮፕላኖች መጡና በምስጢር ይዘውን አየር ላይ ወጡ። ምን ተአምር ሊፈጠር ነው ብዬ ተጨንቄያለሁ። በመጨረሻም ያ አውሮፕላን መሬት ላይ አረፈ ውረዱ ተባልን። ስንወርድ ይህች ሀገር እስራኤል ናት አሉን። ቅድስቲቱ ሀገርም ገባን ይላል።

     በእስራኤል ውስጥ በነበረው እድገት እና ትምህርትም ሙዚቃን የዘወትር ስራው እንዳደረጋት ይናገራል። ታዲያ አሁን ደግሞ የእርሱን ማለትም የራሱን የእድሜ እኩዮቹ ኢትዮጵያውያንን፣ ጀማይካዊያንን እና በተ እስራኤላዊያንን በማስተባበር አዲስ አልበም ሰርተው Ethiopian Reggae ብለው አሳትመዋል።


ይምረጡ
(4 ሰዎች መርጠዋል)
12098 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us