ሸማችና ነጋዴ

Wednesday, 17 December 2014 11:47

ከኪዳኔ መካሻ

This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. '; document.write(''); document.write(addy_text24245); document.write('<\/a>'); //-->\n This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

-    ሸማቾችን ለመጠበቅ የተደነገጉ ሕጎች ምን ይላሉ

-    ሸማቾች የሚባሉት እነማን ናቸው፣

-    የሸማቾች መብቶችና የነጋዴዎች ግዴታ ምን ይመስላል፣

ሰላም ነው እንዴት ናችሁ? ዛሬ ወደ ገበያው ገብተን ሸማቾችና ነጋዴዎች ስለሚመሩበት ሕግ ስለመብትና ግዴታቸው ሸማቾች በሕግ ስለተሰጣቸው ጥበቃ እናነሳለን። ዋነኛ ማጣቀሻ ሕጋችን መጋቢት 12 ቀን 2006 ዓ.ም የወጣው የንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/2006 ነው፡ እንቀጥል፡-

1.በሸመታ ላይ፡-

አንድ ሰሞን የተጀመረ ንግድ ነበር። ብዙዎች በአትራፊነቱ ማለው ተሰማርተውበታል። እዚህ ንግድ ውስጥ ሁሉም ነጋዴ ነው። ዓላማው አንዱን አገልግሎት ወይም እቃ ሸጦ መጠቀም ብቻ አይደለም። የሚገዙት የሚሸጡት የወርቅ ወይም የብር ሳንቲሞች ሰዓሰቶች ሀብሎች እና መሰረታዊ ያልሆኑ እቃዎች ናቸው። ሻጭ በስሩ ለሁለት ለሶስት ሰው በሸጠ ቁጥር ኮሚሽን ያገኛል። ከሱ የገዙ ሰዎችም ያንን እቃ ባሻሻጡ ቁጥር ገንዘብ ያገኛሉ። ኩዌስት ማርኬቲንግ ይባል ነበር። ይህ የሰንሰለት ሽያጭ መነሻው ከውጭ ሀገር ሆኖ ሀገራችንም ድረስ ሰንሰለቱ ዘልቆ ብዙዎች ከ5ሺህ ብር አንስቶ እየከፈሉ ተቀላቅለዋል። ገዢ ሲያፈላልጉ እኛ አትርፈናል ተጠቃሚ ሆነናል ይሉሃል። ድለላው ወይም ማስማማቱ አጓጊ ጥቅሞን እና በአካል የማይታወቁ የተሳካላቸው ሰዎችን በመጠቆም ነበር። የተሸወዱት ተሸወዱና አሁን ጋብ ቢልም በቅርቡም ይህንኑ የኩዌስት ማርኬቲንግ የሚመስሉ ሰዎች አጋጥመውኛል። ለመሆኑ ይህን አይነት ንግድ ሕጋዊ ተቀባይነት አለው?

ስለአንድ እቃ በማስታወቂያ የሰማኸውና እቃውን የገዛኽበት ዋጋው፣ የእቃው አይነት ደረጃ የተሰራበት ሀገር የተለያየ ሆኖብህ አያውቅም? እቃው በመጋዘን ሞልቶ ከመደርደሪያ ላይ ግን ጠፍቶ የተሰለፍክበትና የተንከራተትክበት፣ እጥፍ ከፍለህ የገዛህበት አጋጣሚስ የሚረሳ ነው? እናስ ሕጉ ስለነዚህ ጉዳዮች ምን ይላል?

 1. ሸማች ማን ነው?

አዋጅ ቁጥር 813/2006 በሰጠው ትርጓሜ መሠረት ራስህም ክፍል ሌላሰው ይክፈልልህ መልሰህ ልትሸጠው ወይም ሌላ ነገር ልታመርትበት ሳይሆን ለራስህ ወይም ለቤተሰብህ ፍጆታ የንግድ ዕቃ ወይም አገልግሎት የምትገዛ የተፈጥሮ ሰው ከሆንክ አንተ ሸማች ነህ። የመንግሥትም ሆነ የግል ድርጅቶች ማህበራት ነጋዴ ሊሆኑ ይችላሉ እንጂ ሸማች አይሆኑም። ምክንያቱም የሕግ ሰውነት እንጂ የተፈጥሮ ሰውነት የላቸውም።

የምትገዛው ነገር ሁሉ ከላይ ያለውን ትርጓሜ ብታሟላም ሸማች ሊያስብልህ ይችላል። የምትገዛው የንግድ እቃ ወይም አገልግሎት መሆን አለበት።

በአዋጁ አንቀፅ 2(1) ገንዘብና የገንዘብ ሰነዶች (የገንዘብ ማስተላለፍ ማዘዋወር፣ ቼክ፣ የተስፋ ሰነድ፣ የቀረጥ ቴምብር፣ በፖስታ ቴምብር የመሳሰሉትን) እንዲሁም የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች (ቤት ይዞታ፣ ህንጻ፣ መኪና፣ ግዙፍ ማሽኖች) መግዛት ሸማች አያሰኝም። ከነዚህ ውጭ የሚገዛ የሚከራይ የመለወጥ የንግድ ስራዎችን የሚከናወንባቸው እቃዎችን ስትገዛ ነው ለሸማችነት የምትበቃው። አገልግሎትን በተመለከተ ደግሞ ደምወዝ ወይም የቀን ሙያተኛ ክፍያ ያልሆነ ገቢ የሚያስገኝ አገልግሎት ምትጠቀም ከሆነ ነው አዋጁ ሸማች የሚልህ። ለምሳሌ አገልግሎቱን ምታገኘው በቀን ወይም በወር ከምትከፍለው ሰራተኛህ ከሆነ አንተ ቀጣሪ እንጂ ሸማች አይደለህም።

 1. ነጋዴስ ማን ነው?

የሚሸጥ ነገር ይዞ የወጣ ሰው ሁሉ ነጋዴ አይደለም። በንግድ ሕጋችን አንቀጽ 5 ስር የተዘረዘሩትን የእቃ ወይም የአገልግሎት ንግድ የሙያ ሥራው አድርጎ ጥቅም ለማግኘት የሚሰራ ግለሰብ ወይም ድርጅት ነው። ለምሳሌ ንግድ ፈቃድ የሌላቸው የመንገድ አዟሪዎች፣ በቤተሰብ ደረጃ በእደጥበብ እቃዎን የሚያመርቱ፣ በግብርና በከብት ማርባት፣ በአሳ ማጥመድ ያገኙአቸውን የግብርና ምርቶች ቢሸጡም ነጋዴ አይደሉም። በመሆኑን በሕግ የንግድ ሥራ ተብሎ የሚታወቀው ሥራ ሙያዬ ብሎ ትርፍ ወይም ጥቅም ለማግኘት ተገቢውን የንግድ ፈቃድ አውጥቶ የጅምላ ወይም የችርቻሮ ሽጭ የሚያካሂድ ግለሰብ ወይም ድርጅት ነው። በአዋጁ አንቀጽ 5 መሠረት ነጋዴ የሚባለው።

አዋጅ ቁጥር 813/2006 ጤናማ የንግድ ውድድርን ለማሸነፍ የሚረዱ ድንጋጌዎችንም ያካተተ ቢሆንም የኛ የዛሬው ትኩረታችን የሸማቾች ጥበቃ በመሆኑ ወደዚያው እንለፍ።

 1. ሸማች ምን መብት አለው?

ሸማች የምትባለው ምን ለምን ስትገዛ እንደሆነ አንስተናል። በዚህ ትርጓሜ መሠረት የዕለት ኑሮአችንን ለመግፋት የሚያስፈልጉ ፍጆታዎችን ሸመታ ከምንወጣባቸው የሰፈር ትንንሽ ሱቆች አንስቶ እስከ ትልልቅ የሽያጭና የአገልግሎት መሸጫ ተቋማት ድረስ የምናካሂደው ግዢ መልሰን ለመሸጥ ወይም ለማምረት ካልሆነ እና የምንገዛው ገንዘብና የገንዘብ ሰነድ ወይም የማይንቀሳቀስ ንብረት ካልሆነ ሁላችንም ሸማች ነን። ከዚህ ጋዜጣ አንስቶ ተሳፍረን እስከመጣንበት ታክሲ ሌሎችንም እቃዎችና አገልግሎቶች መሸመት የህወታችን አንዱ ክፍል ነው። በአዋጅ ቁ 813/2006 አንቀጽ 14 ላይ እነኚህ መብቶች ተደንግገውልናል።

4.1.    በቂና ትክክለኛ መረጃ፡- ብዙውን ጊዜ ሸመታ ስንፈፅም ጊዜ የሚፈጅብን መግዛት ስለፈለግነው እቃ ወይም አገልግሎት የምንፈልገውን መረጃ የማግኘት ጉዳይ ነው። አንዳንዴ የሽያጭ ሰራተኛውም በቂ እውቀት የለውም፣ እያለውም ደግሞ ለመግለፅ ፈቃደኛ የማይሆንበት ሁኔታ ያጋጥማል። ለምሳሌ አንድ የታሸገ ምግብ አንስተው እስቲ የመጠቀሚያ ቀኑ ያለፈበት እንዳይሆን እይልኝ? ቢሉት። አይተው መግዛት የእርሶ ፈንታ ነው። አንድ ወር ነው ያለፈው ችግር የለውም ይልዎታል። ወይም ቀን የለውም ይሎታል ወይም ያለፈበትን አላለፈበትም ሊልም ይችላል። ይህ እንዳይሆን ማንኛውም ሸማች ስለሚገዛው እቃ ወይም አገልግሎት ጥራትና አይነት በቂ ብቻ ሳይሆን ትክክለኛ መረጃ ወይም መግለጫ የማግኘት መብቱ ተጠብቆለታል ግዴታው ደግሞ የሻጩ ነው።

4.2.    የማማረጥ መብት፡- አንዳንድ ነጋዴዎች አንተ እቃ ወይም አገልግሎታቸውን ባማረጥክ ቁጥር ፊታቸውን ይከሰክሳሉ። እስቲ ያኛውን አሳየኝ ለማለት ትሳቀቃለህ። ብሎም እነሱ ጥሩ ነው ብለው ከሰጡህ ውጭ ስታማርጥ ያመናጭቁሃል እና ቢያዩህም የምትገዛ አይመስልም ብለው ይዘልፉሃል። ከንግዲህ ግን እንዳትሳቀቅ በአዋጁ አንቀጽ 14(2)እቃዎችን እና አገልግሎቶችን አማርጠህ የመግዛት መብትህ ተጠብቋል።

4.3.    ለመግዛት አለመገደድ፡- ልትገዛ ያሰብከውን ዕቃ ወይም አገልግሎት አይነቱንና ጥራቱን ትክክለኛ መረጃ የማግኘት መብትህን ተጠቅመህ አማራጮችህን በማየትህ ወይም የዋጋ ድርድር በማድረግህ ለመግዛት መገደድ የለብህም ይሉኝታ እንዳይዝህ ይሄን ሁሉ እቃ አስጎልጉዬው አድክሜው ዝም ብዬ ስሄድ ሰውስ ምን ይላል አትበል። ከመስፈርትህ ከሌለህ አንፃር የልብህን አግኝተህ መግዛት ከፈለክ ብቻ ነው መግዛት ያለብህ። በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ጫናዎች ከደላላም ሆነ በነጋዴው እንድትገዛ ያለመገደድ መብት አለህ። መርጠህ አይተህ ተደራድረህም ካልተስማማህ መተው መብትህ ነው።

4.4.    በአግባቡ የመስተናገድ መብት፡- እንደሸማችነትህ ማንኛውም ነጋዴ በትህትናና በአክብሮት የሚያስተናግድህ እንድትገዛው ወይም ደምበኛ እንድትሆነው ብሎ ሳይሆን የሕግ ግዴታ በአዋጁ አንቀፅ 14(4) ስለተጣለበት ነው። ነጋዴውም ሆነ እሱ የቀጠረው ሰራተኛ የስድብ፣ የዛቻ፣ የማስፈራራትና የስም መጥፋት ተግባር ሸማቹ ላይ እንዳይፈፀም ህጉ ጥበቃ ሰጥቷል።

4.5.    የመካስ መብት፡- ሸማች ነህና በገዛኸው ዕቃ ወይም አገልግሎት ወይም አንተ በገዛኸው እቃ ወይም አገልግሎት የሚጠቀም ሰው ቢያንስ ያሰበውን ያህል መጠቀሙ ባይሆንለት መጎዳት የለበትም። ሆኖም ሸማቹ ላይ ወይም ተጠቃሚው ላይ ጉዳት ከደረሰ በአዋጁ አንቀፅ 14(5) ለደረሰበት ጉዳት ካሳ መጠየቅ መብቱ ተጠብቋል። ሸማቹ ወይም ተጠቃሚው ካሳውን የሚጠይቀው እቃውን ወይም አገልግሎቱን ከሸጠለት ወይ ካቀረበለት ሰው አንስቶ በአምራችነት፣ በአስመጪነት፣ በጅምላ ሻጭነት፣ በችርቻሮ ሻጭነት ወይም በሌላ በማናቸውም ሁኔታ በአቅርቦቱ የተሳተፉትን ሰዎች ሁሉ አንደኛቸውን፣ የተወሰኑትን ወይም ሁሉንም ካሳ እንዲከፍሉትና ተያያዥ መብቶችን በጉዳቱ ምክንያት የወጣ ወጪ የታጣ ጥቅም የመሳሰሉትን እንዲተኩ የመጠየቅ መብት አለው።

 1. የነጋዴው ግዴታዎች

ሸማቾች ከላይ የዘረዘርናቸው መብቶች ተጠብቀውልናል። መብት ካለ ያን መብት ለማስጠበቅ መብቱን የሚጥሰው ወገን ላይ ግዴታዎች ይኖራሉ። እነኚህ በአዋጅ ቁጥር 813/2006 ከሸማቾች ጥበቃ ጋር በተያያዘ ነጋዴዎች ላይ የተጣሉ ግዴታዎች ናቸው።፡

5.1.    የዋጋ ዝርዝር፡- በአዋጅ አንቀፅ 15 ላይ ማንኛውም ነጋዴ የዕቃዎችንና የአገልግሎታቹን የዋጋ ዝርዝር በንግድ ቤቱ በግልጽ በሚታይ ቦታ ወይም በእቃዎቹ ላይ መለጠፍ አለበት። ይሄ እቃ ስንት ነው? የሚል ጭንቀት ሸማቹ ላይ መኖር የለበትም። በተጨማሪም የተለጠፈው ዋጋ ታክሲና ሌሎች ሕጋዊ ክፍያዎችን ያካተተ መሆን አለበት። ይህን ሕጉ የደነገገው አንዳንድ ነጋዴዎች ገበያ ለመሳብ ዋጋውን ግብር ሳያካትቱ ስለሚገልፁ ነው። ለምሳሌ 100 ብር የተባለውን እቃ ገዝተህ ሂሳብ ልትከፍል ስትል 115 ብር ይሉሃል። ምነው ስትል ቫት አንዳንድ የአገልግሎት የፌስታል የማስጠቅለያ ምናምን እያለ ዋጋ ይቆልላል። ስለዚህ ሸማቹ አጠቃላይ የሚከፍለውን ዋጋ አስቀድሞ አውቆ የመወሰን መብት ስላለው ነጋዴውም ዋጋውን የመግለፅ ግዴታ ተጥሎበታል።

5.2.    የሚሸጠው ዕቃ መግለጫ፡- ከአዋጁ አንቀፅ 16 ላይ ነጋዴው እንደ አግባቡ ዕቃውን ለመግዛት ለመወሰን አስፈላጊ የሚሆኑ ዝርዝር መረጃዎችን የንግድ እቃው ላይ መለጠፍ ወይም ለሸማቹ በወረቀት መስጠት አለበት። ከዕቃው ስም አንስቶ የተሰራበት ሀገር፣ ጠቅለላ እና የተጣራ ክብደት መጠንና ብዛት፣ ጥራቱንና ከምን እንደተሰራ የሚያሳዩት የእቃው መሰረታዊ መረጃዎችን ከሚዘረዝሩት መግለጫዎች ናቸው።

አጠቃቀሙን በተመለከተ ደግሞ የቴክኒክ ዝርዝሮች፣ የአሰራር ወይም የአጠቃቀም ዘዴዎች፣ አጠቃቀም ላይ ሊወሰዱ የሚገባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች የተመረተበትን ቀንና አገልግሎቱ የሚያበቃበትን ጊዜ የሚመለከቱ መረጃዎችንም ነጋዴው እቃው ላይ መለጠፍ ወይም በወረቀት ለሸማቹ መስጠት አለበት።

አስተማማኝነትንና ጥራትን በተመለከተ ደግሞ ነጋዴው ስለንግድ እቃው ጥራትና አገልግሎት የሚለው ዋስትና እስከመቼ እንደሚቆይና የዋስትናውን ሁኔታዎች መግለፅ አለበት። ሸማቹ ስለዕቃው የሚፈልገውን መረጃ ማግኘት ወይም በኃላፊነት መጠየቅ እንዲችል የአምራቹን፣ የአሻጊውን እና የአስመጪውን ስምና አድራሻም በእቃው ዝርዝር መግለጫው መካተት አለበት። አስተማማኝነቱን እና የተቀመጠውን ሀገራዊ ደረጃ የሚያሟላ የተመለከቱትን መስፈርቶች ማሟላቱን እና ለህብረተሰብ ጥቅም ሲባል በንግድ ሚኒስቴር በሚወጣ የህዝብ ማስታወቂያዎች ላይ የሚጠቀሱ ዝርዝሮችንም የዕቃው መግለጫ ማካተት አለበት።

የዕቃው መግለጫ እቃውን የሚገልፅ መሆኑን ለማረጋገጥ በእቃው ላይ የሚለጠፍ ከሆነ በራሱ በእቃው ላይ ወይም በመያዣው ላይ መለጠፍ አለበት። በወረቀት ለሸማቹ የሚሰጥ ወይም የሚታተም ከሆነ ደግሞ ቢያንስ በአማርኛ ወይም በእንግሊዝኛ ቋንቋ መፃፍ እንዳለበት በአንቀጽ 16(3) ላይ ተደንግጓል።

5.3.    ደረሰኝ መስጠት፡- ደረሰኝ ሸማቹ በገዛው ዕቃ ወይም አገልግሎት ላይ የሚያነሳቸውን የመብት ጥያቄዎች ለማስረዳት እና ለሌሎችም ጉዳዮች ትልቅ ጠቀሜታ አለው። በመሆኑም በአዋጅ አንቀፅ 17 ላይ ነጋዴው ደረሰኝ ወዲያውኑ የመስጠት ግዴታ ተጥሎበታል። የደረሰኞቹን ቀሪ ኮፒዎች ወይም መልሶ ለመሸጥ ለገዛቸው የንግድ እቃዎች ወይም አገልግሎቶች ለማስረጃ ይሆኑ ዘንድ ለ10 ዓመታት ይዞ የማቆየት ግዴታ አለበት።

5.4.    ራስን መግለፅ፡- ሸማቹ ከነጋዴው ጋር ያለው ጉዳይ እቃውን ከመግዛትና ገንዘብ በመክፈል ብቻ አያበቃም። በመሆኑም ለማንኛውም ጉዳይ ተመልሶ እንዲገኝ ወይም ማንነቱ በማያደናግር መልኩ በቀላሉ እንዲለይ በአዋጅ አንቀጽ 18(1) መሠረት የንግድ ስሙን በግልፅ በሚታይ ቦታ የመለጠፍ ግዴታ አለበት። ሸማቹ ከሚሸጠው እቃ ወይም አገልግሎት ጋር በተያያዘ ጥያቄ ሲያቀርብም ነጋዴው በአጥጋቢ ሁኔታ እራሱን ስሙን አድራሻውን የሚሸጠውን እቃ ወይም አገልግሎትና ሌሎችም ሸማቹ የሚፈልገውን መረጃ እንዲወስድ መፍቀድ እንዳለበትም ተደንግጓል።

    ለመሆኑ የንግድ ማስታወቂያስ የእቃዎቹ ስርጭት እንዲሁም ከሸማቹ ጥበቃ አንጻር የተከለከሉ ሌሎች ድርጅቶችና ሕጉን አለማክበር የሚያስከትለው ኃላፊነት ምንይመስላል የሚለው ለሳምንት ይደርልን። መልካም ሸመታ!

ይምረጡ
(5 ሰዎች መርጠዋል)
7978 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

 • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

 • Aaddvrrt5.jpg
 • adverts4.jpg
 • Advertt1.jpg
 • Advertt2.jpg
 • Advrrtt.jpg
 • Advverttt.jpg
 • Advvrt1.jpg
 • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 845 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us