ፕሮፌሰር እንድሪያስ ስለጠበቆች

Wednesday, 11 February 2015 12:41

ከኪዳኔ መካሻ

This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

 

 

ታዋቂው ምሁር ፕሮፌሰር እንድሪያስ እሸቴ በተለያዩ የውጭ ሀገር ዩኒቨርስቲዎች በማስተማር የተለያዩ የፍልስፍና የጥናት ጽሁፎችን በመፃፍ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህርና የዩኒቨርስቲው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሆነው አገልግለዋል። በአሁኑ ጊዜም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ አማካሪ ሆነው እያገለገሉ ያሉ ምሁር ናቸው።

እ.ኤ.አ. በ1484 “The Good Lawyer, lawyers Rodes & Lawyers Ethics” በታተመው ቅጽ 3 የፍልስፍና እና የህግ የጥናት መጽሔት ላይ “Does a lawyers Character matter” የሚል ጹሁፋቸውን ከፍል አንድን ወደ አማርኛ መልሼዋለሁ።

- ጠበቆች አንዳንድ ጊዜ ለባህሪያቸው በቀላሉ የማይጨበጥ የሚመስል ምክንያት በማቅረብ ራሳቸውን የማይመኙት ሁኔታ ላይ ያገኙታል። ሙያዊ ስራቸውን ሲያካሂዱ ከምግባር (ዋለል) አንፃር አጠያያቂ በሆነ መልኩ እንድንሰራ ይጠበቅብናል ይላሉ። በምሳሌነት ጥፋት መስራቱን እያወቁ ደንበኛቸው እንዳይጋለጥ በንቃት መጠበቅን ይጠቅሳሉ። ይህንም በማድረጋቸው ከምግባር አንፃር ጠቃሚ ግብን እንደሚያሳኩና ይህን ግብ የሚያሳኩበት ሌላ የተሻለ መንገድ እንደሌለም ያነሳሉ። ይህ አባባላቸው ግን አመኔታ የሚጣልበት አይመስልም። ምክንያቱም እንደተነገረን አንዳንድ ጊዜ በዚህ ሙያ ውስጥ ጥሩ ነገር የሚገኘው በመጥፎ ሁኔታ በመስራት ብቻ ነው።

በቅድሚያ ጠበቆች እንዴት መልካም ምግባርን ሊደረድር የሚያቀርብ ሁኔታ ውስጥ እንደሚወድቁ ላሳይ። በተለይም ጠበቆች እንዲያደርጉ የሚጠየቋቸው የተወሰኑ ነገሮች፣ ለስራ ዝግጁ የሚያደርጋቸው ስልጠና፣ ሙያዊ ስራቸውን የሚመሩበት እሳቤ እና በተወሰኑ የሕግ ስራዎች ውስጥ የሚያጋጥሟቸው ችግሮች ናቸው ወደዚህ አጠራጣሪ ባህሪ ውስጥ ስበው የሚከቷቸው በመቀጠልም እነኚህን ጠበቆችን ከምግባር አንፃር የሚያስጠረጥራቸውን ግፊቶች ብናውቅም ሙያው ላይ ያለብንን ጭንቀቶች ሙሉ በሙሉ የሚያስወግድ አለመሆናቸውን እጠቁማለሁ። በመጨረሻም ጠበቆች በአፀያፊ ስራዎች ውስጥ የሚሳተፉበት አሳማኝ ምክንያት አለመኖሩን በቀላሉ የሚያሳዩ ሕጋዊ ሁኔታዎችን አስቀምጣለሁ። እዚህ ጋር ጠበቆች በሌላ የህዝቡ ህይወት ውስጥ የሚነሱ ነጥቦችንና ምላሻቸው የተለያዩ የባህሪ ልቀቶችን የሚጠይቁ ነገሮች በቀጥታ ይገጥሟቸዋል። ጠበቆች ከዚህ ማእቀፍ ጋር በተጣጣሙ ፅንሰሃሳቦች የሚመሩ ቢሆን ኖሮ አሁን ስራቸው ላይ እያስተናገዷቸው ያሉ በርካታ አደጋዎችንም ማስወገድ በቻሉ ነበር።

የጠበቆችን ስራ ለመረዳት በሌሎች ሙያዊና ከፍተኛ ኃላፊነትን እንዲሁም በቀጥታ ለግለሰቦች አገልግሎት መስጠትን ባካተቱ ሥራዎች ውስጥ የማይታዩ ጥቂት በግልጽ የሚታዩ የጠበቆችን የሥራ ገፅታዎች ማወቁ ጠቃሚ ነው። አንደኛው ምክንያት ጠበቆች የሚያገለግሉት አካል ጥቅም ወይም ፍላጎት ሁልጊዜም መልካም አለመሆኑ ነው (እንደሚመስለኝ ይህ ከዴቪድ ሂዩም የፍትህ የተወሰኑ ስራዎች ሁልጊዜም መልካም አይደለችም ከሚለው እሳቤው ጋር የሚያያዝ ነው) ከዚህ አንጻር የጠበቆች ሚና ከመነሻውም አጠራጣሪ ነው። የህክምና ዶክተሮች ሚና ግን አጠራጣሪ አይባልም። ምክንያቱም በአጠቃላይ ሀኪሙ ሙያውን ከህክምና ውጭ ላሉ አላማዎች ካላዋለው በስተቀር የሚያስጠብቀው ጥቅም መልካምነቱ የማያጠያይቅ ነው። ይህ በህክምና ዶክተሮችና በጠበቆች ሚና መሀል ያለው ልዩነት ብዙውን ጊዜ ጠበቆች የሚያስጠብቁት የደንበኛቸውን ሕጋዊ መብቶች እንደሆነ አድርጎ በማስቀመጥ ይደበቃል። ሆኖም ጠበቆች የሚያስጠብቁት ጥቅም ጭራሹንም ሕጋዊ ላይሆንም ይችላል። በተጨማሪ ፍትሃዊ ባልሆነ የሕግ ስርዓት አንድ ስሙ ለሕጋዊ መብቶቹ ከሞራል (ምግባር) አንጻር ላይገቡት ይችላሉ። በትክክለኛው የፍትህ ስርዓትም ውስጥ ቢሆን አንዳንዴ ሕጋዊ መብትን መተግበር ጥፋት ሊሆን ይችላል።

ሌላኛው የጠበቆች ሥራ ከዶክተሮች ሥራ የሚለይበት አይነተኛ ምክንያት ጠበቃው የሚቆምለት የደንበኛው ፍላጎት በሌሎች ፍላጎት ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ የሚያሳርፍ መሆኑ ነው። ጠበቃው የደንበኛውን ጥቅም በደምብ ማስጠበቅ የሚችለው የሌሎችን ጥቅም በመዝጋት ወይም በማሸነፍ መሆኑ በተደጋጋሚ የሚታይ ነው። አንድ ዶክተር ግን እየሰራ ያለው የከፋ የህክምና አገልግሎት ኢ ፍትሃዊ ስርጭት ባለበት ማህበረሰብ ውስጥ ወይም እንደ ጦርነት፣ ድርቅ እና የመሬት ርደት ካለ የአስቸኳይ ጊዜ የአደጋ ሁኔታ ውስጥ ካልሆነ በስተቀር ለታካሚው የሌሎች ህመምተኞችን ሁኔታ ሳያባብስ ሙያዊ አገልግሎቱን መስጠት ይችላል። በመሆኑም ጠበቆች እንዲያገለግሉት የሚጠየቁት ፍላጎት አይነትና አገልግሎቱን የሚሰጡበት መንገዶች አይነተኛ ባህሪ ስህተት ለመስራት ተጋላጭ አድርጓቸዋል።

መደበኛው የሕግ ትምህርትም ጠበቆችን ለሙያው ሞራላዊ አደጋዎች የሚያዘጋጅ አይደለም። ይዘቱን ትተነው የሕግ ስልጠና ዋነኛው አላማ ተማሪውን ብቁ ተሟጋች እንዲሆን ማስቻል ነው። የሕግ ትምህርት የሙግትን ክህሎችን አመለካከት ማሳደጉን በሕግ ትምህርቤት የትምህርት ስርዓት የሚሰጡ ብዙዎቹን የትምህርት አይነቶች በመጫን የሚረጋገጥም አይደለም። ሕጎችን ወይም የከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔዎችን መተንተን ሙያዊ የሆነው የሙግትን ጥበብን የማዳበርን አላማ አንቀሳቃሽነቱ በግልጽ የሚታይ አይደለም። ከምጣኔ ሀብታዊና ከታሪካዊ እይታ አንጻር መዋቅራቸውንና የሕግ ድንጋጌዎን የመነሻ ምክንያት ስንፈትሽ ሕግ በአመዛኙ የሚቆጠረው እንደሌሎቹ የኢኮኖሚያዊ የትምህርት ዘርፎች ነው። ይሁን እንጂ በዚህ አካዳሚያዊ ገፅታውም ቢሆን የሕግ ትምህርት የተለመዱ የምሁራዊ ጥናት አላማዎችን አያገለግልም። ተማሪዎችም ሕግን እንደ አካዳሚያዊ የትምህርት መስክ የሚተረጉሙ ስነስርዓቶችን እና ባህሎችን እንዲካኑ አይበረታቱም ወይም አይጠበቅባቸውም። ከዚህ ጋር በተያያዘ የሕግ መምህራንም ተማሪቻቸውን የወደፊቱ የሕግ መምህር ወይም ምሁር አድርገው አይመለከቷቸውም። በሕግ ትምህርት ውስጥ የንድፈ ሃሳብም ሆነ የተግባር ስልጠናዎች ዋነኛ አላማም ተማሪውን በአይነቱ ለየት ላለው ለሙግት (ለክርክር) ሚና ማዘጋጀት ነው። እውቀቱም ጠቀሜታው የተዋጣለት ተሟጋች የሚጠበቅበትን ማሟላት እስከቻለ ድረስ ሲሆን ከሁሉም በላይ ደግሞ ከየትኛውም ተከራካሪ ጎን ቆሞ ጉዳዩን አሳማኝ አድርጎ ለማቅረብ ነው። ይህ አይነት የትምህርት ብልሀት ማሟላት የማይጠይቀው ነገር ቢኖር ትክክለኛው ነገር ምንድን ነው የሚለውን ለመወሰን የሚያስችል የዳበረ አቅም አልያም ይህንኑ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የሚያስችል ዝንባሌን ነው። እንደተባለውም ይህ የሞራል ውስጣዊ እይታ በብልጠት መንገዱ በመሀል ገብቶ አላማው ለገሀዳዊው ዓለም ፋይዳ ያለውም ሆነ የሌለውም ቢሆን ያን አላማ ለማሳሳት የሚቻለውን አማራጭ ለመጠቀም የመወሰን ወይም የመጠቀምን አቅምን ይገታዋል።

የጠበቆችን ሥራ እና ትምህርት ሞራላዊ ተጠያቂነቱን የሚያባብሰው ስለሚናቸው ያለው ባላንጣዊ ግንዛቤ ነው። በዚህ ግንዛቤ ውስጥ ጠበቃው የደንበኛውን ጉዳይ በተቻለ መጠን አሳማኝ አድርጎ እንዲያቀርብ ይጠበቅበታል። ይህ ደግሞ በራሱ የደንበኛውን ፍላጎት ሞራላዊ ፋይዳ ምንም ይሁን ምን ያለ ልዩነት ማስተናገድን ስለሚጠይቅ የጠበቃው ለጉዳዩ ያለው ፍላጎት ለደንበኛው ጉዳይ ባለው ግላዊ አመለካከት የተነሳ እንዳይረግብ ወይም እንዳይቀንስ ያደርገዋል። ከምንም በላይ ደግሞ ከሌላኛው ወገን በተቃራኒ የሚሟገተው ጠበቃ የደንበኛውን ፍላጎት ከተቃራኒው ተሟጋች እና ከሶስተኛ ወገኖች ፍላጎት እንዲሁም እንደ ፍትህ ካሉ ህዝባዊ እሴቶች እንዲያስቀድምም ይጠየቃል። የደንበኛውን ፍላጎት ሲያስጠብቅ ሕጋዊ የሆኑ ጥቅሞችንም የመጣስ ኃላፊነትንም እንዲሸከም ሁሉ ይጠየቃል። በአጭሩ ለአንደኛው ወገን የሚሟገተው ጠበቃ በማህበራዊ ግጭቶች ውስጥ የከፋ ሞራላዊ ሁኔታ ላይ ካለው ወገን ጎን ሊቆም እንደሚችል ሳያሳስበው ለአንዱ መወገን አለበት። የጠበቃው የተቃራኒን ተሟጋችነት እሳቤ እንግዲህ የሙያዊ ስራውን አሳዛኝ አደጋዎች ወደ ጠበቃው መልካም ሚናነት ያሸጋግረዋል። በተወሰኑ የህግ ሙያ ስራዎች በተለይም የወንጀል ክስ መከላከል ዙሪያ ያሉት የተከራካሪ ጠበቃውን የሞራል አቋም ፅኑ ፍላጎት የሚያበረታቱ ናቸው። በጥፋተኝነት በፍ/ቤት መወንጀል በጣም ከባድ ጉዳይ ነው። መንግስት የአንድን ሰው ባህሪ መቆጣጠሩ ማንም ሰው በምክንያታዊነት የሚቀበለው አይደለም። የፍርድ ቅጣቱ የሚካሄደው ክፍት በሆነ የህዝብ እይታ ፊት ሲሆን በዚያም ሰፊውን ትኩረት የሚስበው ከግለሰባዊው ጸጸት ወይም ቁጭት ይልቅ የግለሰቡ ውድቀት ነው። በዚህ የተነሳ ከፋ ተፅዕኖው በግለሰቡ ህይወት ሙሉ ማስተጋባቱ አይቀርም። መንግስት ወክሎ ስልጣኑን በሰጣቸው በግላዊ አመለካከትና ከአድሎአዊነት ጫና ውስጥ የማይወድቁ ተደርጎ በሚገመቱት ፈራጆች ግለሰቡ ጥፋተኛ በመባሉ ነው። ፍርዱ ትልቅ ግምት የሚኖረው በጎን በኩል ደግሞ ግላዊ ህይወቱ ላይ ትልቅና ሰፊ ውጤት የሚያመጣ ሆኖ እያለ በተሰጣቸው ስልጣን ፍርዱን የሚያሳርፍበት ፍርዳቸው በግለሰቡ ላይ ስለሚያመጣው ጫና ጥቂት ብቻ የሚያወቁ ወይም ብዙም ግድ የሌላቸው ሰዎች ናቸው።

በወንጀል የተፈረደባቸው ጥፋተኞች የሚያጋጥሟቸውን ቅጣት በተመለከተ እራሳቸው ሰልጥነናል ብለው በሚኩራሩት እንኳን አንድ ያሉአቸው ተከላካዮች ጥቂት ናቸው። ወህኒ የገቡ ታራሚዎች ኢሰብአዊና አዋራጅ ለሆኑ አያያዝ፣ የተሻለ አያያዝ አላቸው በሚባሉት ዘንድ እንኳን ሰለባዎች ናቸው። በአንድ የሆነ ጉዳይ ላይ መንግስት የወሰደው እርምጃ ተገቢ መሆኑን እርግጠኛ ብንሆንም እንኳን በአብዛኛው የማረሚያ ተቋማት የሚካሄደውን አያያዝ ጋር አስተያየትን እንዴት እንደሆነ ለማወቅ አስቸጋሪ ነው። የወንጀል ፍርደኛው የውርደት ስሜት የእስሩን ጊዜ ሲያጠናቅቅ የሚቋረጥ መሆኑንም እንዲሁ ማረጋገጥና ማሳየት አንችልም። ሕጉ የሚያስከፍለውን ዋጋ የከፈሉ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ የሚመርጡትን ስራ በመስራትና በመረጡት መኖሪያ የመኖርን የመሰሉ ነፃነቶቻቸውን መገፈፋቸው ይቀጥላል። በመሆኑም በወንጀል ፍርድ መቀጣት ጥልቅና ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅ ክፉ አሻራን በግለሰቡ ላይ የሚያሳርፍ ነው። ግለሰቡ ደግሞ ንፁህ በሆነበት ወንጀል ከሆነ የተቀጣው የክፉ አሻራው ስቃይ ግዝፈቱ ከስሌት ሁሉ በላይ መሆኑ እርግጥ ነው። መንግስት ወንጀልን በመቆጣጠሩ ስራና በተለይም አጥፊዎችን ከሶ ጥፋተኛ በማስባልና ወንጀለኞችን በመቅጣቱ ላይ ሰፊ ስልጣንና ኃይል አለው። ፖሊስና ሌሎች የመንግስት የምርመራ አካላት ወንጀልን በመመርመርና ምርመራቸውን የሚደግፍ ማስረጃ በማሰባሰብ ትልቅ ስልጣንና ኃይል አላቸው። አንዴ ግለሰቡ በመንግስት መዳፍ ውስጥ ከገባ መንግስት አንዳቸው ሊያደርገው ያለው ስልጣንና ኃይል ገደብ አልባ ነው። ይሁን እንጂ አንድ ተራ ዜጋ የፈለገ አቅሙ ቢኖረው ውጤታማ መንግስት በሕግ ሊጠይቅ ከሚችልበት አስገዳጅ ኃይል ጋር ሊመጣጠን ግን አይችልም።

ከዚህ መሰረታዊ ሃሳብ በተቃራኒ ተከራካሪ ጠበቃ እንዴት ምክንያታዊ ይሁንታ እንደሚኖረው መረዳት ይቻላል። ከወንጀል ፍርድ ጥፋተኝነት አንፃር ሲታይ ጠበቆች ስለደንበኛቸው ፍላጎት ፋይዳ ብዙም መጨነቅ አያስፈልጋቸውም። ምክንያቱም የወንጀል ተከሳሹን ለመከላከል ጠበቃው የግለሰቡ ዋጋ ያላቸው አላማዎች የሆኑትን ነፃ የመሆንና የጭካኔና የሰብአዊነትን አዋራጅ አያያዝ ለማስወገድ እየሰራ መሆኑን ላይ ሊያርፍ ይችላል። የሆነ ሰው ተከሳሹ አላማው መቀጣት ነው በሚል ይህን መከራከሪያ ላይቀበል ይችላል። በተለይም በሀሳባዊያን ማህበራዊ ንድፈ ሃሳቦች ውስጥ አንዳንድ ጊዜ ወንጀል የፈፀመ ግለሰብ የመቀጣት ፍላጎት አለው ወይም የበለጠ ገፋ ተደርጎ ከታየ ለመፀፀት ወይም ለመታረም የመቀጣት መብት አለው የሚሉ መከራከሪያዎች ያነሳሉ። እንግዲህ የወንጀል ጥፋተኛው ንፁህ ከሆነ ይህ ተቃውሟቸው እሱን አይመለከትም። በተጨማሪ ንፁሃን እና አጥፊዎችን ለመለየት የሚያስችል አስተማማኝ የሆነ ዘዴ ባለመኖሩ ጠበቃው የወንጀል ተከሳሾች ጠቃሚና የሚሰመርባቸው እንደ የተለየ ደንበኛ ግን የማይጋራቸው ኢላማዎች ምን መምሰል አለባቸው የሚለውን ለማሳየት የሚሞክር የሆነ መመሪያ ተግባራዊ ሊያደርግ አይችልም። ይህ ሂደት ደግሞ በተለይ የሚታዩ ላይሆንም ይችላል። ምክንያቱም የወንጀል ተከሳሾች ብዙውን ጊዜ ንፁሁ እንኳን ሳይቀር አንዳንዴ “ጥፋቱን አመነ” ለመቀጣት ያለውን ፍላጎት ገለፀ የሚያስብል ጭንቀት ውስጥ ይገባሉ። አጥፊ ተከሳሽ እንኳን ለመፀፀት ያለውን ፍላጎት ቢያሳይና ቃሉን ቢሰጥ ይህ ፍላጎቱ በወንጀል የፍትህ ስርዓቱ በሚደረገው መልኩ መሟላት አለበት የሚያስብልም ግልጽ ያለ ምክንያት የለም። በየትኛው መልኩ ቢሆን ቅጣቶች በጥፋተኞች ላይ የሚጣሉት ተቀበሉት አልተቀበሉት የሚለው ከግምት ውስጥ ሳይገባ ነው። ስለዚህ በወንጀል ክስ መከላከል ውስጥ ጠበቃው የተሻለ ዋጋ የሚሰጠው ምክንያታዊ ማረጋገጫ የሚኖረው። በመሆኑም የወንጀል ተከላካይ ጠበቃ የአንድ ደንበኛው ሞራላዊ ዋጋ ከሚያሳድርበት ጭንቀት በትክክልም ነፃ የመሆን ስሜት የሚሰማው። (ይቀጥላል)።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
6172 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 733 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us