ፕሮፌሰር እንድሪያስ እሸቴ ስለጠበቆች

Wednesday, 18 February 2015 14:04

ክፍል 2

ከኪዳኔ መካሻ

This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

 

ይህ ጽሁፍ ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ በ1984 (እ.ኤ.አ.) በአንድ የፍልስፍና የሕግ የጥናት መፅሐፍ ላይ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያቀረቡት ፅሁፍ የአማርኛ ትርጓሜው ነው። ባለፈው ሳምንት በክፍል አንድ ጠበቆች አጠራጣሪ ባህሪ እንዲኖራቸው የሚያረጉትን ምክንያት አንስተናል። በዛሬው ጽሁፍ

-    ጥብቅና ሙያ በራሱ ላልተገባ ባህሪ ያጋልጣል፣

-    ጥብቅና ትወና ይመሳሰላሉ፤ የጥብቅናው ትወና ግን የከፋ ነው፣

-    ጠበቆች በአሪስቶትል የሞራል ልቀት ማሳያ እንዴት ይታያሉ?

በወንጀል ክስ መካከል ውስጥ የተከራካሪው ጠበቃ የደጋፊነት አቋምም መነሳቱ ተገቢ ነው። በወንጀል ቅጣት ላይ መንግስት ያለው ጠንካራ ፍላጎትና አስፈሪ ስልጣን እያለ የተከላካይ ጠበቃው ድጋፍና ትብብር እንዴት እንደሚያስፈልግ ለማየት አስቸጋሪ ነው። እንደተባለው በወንጀል ቅጣት ላይ መንግስት ያለው አላማ አሳማኝ ባይሆንም ከፍ አድርጎ ለማስቀመጥ ካልሆነ በቀር እንደተባለው ወንጀልን ማጥፋት እና እውነቱን አውጥቶ አጥፊውንና ንፁህና የመለየት ጥያቄውን በመለየቱ ውስጥ የተከላካይ ጠበቃውን የመንግስትን ፍላጎት የደጋፊነት ሚና ተጨባጭ የሚያደርግ የጋራ ነጥብ የለም። የሌላኛው ወገን መልካምነት ብዙውን ጊዜ እንደተከሳሹ መልካምነት በጥድፊያ ስጋት ውስጥ የሚወድቅ አለመሆኑም ይነሳል። እነኚህ ነገሮች ናቸው እንግዲህ ለደንበኛው ፍላጎት ክብደት እንዲሰጠው ያደረጉት።

በአጠቃላይ የጠበቆች የስራ ባህሪ፣ የሕግ ትምህርት ስልጠና እና የወንጀል ክስ መካከል የተለየ ችግሮች ባንድ ላይ ተደምረው የባላንጣነት (የተከራካሪነት) አመለካከትን አጠናክሮታል። በርግጥም እነኚህ አመለካከቶች ተከታታይ ከሆነ የፍርድ ቤት ሙግት በተለዩ ጠበቆች ስራ ውስጥም መምራትና አቅጣጫ ማስያዛቸውን ግን ቀጥለዋል። እንደ ሕግ አማካሪ የሚያገለግሉ ጠበቆች ለምሳሌ ከነሱ ደንበኛን የሚጎዳ የፍርድ ቤት ክርክርን ለማስቀረት ይሞክራሉ ወይም የሌላኛውን ተከራካሪ ጥቅም የሚያሳጣ ከሆነ ደግሞ የፍርድ ቤት ሙግት እንዲካሄድ ያነሳሳሉ።

1. ውጤታማ ጠበቃ ሀቀኛ ሊሆን አይችልም

ከላይ የተነሱትን የጥብቅና ሙያን ባላንጣዊ (አንደኛውን ወገን የመቃወም) ሚና የሚያሲዙትን የተለያዩ ነገሮች መገንዘባችን በሙያው ላይ የሚሰማንን ምግባራዊ (ሞራላዊ) ምቾት ማጣት አያስወግዱትም የዚህን ምቾት ማጣት ምንጭ ጆን ራውል ያስቀመጠው ቀላልና አሳማኝ የምግባር ስነልቦና (ሞራል ሳይኮሎጂ) መላምት ሊያብራራው ይችላል።

“አንድ ግለሰብ ምን መሆን እንዳለበት ወይም ምን አይነት ስራ ወይም ሙያ ውስጥ መግባት እንዳለበት ሲወስን የተለየ አንድ የህይወት እቅድ ተቀብሏል። በዚህ ጊዜ ምርጫው የተወሰነ የፍላጎት ወይም የተነሳሽነት (የተነሳሽነቱ እጥረትም ሊሆን ይችላል) አቅጣጫ እንዲይዝ ያደርገዋል። የዚህ አቅጣጫ አንዳንዶቹ ገፅታዎች የግለሰቡ የተለዩ ነገሮች ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ የተሰማሩበት ስራ ወይም የህይወት አቅጣጫው አይነተኛ መገለጫዎች ናቸው።”

ጠበቃውም የስራውን ግዴታዎች በብቃት ሲያከናውን ተቀባይነት የሌላቸውን ድርጊቶች መፈጸምን፣ የማይስቡ ጠባዮችን መያዝንና አጠራጣሪ ወይም ተአማኒነት የሚጎላቸው  አላማዎችን ማዳበርን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ አይችልም። ለወንጀል ተከሳሹ ቆሞ ውጤታማ ሙግት ማድረግ ከምግባር ትክክለኛነት አንጻር ተቀባይነት የሌላቸውን እርምጃዎች መከተልን ይጠይቃል። ለምሳሌ ተከሳሹ የሚሟገትበት ፋይዳ ያላቸው አላማዎች እንዳሉት ወይም ዐቃቢ ሕጉ በማስረጃ የማረጋገጥ ሸክሙን ባግባቡ አለመወጣቱን ማሳየቱ ብቻ በቂ ላይሆን ይችላል። ስለዚህ ጠበቃው ሆን ብሎ ደንበኛው ሙሉ በሙሉ ከጥፋቱ ንፁህ መሆኑን የሚያሳይ ገፅታ ያቀርባል፤ ምስክርነቱ እውነት መሆን የታወቀውን የተቃራኒውን ወገን ምስክርነት ቃል ማጣጣል ወይም ማሳጣቱን ወሳኝ ሆኖ ሊያገኘው ይችላል ወይም የደምበኛውን ጉዳይ የሚጎዳውን ቀጥተኛ የሚል መረጃ ተቀባይነት እንዲያጣ ማድረጉ የክርክሩ ብልት ሆኖ ያገኘዋል። በዚህ አይነት መሰል ተግባራት ውስጥ ለረጅም ጊዜ መሳተፉ በስብእናው ላይ የራሱን አሻራ ይተዋል። እነኚህ ተግባራቱ የሚወሰዱት ደግሞ ተቀባይነት እንዳላቸውና ማህበራዊ ይሁንታ እንደሚያሰጡ ሙያዊ ጥሪዎች በመሆኑ ከዚህ ተቃራኒ የሆኑ ፀባዮችን ጠብቆ እንዲቆይ የሚያበረታቱት ወይም ከነዚህ ተግባራት ጋር በሚጣጣሙ ፀባዮችን ከማዳበር እንዲቆጠብ የሚያስችሉት ነገሮች ጥቂት ናቸው። ለእውነት፣ ለፍትሃዊነትና ለመልካም ስም እና ለመሳሰሉት ጠበቃው ያለው የፀና አቋምና መሰጠትም ስራውን በጥሩ ሁኔታ የመወጣት አቅሙ እውን እና ተጨባጭ እንዳይሆን ይከለክለዋል። በጥብቅና ስራ የላቁና የተዋጣለት ለመሆን እንደ ጮሌነት ያሉት የጠበኝነት ወይም የጥል ላይ ፀባዮች እጅግ ጠቃሚ ሆነው ይገኛሉ። በዚህ መልክ ከተከራካሪው ጠበቃ የሚጠየቅበት ስራ (አካሄድ) ቀስ በቀስ በባህሪው ላይ የማይፈለጉ ገፅታዎችን ይፈጥራሉ።   

2. ጥብቅና የሚያስከትላቸው ባህሪዎች

ጠበቆች ጠቃሚ ሙያቸውን በዘላቂነት ለማካሄድ በቀጣይነት የሚያዘንብሉባቸው ባህሪያቸው ላይ ሞራላዊ (ህሊናዊ) ጉዳት የሚያስከትሉ ነገሮች አይነታቸውና መጠናቸው የተለያዩ ነው። ያልተገባ አካሄዳቸውን እየቀጠሉ ተቀባይነት ያለውን ገፅታ እንደሽፋን ለመላበስ የሚጠቀሙት የመልካም ባህሪ ስብእና ባለቤቶች የሙያቸው የመጨረሻው ግብ ለእውነትና ለፍትህ ተአማኒ ባለመሆን እንዲሁም በተወሰኑ ግለሰቦች ላይ ፍትሃዊ ስላልሆነ የሚጸጽታቸው መሆኑ አይቀሬ ነው። ከስራቸው የመጨረሻው ፅኑ አላማና ከመልካም ባህሪያቸው ጋር ያላቸውን ቁርኝት እንደተጠበቀ ከሆኑ ከግላዊና ከማህበረሰባዊ ሀሳቦቻቸው ጋር የሚቃረኑ የሚመስሉ የእለት ተእለት ስራዎቻቸውን ተረጋግተው ማካሄድ አይችሉም። እንዲህ አይነት ሰዎች የመረጡትን ህይወት ሙሉ በሙሉ እና ጥሩ በሆነ ሁኔታ እየኖሩት እንደሆነና የዛ ህይወት አካል የሆነውን ውጤት ሊያፈራ አለመቻሉን ከማወቃቸው በሚወለድ ጫና የተነሳ ሊሰቃዩ የሚችሉ ናቸው። ሞራል (የህሊና) ሀቀኝታቸው በቋሚነት ይሰናከልባቸዋል። ሌሎቹ ደግሞ አነስተኛ እራስን የመግዛት አቅም እና ለአይነተኛ ሀሳባዊ ግቦች ጋር የላላ ቁርኝት ያላቸው ሲሆኑ የሙያቸውን የበለጠ ራቅ ያሉ ተቀባይነት ያላቸው አላማዎች የማስተዋል እይታቸውን ለማጣት የተጋለጡ ናቸው። በዚህ ምትክ እንደ ሀብት እና ማህበራዊ ደረጃ ላሉት ማህበረሰቡ ስኬታማ ለሆነ የውጊያ ወይም የባላንጣነት ክህሎታቸው ማህበረሰብ ወደሚሸልማቸው ጊዜያዊ ጥቅሞች ጋር ትስስራቸውን ይለውጣሉ። ሌሎች ጠበቆችም ደግሞ ፋይዳ ቢስ የሆኑ ዝንባሌዎችን ሊይዙ ይችላሉ። ይህም የሚያደርጉት ለጥቅማቸው ሲሉ የብልጠት ጮሌነትን ፣ የሌለውን ሃሳብ በዘዴ መቆጣጠርን እና ሌሎችን የማዋረድን ስራዎች (ድርጊቶች) እውቅና እና ሙገሳ በመስጠት ነው። ለእነሱ የሙያ እርካታ ማለት ሌሎች በነሱ ሀይል ስር ወድቀው ለተመልካቹ መሳለቂያ ሲሆኑ ማየትንም የሚያካትት ነው።

ይህን ስል ተካራካሪ ጠበቃዎች በነዚህ ሶስት ጎራዎች ሙሉ በሙሉ ይከፈላሉ ወይም ይመደባሉ ማለቴ አይደለም። የተቀመጠው ነገር በጅምላና በዋና ዋናነት የተሟጋችነት ሚናን ከመያዝ ሊገኙ የሚችሉ የጠባይ አይነቶችን ለማሳየት ያህል ነው። በዚህም መሰረት አንድ ጠበቃ በሙያው ህይወቱ በእነዚህ የተለያዩ አይነት ባህሪዎች ውስጥ መሻሻል እያሳየ ሊሄድ ወይም በተለያዩ የህይወት ደረጃዎች ውስጥ በእነዚህ የባህሪ አይነቶች ውስጥ ሊመላላስ ይችላል ማለት ነው። ለምሳሌ የመጀመሪያው አይነት ባህሪ የተረጋጋ (ቋሚ) አለመሆኑ ግልፅ ነው። እንዲህ አይነት ጠበቆችን የቁጭት ወይም ራስን የመናቅ ስሜቶች እየተወሰኑ የተሟጋችነት ዝንባሌያቸውን ሊወሩትም ይችላሉ። እነኚህ ስሜቶች ላይ የሙጥኝ ማለቱ ሙሉ በሙሉ ሊያሽመደምዳቸው ስለሚችልም እነሱን ከሚያመነጨው ከሀሳባዊ መነሻቸው በመሸሽ ምላሽ ሊሰጡ ይችላሉ። እንዲህ አይነት ጠበቆችም እራሳቸውን ሙሉ በሙሉ ወደ ባላንጣዊ (ተቃርኖአዊ) ሚና ውስጥ ለማስገባት ሊወሰኑና ህብረታቸውንም ወደ ማህበረሰቡ ማበረታቻዎች ሊያዞሩ ይችላሉ። በሌሎቹ አይነት ባህሪዎች ውስጣዊ ግጭትንም ሆነ እርጋታ ማጣትን ማስወገድ አይችልም። ለምሳሌ በ`halo effect` ወይም ባለፈው የተወሰነ ድርጊት የሰውየውን ድርጊት ወይም ስራ ቀድሞ ማድነቅ) የተነሳ በሁለተኛው አይነት ባህሪ ውስጥ ራስን መሸንገል ሊመጣ ይችላል። ይህ ሀሎ ኢፌክት የሚፈጠረው አንድ ሰው ራሱን በሙያ ወይም በህይወት ውስጥ ቁሳዊ ስኬቶች በሌሎች ለህዝብ ሙገሳና ይሁንታ ብዙም ይፋ ባልሆነውም የህይወት ገፅታ ላይ ስኬት የመኖሩ ምልክት ናቸው ብሎ እራሱን ሲያሳምን ነው። 

 3. ጥብቅና እና ትወና

ለዚህ ጨፍጋጋ የጠበቆች ስራ እንዴት ባህሪው ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳርፍ ለሚያሳይ ምስል የተመሰረተበትን ስነልቦናዊ መላምት በማብጠልጠል የመቃወሚያ ድጋፍ ማግኘት ይቻላል። ለዚህም ውጤታማ የሆነ ተሟጋች ጠበቃ አስቀያሚ በሆኑ አስራሮች ውስጥ መሳተፍ እንዳለበት እንዲሁ በቀላሉ የሚቀበል ሰው የሙያዊ ስራቸው ግላዊ አመለካከትና ውስጣዊ ፍላጎታቸውን ይቀርፀዋል የሚለውን አባባል ላይስማማበት ይችላል። አንዴ ጠበቆች ከሕጉ ምህዋር ከመጡ ወደ ተራ ግላዊ ባህሪያቸው ይመለሳሉ የሚል አስተያየትም ሊሰጥ ይችላል። ከቤተሰባቸውና ከጓደኞቻቸው ጋር ሲሆኑ በስራቸው ላይ ያደረጉትን ነገር የሚያዩት እኛ በምናይበት መንገድ ነው። በአጭሩ ባሪያቸውን ከሙያዊ ስራቸው የተለዩ ነው ሊባልም ይችላል። እንዲህ ከሆነ ይህን ከፍሎ መለያ የሚቻል ለማድረግ ጠበቆች ስለስራቸው እንግዳ የሆነ አመለካከት ሊኖራቸው ይገባል። በሙያቸው የሚሰሩትን ስራም እንደ ትወና አይነት አርገው መመልከት አለባቸው። ደግሞም ጠበቆችን የተዋናዮች ምስል ለራሳቸው እንዲሰጡ የሚያደርግ የስራ ገፅታም አላቸው። ውጤታማ የሆነ የሙግት ውክልና ራስን ከደንበኛው ማንነትና ሁኔታ ጋር አንድ አርጎ ማቅረብን ይጠይቃል። የፍርድ ወንበር ላይ የተቀመጡትን ዳኞች ርህራሄ ለማግኘት በምናባቸው እንደቀረፁት ማንነት ሆኖ መቅረቡ ለጠበቃው አስፈላጊ ሊሆንበትም ይችላል። የትወናው ክፍሎች የጠበቃውን የመውጋትና የማሳመን ክህሎት በዘዴያዊ አቀራረብ የማሳያ እውነታ የሚገልፁ ሲሆን የብልጠት ጮሌነትን እና በተቋማዊ እሳቤ የያዘውንና በይፋ የሚካሄደውን ያልሆነውን እንደሆነ አድርጎ ማቅረብንም የሚያጠቃልሉ ናቸው።

ማስመሰል በሙግት ውስጥ የሚኖረው ቦታ እንዳለ ሆኖ ይህ የፈጠራቸውን ጠበቃው እንደ ተዋናይ አድርጎ ማሰብ እና በግላዊ ፀባይና በሙያዊ ስራ መሀል ልዩነት መፈጠሩን የሚያሳምኑ ነገሮች አያደርጋቸውም ቴአትር በስሜታችንና በእምነታችን ላይ ጥልቅና ብዙ ጊዜ የሚቆይ ተፅዕኖ ማሳደሩ እውነት ነው። በሆነ ተውኔት ውስጥ አንዳንዶቹ ገፀ ባህሪያት ከሌሎቹ ሲገፋቸው እኛ ደግሞ እርህራሄና ስሜታቸውን የመጋራት ይሰማናል። ገጸባህሪያቱ ግጭት ውስጥ ካሉ እራሳችንን ለአንደኛቸው ወግነን ልናገኘውም እንችላለን። እንዲህም ሆኖ ግን ሁነኛ የሆነ ከመድረኩ ትወና ጋር የሚለየን ክፍተት አለ። እሱም የገፀባህሪውን እጣ ፈንታ ሊለውጥ የሚችል የምንወስደው እርምጃ ወይም የምንወስነው ውሳኔ አለመኖሩ ነው። እንግዲህ እዚህ ወሳኝ ገጽታ ላይ ነው የጠበቆች የውክልና ገፅታ ከተዋናዮች ውክልና የሚለየው። ደንበኛቸው ህያው ሆኖ እንዲታይ ወይም ምስክሩ ዋሾ መስሎ እንዲታይ ጠበቆች የሚያደርጉት ጥረት የግለሰብ ህይወት ላይ ተፅዕኖ የሚያሳርፍ ፍርድ ለማግኘት የሚደረግ ነው። በዚህ የስራቸው ተግባራዊ ውጤት አንፃር ሲታይ ስራ ጠበቆች ከላይ የሚያነሳው ነጥብ የሚይመስል ነገር በመሆኑ ይፋዊ ቃላቸው እና ስራቸው ከሚናቸው ጋር አብሮ ሊያያዝ የሚችልበት መንገድ የለም። ተሟጋችን መርታት የሙያ ስራንና ግላዊ ባህሪ መለየቱ ራስን ለመሸንገል የሚያመቻች ከሆነ ጠበቃው የያዘው እምነትና በስራው ውስጥ የሚወስዳቸው እርምጃዎች የሙያዊ ሚናው አካል መሆናቸውን ራሱን እንኳን ማሳመን አይችልም። ምክንያቱም የራስን ባሪ ከስራ ፀባይ መለያው ድንበር በምን እንደተደገፈ እንኳን ማስረዳቱ አስቸጋሪ በመሆኑ ነው።

4. የጠበቆች የሞራል ደረጃ

ሌላኛው የጠበቃ ስራ ባሪውን ያዘቅጠዋል ለሚለው አባባል የሚሰጠው የመልስ ምት ትንሽ ለየት ያለ ነው። የኒቾማችያን አቴክስ 3ኛ መፅሐፍ ውስጥ ወኔ (ድፍረት) አንደኛው ጉዳይ ሲሆን አሪስቶትል ምሉእ (የሞራል ልቀት) መልካምነት ባለው ሰው ውስጥ ወኔ (ድፍረት) እንዴት እንደሚገለፅ ሲናገር “በጣም ምርጥ ወታደሮች የመሰሎቻቸው አይነት ሰዎች ሙሉ በሙሉ የላቀ መልካም ሞራል ላይኖራቸው ይችላሉ። ሆኖም ያነሰ ደግነትና ሌላ ጥሩ ነገር የሌላቸው ግን ሙሉ መልካም ሞራል ሊኖራቸው ይችላል።  ምክንያቱም ጥሩ ወታደሮች ለማይረባ ጥቅም ሲሉ አደጋ ለመጋፈጥና ህይወታቸውን አሳልፈው ለመሸጥ የተዘጋጁ ናቸው” ብሏል። እንዴት ምርጥ ወታደሮች ሙሉ የሆነ ብቃት (ልቀት) እንደሚያንሳቸው መግለፁ አስፈላጊ ነው። አሪስቶትል ይህን የሚለው ለዘመናዊው የተወሰኑ ድርጊቶች ክፍት ወይም ጭካኔ ያስፈልጋቸዋል ለሚለው እይታ ባለመሆኑ ለጥሩ ወታደሮች ክፍተት አላላበሳቸውም። አልያም ምርጥ ወታደሮች መልካምነት ያጥራቸዋል የሚል ሀሳብም አልሰጠም። ይልቁንስ ወደ ወረዱ ፍላጎታቸውና መሻታቸው አልወረዱም፣ በተሸመደመደ ፍቃዳቸው ትክክለኛ ነው ብለው ከወሰኑት ነገር ላይ ፊታቸውን አላዞሩም፣ ውዱንና ተገቢውን ለዘቀጠ ፍላጎትና ስሜታቸውን ተላልፎ በመስጠት ብቻ ለማግኘት አልመረጡም። እንዲህ ያለው የመልካምነት ፍላጎት የሌላቸው መካከለኛ መልካምነት ያላቸው ከገብጋባነት ውጭ የሚሆኑበት ቁርጠኝነት የላቸውም። ስህተት የሆነው ስለግባቸው የደረሱበት ውሳኔ በመሆኑ በዚህ ህፀፅ ላይ በመመስረት ነው እኚህ የላቀ ተግባራዊ ውሳኔን ከሚጠይቁ ተግባራት ይልቅ ለተወሰኑ ስራዎች ነው የሚስማሙት ሲል የደመደመው። የተለሳለሰ የሞራል ብቃት (መልካምነት) ያላቸው ሰዎች ለምርጥ ወታደራዊነት ተስማሚ ናቸው የሚለው የአሪስቶትል እሳቤ ምክንያቱ ከፍተኛ የሞራል እይታ ያላቸው ሰዎች በፅኑ ፍላጎት ለሰውነት የማይችሉትን ግብ መካከለኛ ሞራል ያላቸው ማንገቡ ላይ ብቻ በማተኮር ሊተጉበት ስለሚችሉ ነው። ይህ እሳቤው ያልተለመደ በሆነው የስነልቦናዊ ውስጣዊ እይታ ላይ ያረፈ ይመስላል። እሱም እይታው ከላይ ያላቸው ፀሐይ ላይ ካተኮረ በፕላቶ ዋሻ ውስጥ እምድር ላይ ታስሮ ያለ ሰው ከፊቱ ውልብ በሚሉ ጥላዎች መማለሉ የማይመስል ነገር ነው የሚለው አባባል ነው።

የአሪስቶትልን የጥሩ ወታደር ማሳያ ካየን በይበልጥ የሚስበውን የጠበቃን ምስል ማበጀት እንችላለን። በክርክር ሂደት ውስጥ የሚያስማሙ ድርጊቶችን በማድረጋቸው ጠበቆች ሊወርዱ ፍላጎቶቻቸውና መሻቶቻቸው እጅ እየሰጡ አይደለም። ወይም ደግሞ ከትክክለኛ ምርጫና ድርጊት የተነጠሉት ሂደቱ በተወሰነ መልኩ የፍቃዳቸውን ጥንካሬ ነጥቆአቸውም አይደለም። በአሪስቶትል ትንተና መሰረት የሙግቱ ሂደት ጠበቆች እይታቸውን ዝቅ እንዲያደረጉ ስለሚያስገድዳቸው ነው። ከሂደቱ ጋር በመጣበቃቸው ጠበቆች ከፍትህ ከፍ ያሉ አላማዎች እይታቸውን በማንሳት የተፈለገው ውሳኔ ጥሩ ህግ የሚያስገኝ ይሁን አልያም ክፉዎች የሚገባቸውን ቅጣት መቀበላቸው የሚያረጋግጥ የማየት ፍላጎታቸውን ማሸነፍ ወይም ተቃራኒው ወገን የመሸነፍ የተናነሰ ጥሩ መጨረሻ የማይማርኩና የማይስቡ አላማዎች መካከለኛ ሙያዊ ጥሪ ያለውን ሰው ፅኑ ፍላጎት ግን ይስባሉ። ጠበቆች ትኩረታቸውን ሙሉ በሙሉ ለሰጡበት መሃል ላይ ላለ ሙያቸውም ይቅርታ መጠየቅ አያሻቸውም። (ይቀጥላል)

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
6346 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 924 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us