ሕግ የማያውቃቸው ደላሎች

Wednesday, 25 March 2015 11:32

ከኪዳኔ መካሻ

This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. '; document.write(''); document.write(addy_text85284); document.write('<\/a>'); //-->\n This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.


-    በተለያዩ ቤት መኪና የሚያከራዩና የሚያሻሽጡ ደላሎች ስራና በሕጋችን የተቀመጠ ድንጋጌዎች

-    ደላሎች በሕግ የሥራ ፈቃድ፣ የገቢ ግብር እንዲሁም በስራቸው ለሚያደርሱት ጉዳት ያለባቸው ኃላፊነት ምን ይመስላል?

-    በሕግ ተገቢው ቁጥጥር ከሚደረግባቸው የድለላ ስራዎች መካከል ስለመድህን ድለላን ሕጉ ምን ይላል

እንዴት ናችሁ ሰላም ነው? ዛሬ የድለላ ሥራን እና ኃላፊነትን የሚመለከቱ ሕጎቻችንን እናነሳለን።

 1. ድለላ በተግባር፡- በመጨረሻ ጊዜ የተደለላችሁበትን ቀን አስቡት። ደላላው እንዴት ነበር? በደላላው በኩል የገዛችሁት የሸጣችሁት ነገር ተመቻችሁ ዋጋው የዕቃው ወይም የአገልግሎቱ ጥራት እንደተባለው አገኛችሁት? ለደላላውስ ስንት ከፈላችሁ?

አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ደላላ የሚለውን ቃል “በቁሙ መደለል ማታለል መሸንገል” ይሉታል፤ በ1948 በታተመው መፅሐፍ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ መፅሐፋቸው። ዶ/ር እሌኒ ገ/መድህን ደግሞ በ1991 ስለኢትዮጵያ የእህል ደላሎች ሚና ካቀረቡት የጥናት ፅሁፍ ላይ ደላላ የሚለው ቃል ምንጩ ከአረቢኛ መሆኑንና በሀገራችን ብቻ ሳይሆን በናይጄሪያ “ዲላሊ” በህንድ “ደላል” የሚለው ስያሜ እንዳለው ጠቅሰዋል።

ደላሎች ቤት፣ መሬት፣ መኪና መሸጥ ማከራየት ብቻ ሳይሆን ከምንመገበው እህል አንስቶ ሌሎች ቁሳቁሶች የቤት ሠራተኛ ብሎም የፍቅር ወይም የትዳር አጋር ያገናኛሉ። በአምራቹና በጅምላ ወይም በችርቻሮ ሻጩ በአጓጓዡ መካከል አሉ። በገዥና በሻጭ መካከል ቤት፣ መኪና ሽያጭ ኪራይ በየሰፈራችን በሚያጋጥሙን ላይ እናተኩር። ለምሳሌ ቤት ለመከራየት ትሄዳለህ። የፈለከውን አይነት ቤት ብትጠይቀው ደላላው የለም አይልህም። የሚነግርህና ደርሰህ የምታየው ቤት አንዳንዴ አይገናኝም። እዚች ጋር እያለ ቅርብ ነች፤ እያለህ በወሬም በመንገድም አዳክሞ ቤት ለመባል አማራጭ ከግድግዳ በቀር የማይታይ ነገር ያሳይሃል። በዋጋዋ ደንግጠህ ሳታበቃ ስለአከራዮቹ መልካምነት ስለሰፈሩ ጥሩነት ይሰብክሃል። ከተከራየህ 10 በመቶ ያስከፍልሃል። ከአከራዩም ይቀበላል። መቶ ብር ጨምሮ የሚከራይ ተከራይ ሲያገኝ አከራይህን ጀንጅኖ ወይ ዋጋ ያስጨምርብሃል ወይም ሰበብ ፈጥረው ቤቱን ያስለቅቁሃል።

ብሎልህ ቤት ከገዛህ ደግሞ ደላላው ዋጋ ይነግርሃል፤ ቤቱን ያሳይሃል። ትስማማለህ ከዋጋው ሁለት ከመቶ ይቀበልሃል። ሻጭም የራሱ ደላላ ከሌለው ይኸው ደላላ ሁለት ከመቶ ይቀበላል።

ፈርቅ የሚባል ነገርም አለ። ለሻጭ ከዚህ በላይ ከሸጥኩ ለኔ ብሎ ንብረቱ ከሚያወጣው በላይ የሚያጓጓ ዋጋ ይጠራለታል። ለምሳሌ 24ሺህ የሚያወጣን ሶስት መቶ እሸጥልሃለሁ ከዚያ በላይ ከሸጥኩ ለኔ ትተውልኛለህ ብሎ ይስማማል። ከገዢ ጋር መጥቶ የንብረቱን ጥሩነት የዋጋውን ርካሽነት አሳምኖህ ከ350ሺ በታች አይሸጥም ቅድም አንዱ 345 ሺህ ሰጥቶት እምቢ አለ ይልሃል። አንድ ሁለት ተመሳሳይ ንብረቶችን 500ሺ ይባላሉ ብሎ ያሳይሃል ከዛ ትስማማለህ። በዚህ ደላላው 2 በመቶ ኮሚሽኑን ጨምሮ 50ሺ ፈርቅ ይይዝብሃል ወይም በግልባጩ 50ሺህ የምትሰጠኝ ከሆነ 300ሺ ላስጨርሰው ይልሃል። እሺ ካልክ 350ሺህ ከፍለህ ለሻጭ 300 ሺ ይደርሰዋል መካከል ላይ ያላቸው ፈርቅ ነች።

ድለላ ከእውነት፣ ከስነምግባር አንፃር ምንም ስለማይጠይቅ እዚያው በአካባቢህ ካለህ መረጃ ተነስተህ ልትከብርበት ትችላለህ። ምላስና ከገዥና ከሻጭ የተሻለ መረጃ ካለህ በቂ ነው። የቤት ኪራይም ሆነ ሽያጭ ዋጋ በገበያው ወይም በሻጩ አይደለም የሚወሰነው። በአካባቢው ደላሎች ነው። ይሄን የገበያውን ሚና የወሰዱት ለፈርቅ ስለሚመቻቸውና ዋጋ በመጨመረ ቁጥር በመቶኛ የሚያገኙት ክፍያ ስለሚጨምር ነው። እኛ ጋር ደላላው ሌላ ሕጉ ሌላ ነው ሕጉ ምን እንደሚል እንይ።

 1. ድለላ በሕጋችን፡- በ1952 የወጣው የንግድ ሕጋችን አንቀፅ 57 ስለ “ደላሎች” ይናገራል።
  1. ድለላ ተዋዋዮችን እንደ ሽያጭ፣ ኪራይ፣ ኢንሹራንስ የማመላለሻ ውል ለመዋዋል የሚፈልጉ ሰዎችን ፈልገው የሚያገናኙ ናቸው። እውነታው ግን ደላሎች ፈልገውን አያውቁም። ገዥ ወይም ሻጭ ነው ፈልጎ የሚያገኛቸው።
  2. ድለላ ራሱን የቻለ ጥቅም ለማግኘት የሚሰራ የሙያ ተግባር ሲሆን ደላላው ምንም ያገናኝ ምን በንግድ ሕጉ መሠረት ነጋዴ ነው። በመሆኑም የንግድ ፈቃድ ማውጣት አለበት። ይህን ለማግኘት ደግሞ የድለላ ሙያ ልምድ፣ የትምህርት ዝግጅት አስፈላጊ ካፒታል ቋሚ አድራሻ ያስፈልጋል። የንግድ ፈቃድ በግል ንግድ ወይም በንግድ ማህበር መሆን አለበት። ስለዚህ ከንግድ ስራ የሚገኝ ገቢ ግብር መገበር ያገኙት ገቢና ግብር መታወቅ አለበት። ተገቢው አካልም አሰራራቸውን ቁጥጥር ሊያደርግበት ይገባል።

በተግባርስ ሌላ ነው የመድህን ዋስትና ደላሎች ብቻ በብሔራዊ ባንክ ፈቃድ የሚሰጣቸውን ቁጥጥር የሚያደርግባቸው ሲሆን ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶች ቡና፣ ሰሊጥ የገበያ አገናኞችም እንዲሁ ይደረጋል። የቁም ከብት ግብይት ላይም ግብይቱንና የመካከል ደላሎችን የሚቆጣጠር ተመሳሳይ አዋጅ ወጥቷል። ከዚህ ውጭ በተለይ የቤት ኪራይና ሽያጭ ደላሎች ተወሰኑ ካልሆነ በስተቀር የንግድ ፈቃድ ያላቸው ግብር የሚገብሩ ፈቃዱን ለማግኘት ሙያው የሚያስፈልገው ልምድና ትምህርት እንዲሁም ስነምግባር የላቸውም ግን ይደልላሉ።

 1. የደላላ አበል የንግድ ሕጋችን በድላላው አስማሚነት ውሉን ካስጨረሰ የውሉ ግዴታ ቢፈፀምም፣ ባይፈፀምም ይከፈለዋል ይላል። በተግባር ግን የሚታየው ደላላው ዋጋ ይነግርሃል፤ ቤቱን ያሳይሃል። ተከራክረህ የምትፈልገው ዋጋ ላይ የምትደርሰው አንተ ነህ።

-    በልማድ የታወቀ ካልሆነ ወይም ሌላ ስምምነት ከሌለ አበል የሚከፈለው አገልግሎቱን የጠየቀው ሰው ነው።

-    በተግባር ግን ለአንድ አገልግሎት ደላላው ወይም ደላሎቹ ከሁለቱም ይቀበላሉ።የሚከራይ ቤት አለ እንበል። አከራይ ለደላላ ይነግራል። ደላላ ተከራይ አይፈልግም። ተከራዩ ነው ቤት ፈልግልኝ የሚለው ሕጉ እንደሚለው ተዋዋችን ደላላው ስለማይፈልግ የሚፈልጉት እነሱ ስለሆነ ከሁለቱም አበል ይጠይቃል።

-    የአበሉ መጠን በቅድሚያ በስምምነት መወሰን አለበት። ደላላውና ተዋዋዮቹ የደለለበትን ይህን ያህል ልከፍልህ ተባብለው መስማማት አለባቸው። በተግባር ግን ይህ ስምምነት ስለማይደረግ ደላላው ኪራይ ከሆነ የመጀመሪያውን ክፍያ 10 በመቶ ሽያጭ ከሆነ 2 በመቶ ይቀበላል።

ስምምነት ከሌለ የደላላው አበል በልማድ መሠረት ይቆረጣል ይላል ሕጉ ደላሎች ለዚህ ነው አበላቸው በቁርጥ እንዳይሆን የሚፈልጉት። ስለዚህ በአንድ ቀን ሄዶ ቤቱን አሳይቶ ዋጋ ለተናገረበት ኪራይ 10 በመቶ ሽያጭ 2 በመቶ ትከፍላለህ።

ሕጉ ተዋዋዮች ቢስማሙም እንኳን የተስማሙበት አበል ከባድ መስሎ ሲታየው ወይም ደላላው ከሰጠው አገልግሎት ጋር ተመጣጣኝ አለመሆኑ ሲታየው በአንቀፅ 59(3) ለፍ/ቤት የመቀነስ ስልጣን ሰጥቶታል። በተግባር ግን ደላሎች በዚህም በዚያም ብለው ተመጣጣኝ ሆነ አልሆነ ያስከፍሉሃል።

የን/ሐ/አ 58 ደላላው ኃላፊነት አለበት ይላል። በሁለቱም ተዋዋዮች ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት ኃላፊ ነው።

በተግባር ደላላ ቢጎዳህም ከብስጭት በስተቀር ብዙ ሰው በኃላፊነት ካሳ ሲጠይቀ አይታይም። ቋሚ አድራሻ ቀርቶ ስማቸውን እንኳን የማናውቃቸው ሰዎች ናቸውና የሚደልሉት ለመጠየቅም ቢሞከር አስቸጋሪ ነው።

ደላላ ስትጠቀሙ በተለይ ለገዥ ወይም ለተከራይ አበሉን በተመለከተ በቁርጥ በቅድሚያ ተስማሙ በፐርሰንት ከሆነ ዋጋውን ከፍ ያደርጉባችኋል። በፅሁፍ አድርጉት ከአገልግሎቱ ጋር የተጋነነ ክፍያ ከጠየቋችሁ ተስማምታችሁም ቢሆን ለመክፈል እምቢ በሉ።

ቢቻል ንግድ ፈቃድ እና ቋሚ አድራሻ ያላቸውን ደላሎች ተጠቀሙ። ከገዥ ወይም ከሻጭ ጋር ከተገናኛችሁ በኋላ ስለዋጋው ስለደላላው አበል በደምብ ተነጋገሩ ሁለታችሁም አበል በየግል ከመክፈል ያድናችኋል።

መንግሥት የቤት፣ የመኪና ሽያጭና ኪራይ ደላሎች ላይ በተለይ ስራው ሙያዊ የታወቀ እውቀቱና ተገቢው ስነምግባር ያላቸው በኃላፊነት ሊጠየቁ የሚችሉ ሰዎች የሚሰሩት ስራ እንዲሆን ተጨማሪ ሕጎች ማውጣትና ተገቢውን ቁጥጥር ደላሎች ላይ ማድረግ አለበት።

 1. የመድህን ድለላ፡- በአግባቡ ቁጥጥር እየተደረገባቸው ከሚሰሩ የድለላ ስራዎች መካከል ለአብነት የመድህን ድለላ ስራን እናንሳ። የመድህን ሥራን ለመደንገግ የወጣው አዋጅ ቁጥር 746/2004 በአንቀፅ 2(19) ላይ የመድን ደላላን ትርጓሜ ሰጥቷል። በዚህ ትርጓሜ መሰረት የመድህን ደላላ ማለት በመድህን ገቢው ሰው ስም የመድህን ውል ለማማዋ የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶችን የሚያመቻች፣ የመድን ውል ለመዋዋል የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶችንየሚያመቻችና የመድን ውል ቀጣይ አስተዳደርና እድሳትን ለመድን ገቢው እገዛ የሚያደርግ እንዲሁም በመድን ውለታና በካሳ ክፍያ ጥያቄ ላይ ለመድን ገቢው የማማከር አገልግሎት የሚሰጥ ሰው ነው። ለዚህም አገልግለቱ ከመድን ገቢው ኮሚሽን ያስከፍላል። ይህ በሕግ የተደነገገ ከልማዳዊ ድለላ ሥራዎች በተለየ መልኩ የመደን ደላሎች የሚሰጡትን አገልግሎት ወሰን መቀመጡ አገልግሎቱን ጠቃሚዎችም ሆኑ የመድህን ደላላው ሚናውን ለይቶ እንዲያውቅ ስለሚያደርገው በልማዳዊ የድለላ ስራዎች ላይ የሚታዩት ችግሮች እንዳይከሰቱ ያደርጋል።

ከሌሎች የተለመደ የደላላ ስራዎች በተቃራኒ በመድህን ደላላነት ለመሰማራት የሚያስፍለገው መስፈርትና ፈቀድም በአዋጅ ቁጥር 746/04 አንቀፅ 39 ስር ተቀምጧል።

የመድህን ደላሎችን ቸምሮ ማንኛውምየመድህን ረዳት ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ካልተሰጠው በስተቀር በመድህን ድላላ ስራ ላይ መሰማራት አይችልም። ህ አገልግሎቱ ሙያዊ ደረጃውን እንዲጠብቅ የሚያደርገው ሲሆን ብሔራዊ ባንኩምየሚያስፈልገውን ዝቅተኛ የብቃት መመዘኛ መስፈርት በመመሪያ ይወስናል።

በተጨማሪ የመድን ደላላው ፈቃድ ለማግኘት ማመልከቻ ማቅረብ የሰነድ ምርመራና የፈቃድ ክፍያም ይጠይቃል።

የመድን ደላላው ፈቃድን ካገኘ በኋላ ብሔራዊ ባንኩ በወሰነው ጊዜ ፈቃዱን ማሳደስ አለበት። በተጨማሪ ፈቃድን ለማሳደስ ፈቃዱን ለማገድ ወይም ለመሰረዝ የሚያበቁ ሁኔታዎችንም ተቆጣጣሪው ብሔራዊ ባንክ በመመሪያ የወሰነ በመሆኑ ባልታደሰ ወይም በተሰረዘ ፈቃድ ወይም ያለ ፈቃድ ሲሰራ የተገኘ የመድን ደላላም ሕገወጥ ስራ ላይ እንደተሰማራ ይቆጠራል። ይህ ለአብነት ያነሳነው በፈቃድና በቁጥር የሚሰራ የመድን ድለላ ስራ ውጤታማና ተገልጋዩን የሚያረካ አስተማማኝ ተጠያቂነት ያለበት ሙያዊ ደረጃውን የጠበቀ የድለላ ስራ እንዲሆን አድርጎታል። በመሆኑም ከላይ ያነሳናቸው የተለምዶ የድለላ ስራዎችም በሚመለከተው አካል ተገቢው ሕግ መስፈርትና ፈቃድ ቢወጣላቸው የድለላ ሥራ አሁን ካነሳነው ገፅታው የተለየ አስተማማኝ ጠቀሜታ ይኖረዋልና የሚመለከታቸው አካላት ቢያስቡበት መልካም ነው።

ይምረጡ
(3 ሰዎች መርጠዋል)
6930 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

 • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

 • Aaddvrrt5.jpg
 • adverts4.jpg
 • Advertt1.jpg
 • Advertt2.jpg
 • Advrrtt.jpg
 • Advverttt.jpg
 • Advvrt1.jpg
 • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 829 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us