ከመድን ዋስትና ጋር የተያያዙ የወንጀል ኃላፊነቶች

Wednesday, 01 April 2015 15:11

በኪዳኔ መካሻ (የሕግ ባለሙያ)

This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

 

1. ሞቻለሁ ብሎ የመድን ዋስትና ያጭበረበረው አሜሪካዊ ተከሰሰ

አሰሽዬትድ ፕሬስ ባለፈው ሳምንት ያወጣው ዘገባ ነው። ግለሰቡ ጆስ ላንቱጋ የ62 ዓመት በቤት ውስጥ እቃዎች በንግድ ሥራ የሚተዳደር የፍሎሪዳ ነዋሪ ነው። ከሁለት ዓመት በፊት ለመዝናናት ቬንዙዌላ በነበረበት ጊዜ በሀሰት እንደታመመ አድርጐ የንግድ ስራው የሚፈለግበት በርካታ ሚሊዮን ዶላር ሳይከፍል እንደሞተ ይገለፃል።

ለህይወቱ የመድን ዋስትናስትና ሽፋን የሰጡ ኩባንያዎችም ሁለት አበዳሪዎቹ ክስ ይመሰርቱባቸዋል። ምክንያቱም ጆስ ሞተ ከተባለበት ጊዜ በፊት ከህይወት የመድን ዋስትና የሚገኘው ክፍያ ለአበዳሪዎቹ ዕዳ መክፈያ እንዲውል ተስማምቶ ነበር። በዚህም ኩባንያዎቹ ሆን ብሎ ነው እንጂ ጆስ አልሞተም የሚል ጥርጣሬ ስለገባቸው ምርመራ ጀመሩ።

ሆትፎርድ የተባለው የህይወት የመድን ኩባንያ የመሰረተው ክስ የጆስ አስክሬን እንደተቃጠለ በማስረጃነት የቀረበው የሰነድ ማስረጃ ሰራተኛውን በጉቦ በመደለል የተገኘ ነው በሚል መነሻ ላይ የተመሰረተ ነበር። ሌሎቹ ኩባንያዎች ደግሞ ጆስ ላንቲጓ በማጭበርበር ከህይወት የመድን ክፍያ የሚገኘውን ገንዘብ ለአካባቢው አበዳሪዎች ከመጥፋቱ በፊት እንዲከፈል ተጠቃሚ አድርጓቸዋል።

የጆስ ልጅ የመድን ኩባንያውን የአባቴን ሞት የሀሰት አድርጐ በማቅረብ የቬንዙዋላ መንግስት የሞት ምስክር ወረቀቱን እንደሰረዘ አድርጐ በሀሰት አቅርቧል ብሎ ክስ ይመሰርትበታል። የመድን ኩባንያውም የቬንዙዋላ ጠባቂ የቬንዙዋላ መንግስት የሞት ምስክር ወረቀቱን ውድቅ እንዳደረገ አስመስሎ ማቅረቡን ያምናል። ዳኛውም ማን የጆስ የሞት ምስክር ወረቀትን እንዳጭበረበረ ባይታወቅም፤ ሰነዱ ግን የተጭበረበረ ነው የሚል ውሳኔ ይሰጣሉ።

ክርክሩ በዚህ ደረጃ ላይ ደርሶ የመድን ኩባንያዎቹም የጆስ የሞት ም/ወረቀት የተጭበረበረ ነው የሚለው ማስረጃ የሀሰት በመሆኑ ተቀባይነት ስላጣ ግራ ገብቷቸው እያለ አንድ ዜና ተሰማ።

ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ሰሜን ካሮሊና ማዛት ቦንኰምብ ካውንቴ ውስጥ አንድ መኪና አስቁመው የአሽከርካሪውን ማንነት ሲመለከቱ ሞቶ አስክሬኑ በቬንዙዌላ ውስጥ ተቃጥሏል የተባለውን ጆስ ላንቲጓን ከባለቤቱ ጋር ሆኖ ያገኙታል።

ጆስ ላንቲጋ ተይዞ ፍሎሪዳ ውስጥ 9 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ የህ/የመድን ዋስትናስትና የማጭበርበር ክስ እንደቀረበበት ዐቃቤ ሕጉ ገልፀዋል።

ዐቃቤ ሕጉ እንደገለፁት ጆስ ላንቲጓ ላይ የእስር ማዘዣ ወጥቶበት የነበረው ከዓመት በፊት ቢሆንም፤ ዐቃቤ ሕጉ በጉዳዩ ላይ የተሰበሰቡ መረጃዎች ችግር ስለነበረባቸው ውድቅ አድርገውት ነበር። ሆኖም አሁን ግን ተጨባጭ ማስረጃ ስላለ አዲስ የመ/ማጭበርበር ክስ ባለፈው ሳምንት ቀርቦበታል።

ባለቤቱንም በተመለከተ ቀደም ብሎ ጆስ በህይወት መኖሩን ስለማወቋ ሊረጋገጥ ስላልቻለ ሰሜን ካሎሪና ውስጥ አብራው ስትያዝ ማረጋገጫ ነበር። ነገር ግን ሳይሞት እንደሞተ መደረጉን ማወቋ አብራው መገኘቷ ስላረጋገጠው በፌዴራል ፖሊሶች ፍሎሪዳ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውላለች።

የዶስን ቤተሰብ በተለያዩ ክሶች ላይ ወክለው ሲከራከሩ የበሩት ጠበቃ ጆሽዋ ዋልሲ እሳቸውና የጥብቅና ድርጅታቸው ከክርክሩ መውጣቱን ወዲያውኑ ገልፀዋል።

“እኔና የጥብቅና ድርጅቱ ጆስ ሞቷል በሚለው ማስረጃ በመተማመናችን መታለላችንን ስናውቅ በጣም ነው የደነገጥነው” ሲሉ ገልፀዋል።

ይህ ሰሞኑን አሶሺዬትድ ፕሬስ ያወጣው የመድን ማጭበርበር ጉዳይን ለምሳሌነት ነው ያነሳሁት። እንዲህ አይነት የመድን ማጭበርበርና ሕገወጥ የመድህን ስራዋች ሲፈፀሙ የወንጀል ሕጋችን እና የመድህን አዋጁ የደነገጓቸውን ኃላፊነቶችና ቅጣቶች እናያለን።

የመድህን ስራዎችን የሚቆጣጠረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የመድን ማጭበርበር ድርጊቶችን የመድን ኩባንያዎች ለብሔራዊ ባንኩ እንዲያሳውቁ የሚያስገድድ መመሪያ በጥር ወር 2007 ዓ.ም አውጥቷል።

2. የመድን ማጭበርበር ድርጊት በወንጀል ሕጋችን

በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀፅ 698 ላይ ኢንሹራንስን በተመለከተ የሚፈፀሙ የአታላይነት ድርጊቶችና የሚያስከትሉት የወንጀለ ኃላፊነቶች ተቀምጠዋል።

  • የማይገባ ብልፅግናን ለራስ ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ፤

ሀ. መድን የተገባለትን አደጋ መፍጠር

ለ. ፍሬ ነገርን መደበቅ፣ ማሳሳት፣ ማረጋገጥ፣ ሀሰተኛ መግለጫ በመስጠት የመድን ኩባንያውን ያሳሳተ

-    የመድን ዋስትናውን የገንዘብ ልክ

-    የውሉን ዘመን

-    የመድን ዋስትናውን ተጠቃሚዎች የሚመለከቱ ነገሮችን መደበቅ የተሳሳተ መረጃ መስጠት በውሉ ውስጥ በተገለፀው ጥቅም ላይ ተፅዕኖ በሚያደርግ አኳኋን ድርጊቱን ከፈፀመ

ሐ. በማንኛውም ሌላ መንገድ ከመድን ዋስትና እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የአታላይነት ድርጊት የፈፀመ በቀላል እስር (ከ10 ቀን እስከ 3 ዓመት) ወይም ሁኔታው ከባድ ሲሆን ከ5 ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስርና ከብር 50 ሺህ በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል።

ይህ የማታለል ድርጊት የተፈፀመው በሀሰተኛ ሰነድ ሲሆን፤ ደግሞ ሀሰተኛ ሰነድ ማዘጋጀትን መጠቀምን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች በተደራቢነት ተፈፃሚ እንደሚሆኑ ቁጥር 699 ይደነግጋል።

3. በወንጀል የሚያስጠይቁ የመድን ስራዎች

ሌሎች በመድህን ስራ አዋጁ ላይ የተከለከሉ ተግባራትን የሚፈፅሙ የመድን ዋስትና ስራ ላይ የተሰማሩና ተያያዥነት ያላቸውን ስራዎች የሚሰሩ ደግሞ በወንጀል ሕጉ የበለጠ የሚያስቀጣ ስለሆነ በአዋጁ ላይ በተቀመጠው ቅጣት መሰረት በወንጀል ይቀጣሉ።

ለምሳሌ በመድህን ስራ በአዋጅ ቁጥር 746/2004 አንቀፅ 3 (1) ማንም ሰው ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ሳያገኝ በኢትዮጵያ ውስጥ የመድህን ዋስትና ሥራ መስራት አይችልም። ይህን ሲሰራ ከተገኘ እስከ 15 ዓመት ፅኑ እስር ይቀጣል።

በአንቀፅ 3(4) ከብሔራዊ ባንኩ ፈቃድ ሳያገኝ የመድን ስራ ለመስራት ማስታወቂያ ያወጣ ወይም የመድን ስራ እየሰራ መሆኑን ብ/ባንኩ ለማመን ምክንያት ሲኖረው ይህንኑ ለማጣራት በይዞታው የሚገኙ የንግድ መዝገቦች፣ ቃለ ጉባኤዎች፣ ሂሳቦች፣ የዋስትና ሰነዶች፣ ማስታወሻዎች፣ ገንዘብ ማዘዣዎችና ሌሎች ሰነዶች እንዲቀርቡ ማዘዝ ስለሚችል ይህን ለማቅረብ ፍቃደኛ ያልሆነ ሰው ከ7-10 ዓመት ጽኑ እስር እና ከ50 እስከ 100ሺህ ብር እስር ይቀጣል።

በአንቀፅ 17 ላይ ደግሞ ማንኛውም የመድን ኩባንያ ዳይሬክተር ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይም ከፍተኛ ስራ አስፈፃሚ ወይም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመድን ሰጪው ስራ አመራር የሚሳተፍ ሰው

ዳይሬክተር ሥራ አስፈፃሚ ሆኖ የሚሰራበት ድርጅት ከስሬያለሁ ብሎ ካመለከተ ወይም በፍ/ቤት የኪሳራ ውሳኔ ከተሰጠበት ወይም በኪሳራ ምክንያት በፍ/ቤት ትዕዛዝ ንብረቱ በንብረት ተቆጣጣሪ ስር ከዋለ ወይም ብድር ባለመክፈሉ የራሱ ወይም የኩባንያው ንብረት በባንክ ከተወረሰበት፤

ማንኛውንም ብድር ወይም ግብር ባለመክፈሉ ተከሶ ከተፈረደበት ራሱን ከመ/ሰጪ ስራ አመራር ማግለል አለበት። ወይም ብሔራዊ ባንክ የሚያመጣቸውን የብቃት መመዘኛዎች ካላሟላም ማግለል አለበት። ይህን ካላደረገ ከ10 እስከ 15 ዓመት ፅኑ እስር እና ከ50 እስከ 100ሺህ ብር መቀጮ ይቀጣል። ሌላው በአንቀፅ 33(6) ስር ማንኛውም የመድን ሰጪ ዳይሬክተሮች መድን ሰጪው ለመ/ገቢዎችና ለሌሎች አበዳሪዎች ያለበትን ግዴታ መውጣት እንደማይችል ወይም ክፍያዎችን በወቅቱ መፈፀም ሊሳነው እንደሚችል ሲገመት ሁኔታውን በጋራም ሆነ በተናጥል ወዲያውኑ ለብሔራዊ ባንክ ማሳወቅ አለባቸው። ይህን ካላደረጉ ከ7 እስከ 10 ዓመት ጽኑ እስራት እና ከ50 እስከ 100ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ይቀጣሉ።

በአንቀፅ 57(6)(ለ) ስር ደግሞ ማንኛውም የመድን ሰጪ ዳይሬክተር ወይም ሰራተኛ ለማታለል በማሰብ የሀሰት ወይም አሳሳች መግለጫ የሰጠ ወይም በመ/ሰጪው መዝገብ፣ ሂሳብ፣ ሪፖርት ወይም መግለጫ ውስጥ የመዘገበ ወይም መመዝገብ የነበረበትን መግለጫ ወይም መረጃ ሳይመዘግብ የቀረ

መድን ሰጪው ዕዳ መክፈል በማይችልበት ወሰን ላይ መሆኑን እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው የመድን ውል የተዋዋለ ወይም ሌላ ሰው እንዲዋዋል ያፀደቀ ከ10 እስከ 100 ሺ በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል።

ሌላው በአንቀፅ 57(7) ስር የተደነገገው የመድን ስራ አዋጁን እና አዋጁን ለማስፈፀም የወጡ ደንቦችን መመሪያዎችን የተላለፈ ወይም አፈፃፀማቸውን ያሰናከለ ማንኛውም ሰው እስከ 3 ዓመት በሚደረስ እስርና እስከ ብር 10ሺህ በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እንደሚቀጣ አዋጁ ይደነግጋል።

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
5816 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 781 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us