የኮኮናት (የዘንባባ) ዘይት ጥቅሞች

Wednesday, 04 October 2017 12:55

 

በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከዘንባባ ፍሬ የሚገኘው ዘይት ጐጂ ባክቴሪያን የመግደል አቅሙ እጅግ ከፍተኛ ነው። የአሜሪካ ልክ ህክምና ማህበር ባደረገው ጥናት እንዳረጋገጠውም ይህ ዘይት 50 በመቶው ላውሪክ አሲድ በመሆኑ በቫይረስ የሚመጣ ኢንፌክሽንን ለመከላከል ያገለግላል። በተጨማሪም ስታፊሎክስስ አውሪየስ የተባለውን አደገኛ ባክቴሪያ ለመግደል ይጠቅማል። በዚሁ ጠቀሜታውም የዓለማችን ምርጡ ምግብ ተብሎ ይጠራል።

 

ወደምግብነት ይዘቱ ስንመጣ ደግሞ የዘንባባ ፍሬ ዘይት ረሃብን በማስታገስ በኩል ወደር የማይገኘለት ነው። ይህ ዘይት በውስጡ የሚገኘው ፋቲ አሲድ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ ይህ ፋቲ አሲድ የምግብ ፍላጐትን መጠን በመቀነስ የረሃብ ስሜት እንዳይሰማ ያግዛል። በዚህም በተለይ የሰውነታቸውን ክብደት ለመቀነስ የሚፈልጉ ሰዎች የሚመገቡትን የምግብ መጠን በመቀነስ ክብደታቸውን እንዲቀንሱ ያግዛቸዋል።

 

በሌላ በኩል ደግሞ የዘንባባ ፍሬ ዘይት በደም ውስጥ የሚገኘው ኮሌስትሮል መጠን እንዲቀንስ የማድረግ ጠቀሜታ አለው። በዚህ ዘይት ውስጥ የሚገኘው ሳቹሬትድ ስብ ጠቃሚ የሆነው ኮሌስትሮል መጠን እንዲጨምር በተቃራኒውም ጐጂ የሆነው ኮሌስትሮል መጠን እንዲቀንስ ያግዛል። ከዚህ ጋር ተያይዞም እንደ ስኳር ህመም፣ ከፍተኛ የደም ግፊት እና ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይከሰቱ ይከላከላል።

 

በዘንባባ ፍሬ ዘይት ውስጥ የሚገኘው ሳቹሬትድ ፋት በተፈጥሮ የሰውነት ተግባራት እንዲፋጠኑ፣ ከፍተኛ የሆነ ኃይል እንዲያመነጩ እንዲሁም ከምግብ ጋር የሚገቡ ስቦች በፍጥነት ተቃጥለው የስብ ክምችት እንዳይፈጠር የማድረግ ጠቀሜታ ስላለው ያልተፈለገ የሰውነት ክብደትንና የልብ ህመምን ለመከላከል ያግዛል። የዘንባባ ፍሬ ዘይት ከሰውነት ጋር በቀላሉ መዋሃድ የሚችል በመሆኑም በርካታ ጠቀሜታዎችን ይሰጣል።

 

የዘንባባ ፍሬ ዘይት ከዚህ በተጨማሪም አደገኛ ባክቴሪያዎችን የመግደል ባህሪይ ስላለው የቆዳን ጤንነት ለመጠበቅ ያግዛል። ቆዳ ላይ ተፈጥረው ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ባክቴሪያዎችን በማስወገድ እንዲሁም እንደፎረፎር ያሉ ችግሮችን ከጭንቅላት ላይ እንዲፈጠሩ የሚያደርጉ ባክቴሪያዎችን በመከላከል ረገድ የዚህ ዘይት ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው።

ይምረጡ
(3 ሰዎች መርጠዋል)
916 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1033 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us