ከባድ ብርድ ልብሶች መድሐኒት ናቸው

Wednesday, 04 October 2017 12:57

 

ሙቀት ለሰው ልጆች አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች አንዱ ነው። ሙቀትን ለማግኘት የተለያዩ አማራጮችን የምንጠቀም ሲሆን፤ ከእነዚሁ መካከልም ውፍረት ያላቸው አልባሳትን መልበስ ነው። ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ደግሞ ክብደት ያላቸው እንደ ብርድ ልብስ ያሉ አልባሳትን መልበስ በርካታ ጥቅሞች አሉት። በፍራንኮኒያ ሆስፒታል ቴራፒስት የሆኑት ዶክተር ከረን ሙር እንደሚሉት ደግሞ ከፍተኛ ክብደት ያላቸው አልባሳትን ለብሶ መተኛት እንደ ጭንቀት፣ ድብርት እንቅልፍ ማጣት እንቅልፍ ማጣት እና መሰል የአዕምሮ ችግሮችን ለመከላከል ያግዛል።

 

እንደ ባለሙያው ገለፃ በሰውነት ላይ የሚያርፍ ክብደት ወይም ጫና ለሁሉም የሰው ልጅ መጠነ ሰፊ ጠቀሜታን ይሰጣል። ክብደት ያላቸው ነገሮች ሰውነታችን ላይ በሚያርፉበት ጊዜ ልክ ሰውነትን እንደመታሸት ሁሉ ለአካል እና ለአዕምሮ እንዲሁም ለስነ ልቦና የሚሰጠው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው ተብሏል። በሰውነት ላይ የሚያርፈው ጠንከር ያለ ጫና በሰውነት ላይ በሚያርፍበት ጊዜ ሰውነትን ዘና የማድረግ እና የማረጋጋት ጠቀሜታ ይሰጣል። ዶክተር ሙር እንደሚሉትም ክብደት ያላቸው አልባሳትን ለብሶ መተኛት በንዴት፣ በአንቅልፍ ማጣት ወይም በድብርት ምክንያት ራሳቸውን ለመቆጣጠር ያልቻሉ ሰዎችን ለመፈወስ ጥሩ መፍትሄ ሆኖ ተገኝቷል።

 

ክብደት ያላቸው ብርድልብሶች ሰውነት ላይ በሚያርፉበት ወቅት ሰውነትን ከማሞቅ በተጨማሪም በሰውነት ላይ የሚያሳርፉት ሙቀት የነርቭ ሥርዓታችን እንዲነቃቃ ስለሚያደርግ ከላይ የተጠቀሱት ስሜቶች እንዲወገዱ የማድረግ ጠቀሜታ አለው። ባለሙያው አሰራሩን ሲያስረዳም ይህ ጫና በሰውነት ላይ በዝግታ በሚያርፍበት ጊዜ ሴሮቶኒን የተባለው ንጥረ ነገር በሰውነት ውስጥ በብዛት እንዲመነጭ ያደርገዋል። ይህ ንጥረ ነገር ደግሞ ለሰውነት እና ለአንጐል ጥሩ የሆነ እና የመዝናናት ስሜት እንዲፈጠር ያደርጋል። ይሄ ሴሮቶኒን ሜላቶኒን ወደተባለው ንጥረ ነገር በሚቀየርበት ወቅትም ሰውነት የማረፍ እና የመረጋጋት ስሜት እንዲፈጠርበት ያደርገዋል። ክብደት ያላቸው የብርድ ልብሶች ለሰውነት ተስማሚ እና ተመጣጣኝ የሆነ ክብደት እንዲኖራቸው ተደርገው የተሰሩ በመሆናቸው በሚያርፉበት የሰውነት ክፍል ላይ ሁሉ ተመሣሣይ ክብደት እንዲያርፍ ያደርጋል። ክብደት ሲያርፍባቸውም እና ሰውነት መነቃቃት ሲጀምር አንጐል የሚያመነጨው ሴሮቶኒን መጠን እንዲያሻቅብ ያግዘዋል።

 

በ2008 (እ.ኤ.አ.) በዋሽንግተን በተደረገ እና ኦኩፔሽናል ቴራፒ ጥናት ማረጋገጥ እንደተቻለው ክብደት ያላቸው ብርድልብሶች በንዴት ስሜት ውስጥ ያሉ ሰዎችን ለማከም ያግዛሉ። ይሄንን እውነታ ለማረጋገጥ በ2012 በአውስትራሊያ የተደረገ ጥናት እንዳመለከተው ክብደት ያላቸው ብርድ ልብሶች ድብርት እና ጭንቀት የመሳሰሉ ችግሮችን ለማስወገድ ያግዛል።

 

ከአንጐል ችግር ጋር ተያያዥነት ያላቸው እንደ ድብርት፣ ጭንቀት፣ የአንጐል መታወክ ያሉት ችግሮች በአንጐል ውስጥ የሚመነጨው የሴሮቶኒን ንጥረ ነገር መጠን አነስተኛ በሚሆንበት ወቅት ነው ይላሉ በመስኩ የተደረጉ ጥናቶች። በመሆኑም ክብደት ያላቸውን ብርድ ልብሶች መልበስ በቀጥታ ሰውነት ይሄንን ንጥረ ነገር በማመንጨት የአንጐል ሴሮቶኒን መጠን እንዲያሻቅብና ሰውነትም እንዲነቃቃ ያደርገዋል።

 

ክብደት ያላቸው ብርድልብሶች ከዚህ በተጨማሪም እንደ ኦቲዝም፣ አልዛይመርስ እንዲሁም የእግር መንቀጥቀጥን ይከላከላል። በሴቶች ላይም በማረጥ ጊዜ የሚከሰቱ ከአንጐል ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ችግሮች ለመከላከል ያግዛል። በአጠቃላይ ሲታይም ክብደት ያላቸው ብርድ ልብሶችን ለብሶ መተኛት ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ምንም አይነት መድሐኒትን ሳንጠቀም ከአንጐል ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ችግሮች ለማስወገድ የሚረዳ መፍትሄ ነው ብለዋል ባለሙያዎቹ። ከላይ ከተጠቀሱት የአንጐል ችግሮች የቀን ውሎ ውጤታማ እንዳይሆን ከማድረግም በተጨማሪ እንደ ልብድካም ያሉ ተያያዥ የጤና ችግሮችን የማያስከትሉ ከመሆናቸው አንፃር በዚህ መልኩ መከላከል ይቻላል ተብሏል። እነዚህን የብርድ ልብስ አይነቶች ሁሉም ሰው መጠቀም የሚችል ቢሆንም የመተንፈሻ አካላት ችግር፣ የደም ዝውውር እክል ወይም ከሰውነት ሙቀት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ችግሮች ያሉባቸው ሰዎች ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ይላሉ ባለሙያዎቹ።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
968 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1080 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us