Items filtered by date: Wednesday, 12 April 2017 - Sendek NewsPaper

 

በዮሴፍ አለሙ

 

ኢትዮጵያ ከ10 አመት በላይ በየአመቱ ከ8 በመቶ እስከ 11 በመቶ ፈጣን የሚባል  ኢኮኖሚያዊ እድገት እያስመዘገበች  መሆኗን ድረ-ገፁ CIA WORLD FACTBOOk  ያለፈው ጥር 12 ቀን 2017 በፈረንጆች አቆጣጠር ትኩስ መረጃውን እንካችሁ ይለናል። በሚገርም  ሁኔታ ከ188ቱ የIMF አባል አገሮች መካከል  ፈጣን  ኢኮኖሚያዊ እድገት በማስመዝጋብ ኢትዮጵያችን በ5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ይህ ፈጣን  ኢኮኖሚያዊ እድገትም አስተማማኝና ቀጣይነት አለው ከሚባለው የግብርና እና የአገልግሎት ዘርፍ የመጣ መሆኑን ድረ-ገፁ ይገልፃል።


ነገር ግን ፍትሀዊ ነው ከሚባለው ከእስካንድኒቪያን ሀገሮች ኢኮኖሚ አንፃር ሲታይ  ይህ የኢትዮጵያ ፈጣን የሚባለው ኢኮኖሚያዊ እድገት ሁሉንም ኢትዮጵያዊ  ያማከለ ወይንም ያዳረሰ ባለመሆኑ ምክንያት  ኢትዮጵያችን በኢኮኖሚ ዕድገት ከአፍሪካ  በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡  ይህ ማለት በኢኮኖሚስቶቹ ቋንቋ ኢትዮጵያ አንፃራዊ አይደለም፡፡ ፍፁም ያልተመጣጠነ ኢኮኖሚያዊ እድገት ያላት አገር ሲል  ዝቅ አድርጎ አስቀምጧታል - ይህ በቁጥር  ሲገለፅ   ኢትዮጵያ 33 በመቶ ያልተመጣጠነ የሀብት ክፍፍል  የታየባት ሀገር ሲል በ173ኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል በ2011ዱ ጥናት መሰረት ። ሆኖም ግን  ኢትዮጵያችን ድህነትን ታግላ ለመጣል፥ ድህነትን ታሪክ ለማድረግ ደፋ ቀና እያለች መሆኗንን  ድረ-ገፁ  CIA  ባይክድም  እውነታው ግን ኢትዮጵያችን ካላት ፈጣን የሆነ የህዝብ እድገትና የአጭር ጊዜ የእድገት ጅማሮ ምክንያት በፕላኔታችን ላይ አሁንም ድረስ  ድሀ ከሚባሉት ተርታ መሆኗን ይገልፃል።


ሌላኛው  ተጨማሪ እንቅፋት ከዓለም የአየር ንብረት ጋር ተያይዞ  ዝናብ ወቅቱን  ጠብቆ ባለመዝነቡ ምክንያት ከ30 ዓመት በኋላ ድጋሚ በ2015/2016 የተከሰተው ድርቅ ብዙ ሚሊዮን ኢትዮጲያዊውያንን ለረሀብ   አጋልጧል። ለዚህ ደግሞ ትልቁ ምክንያት 80 በመቶ ኢትዮጵያዊ በግብርና የሚተዳደር መሆኑ ነው። ነገር ግን በዚሁ አጋጣሚ የአገልግሎት  ዘርፉ ደግሞ ግብርናውን በመከተል  ለአገሪቱ  GDP ዕድገት ከፍተኛ ድርሻ እያደረገ ይገኛል።


የመሬት ባለቤትነትን በተመለከተ፦  መንግስትም  ሆነ  ግለሰቡ መሬት ላይ የጋራ የሆነ የባለቤትነት መብት እንዳላቸው   በህገ-መንግስቱ  ላይ የተብራራ  ቢሆንም  ነገር ግን የግለሰቡ  መብት መሬቱን ተከራይቶ ወይም ተኮናትሮ  ለ99 አመት  የመጠቀም መብት እንጂ  መሬቱን የመሸጥም ሆነ የግሉ የማድረግ እንዲሁም በመሬቱ ዋስትና ላይ ተመስርቶ ገንዘብ የመበደር  መብት እንደሌለው  ይጠቅሳል።


በህገ-መንግስቱ መሰረት ግለ-ሰቡ መሬቱን ተከራይቶ የመጠቀም  መብት ይኑረው እንጅ  በአጠቃላይ መሬቱን  በበላይነት የመቆጣጠር ስልጣን ያለው መንግስት ነው እንደ ሲ.አይ.ኤ ዎርልድ ፋክት ቡክ /CIA world  FACTBOOk/ ተጨማሪ መረጃ፡፡ ነገር ግን እንደሚታወቀው ይህ 80 በመቶ በግብርና የሚተዳደረው ገበሬ የረጅም ጊዜ የኪራይ /lease/ መብት  እንዲኖረው በሰነድ የተደገፈ ህጋዊ የማረጋገጫ ደብተር  ተሰጥቶታል።
እንደሚታወቀው በፈረንጆች ከ2005  ጀምሮ መንግስት መሬትን አስመልክቶ አዲስ ስርዓትን በመዘርጋት ማንኛውም የድሮ  የመሬት ባለይዞታዎች ሁሉ ሰነድ ላይ  እንዲመዘገቡ በማድረግ  እያንዳንዱ ገበሬ የረጅም ጊዜ የሊዝ መብት እንዲኖረው  የማረጋገጫ ደብተር ሰጥቶታል ሲል ሲ.አይ.ኤ  ህገ-መንግስቱን  መሰረት አድርጎ አስቀምጦታል። በመጀመሪያው የመሬት ጥናት መሰረት ይህ በሰነድ የታቀፈ የይዞታ  ማረጋገጫ ደብተር እያንዳንዱ አርሶ አደር  መሬቱን  ለማልማት በየትኛውም የልማት አማራጭ ያለውን ሀይል መሬቱ ላይ በማፈሰስ ከእርከን እስከ መስኖ ልማት ድረስ እንዲያለማ መልካም  የሚባል መነሳሳትን ፈጥሮለታል ይለናል  ድረ-ገፁ CIA።


ነገር  ግን እንደ ድረ-ገፁ ዘገባ ይህ የመሬት የይዞታ መብት በአዲስ አበባ ፍትሀዊነት በጎደለው አካሄድ ማለትም  ለሙስናና ለብልሹ አሰራር የተጋለጠ በመሆኑ ምክንያት አፈፃፀሙ ዝቅተኛ በሚባል ደረጃ እየተፈፀመ መሆኑን በጥናት ደርሼበታለው ሲል CIA  አስረግጦ ይናገራል። ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያ ‘በትሬዲግኢኮኖሚክስ' ጥናት መሰረት 32 በመቶ ሙስና የተጠናወታት ሀገር መሆኗንና  በደረጃ  ሰንጠረዥ ደግሞ  108ኛ ላይ መቀመጧ ሀገሪቷ ኪራይ ሰብሳቢዎችና ሙሰኞች የበዙባት ሀገር ለመሆኗ ጥሩ ማስረጃ ነው ለማለት ያስደፍራል።


ሌላው ይህ ድረ-ገፅ  ኢትዮጵያ  ከውጭ ገበያ የምታገኘው የምንዛሪ ገቢ በይበልጥ  እያቀረበችው ካለው የአገልግሎት ዘርፍ የመነጨ  ነው ይለናል። ለዚህ የአገልግሎት ዘርፍ ደግሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ  ኢትዮጵያ ወደ ውጭ የምትልካቸውን የግብርና ምርቶችን ቡናን ጨምሮ  በማስከተል ቀዳሚ  ተምሳሌት ነው ይለናል። ቡናን ካነሳን ደግሞ ቡና ለኢትዮጵያችን  የውጭ ምንዛሬ  በማስገኘቱ ረገድ ከፍ ያለ ቦታ ቢኖረውም ሌሎች ምርቶች ማለትም ወርቅ፣ ጥራጥሬ፣ የቅባት እህሎች፣ ጫት፥ ከብቶችን፥ እንዲሁም የአበባ ምርትን ጨምሮ ጠቃሚ በሚባል ደረጃ ለውጭ ገበያ እያቀረበች መሆኑን የCIA  ጥናታዊ ዘገባ ያስረዳል። በሀገሪቱ ነገር ግን   ለውጭ ምንዛሪ ከምትልካቸው አጠቃላይ ምርቶች መካከል የፋብሪካ ውጤቶች ከ8 በመቶ በታች መሆናቸውን መረጃው ይጠቁማል። ኢትዮጵያ በውጭ ገበያ ላይ ምርቶችን በማቅረቡም ሆነ በመግዛቱ በኩል አሁንም ድረስ ኢትዮጵያ  ያልተሻገረቻቸው ገና ብዙ ሰንሰለታማ ችግሮች  እንዳሉባት ጠቅላይ ሚኒስተሩ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሳይቀር በቅርቡ ማብራሪያ  የሰጡበት ጉዳይ ነው፡፡


የመዋእለ ሀብት ፍሰትን/ኢንቬስትመንትን/ በተመለከተ፦ በባንክና የኢንሹራንስ አገልግሎት   ዘርፍ ላይ የመዋእለ ንዋይ ፍሰት፥ በቴሌኮሙኒኬሼን እንዲሁም በጥቃቅንና  አነስተኛ ብድርና ቁጠባ ኢንቬስትመንት ላይ  ለሀገር ውስጥ ኢንቬስተሮች ብቻ የተፈቀደ  ሲሆን በጨርቃ ጨርቅና በቆዳ ውጤቶች  ላይ፥ በግብርናው መስክ  በተለይም ለኢንዱስትሪው የሚበጁ ጥሬ እቃ ምርቶችን በማምረቱ ረገድ እንዲሁም መብራትንና የመብራት ግብዐት የሆኑ መሳሪያዎችን  በማምረቱ በኩል ደግሞ የውጭ ባለሀብቶች ይበልጥ እንዲሳተፉበት እየተደረገ ነው።


ሌላው CIA world  ማወቅ አለባችሁ የሚለን እውነታ  ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋ በእቅድ ላይ የተመሰረተ /planned/ መሆኑን ነው። ለዚህ ደግሞ ባለፈው በፈርንጆች 2015 ማብቂያ ላይ መንግስት ከ2016-2020፤   2ኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሺን /GTP II/ ዘመን አስመልክቶ የ5 አመት እቅድ ይፋ ማድረጉ  ኢትዮጵያ በእቅድ የምትመራ ኢኮኖሚ እየተገበረች መሆኗን  ጥሩ ማሳያ ነው ይለናል ድረ -ገፁ።


በዚህ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሺን አቅድ  ኢትዮጵያ ለኢንዱስትሪው ዘርፍ ትኩረት ሰጥታ ትሰራለች የሚለን ድረ ገፁ በተለይም በጨርቃጨርቅና በቆዳ ምርቶች እንዲሁም  በኢንዱስትሪው ውስጥ አልፈው ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የግብርና ምርቶችን ጭምር  ለውጭ ምንዛሪ ብታቀርብ የተሻለ አማራጭ ሊኖራት እንደሚችል በዚህ በሁለተኛው የ5 አመቱ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ አቅዳ ደፋ-ቀና እያለች መሆኗን መረጃው ይጠቁማል።


በተጨማሪም የሀይል ግንባታና ስርጭትን አስመልክቶ፣ የመንገድ ግንባታ የባቡር ሀዲድን ጨምሮ እንዲሁም ኤርፖርቶችንና የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባትና በማስፋፋቱ በኩል  ኢትዮጵያ   በአዲሱ የመሰረተ-ልማት ግንባታ  ውስጥ  አቅዳ እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች።


በኢንዱስትሪው ዘርፍ በኩል ደግሞ  የነበረውን 16 በመቶ የኢንዱስትሪ ጉዞ  ከግብርናው እና ከአገልግሎት ዘርፉ ጎን ተራምዶ   ለአገሪቱ የGDP እድገት  ከፍተኛ ሚና እንዲጫወት ለማድረግ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪውን ሊደግፉላት  የሚችሉ ከህዳሴው ግድብ በተጨማሪ ሶስት ታላላቅ  የሀይል ምንጭ ግድቦችን በመገንባትና እንዲሁም ሌሎች ሊተኩ የሚችሉ  የተፈጥሮ የሀይል አማራጮችን ጭምር  ተጠቅማ  ወደ 10320 ሜጋ ዋት  ከፍ በማድረግ አስተማማኝ የሀይል ክምችትን ለመገንባት አቅዳለች ይለናል  ድረ -ገፁ   CIA።


ድረ-ገፁ ኢትዮጵያ ከሁሉም  ጎረቤቶቿ ጋር መልካም የሚባል የንግድ ትስስር ለመፍጠር  በመስመር ግንባታው ዘርፍ  ማለትም ኢሌክትሪካል ሲስተም የተገጠመለት የባቡር ሀዲድ መስመርን በመገንባት ባለችበት የቀጠናው ዞን ተስፋ የሚጣልበት ኢኮኖሚያዊ አማራጭ ሊፈጥርላት ይችላል ሲል ይጠቅሳል።  ለዚህ ደግሞ በመጠናቀቅ ላይ ያለው ኢትዮ-ጅቡቲ  የባቡር ሀዲድ ኢትዮጵያ በባቡር መስመር ግንባታ ላይ  ያላትን  ቁርጠኝነት በደንብ ያሳያል የሚለን ድረ-ገፁ እናም ኢትዮጵያ ከሁሉም ጎረቤቶቿ  ጋር ለመገናኘት ወደ ፊት ወደ ጎረቤቶቿ የምትገነባቸው የባቡር መስመሮችም ከዚሁ ከኢትዮ-ጅቡቲ መስመር ጋር  እንዲጣመሩ በማድረግ  በቀጠናው ዞን የረባ የገበያ ትስስር በመፍጠር የንግድ ግንኙነቱን ማሳለጥ ብቻም ሳይሆን ማህበራዊ መስተጋብርን  የባህል ልውውጥን ጨምሮ ጥሩ የሚባል ቅርርብና ትውውቅን ይፈጥራል ሲል ያስቀምጣል ድረ ገፁ።


ኢትዮጵያ በኤርፖርት ግንባታና የማስፋፋት ስራዎችም ላይ እቅዷን ለመተግበር ከፍተኛ ትግል እያደረገች መሆኗን ድረ-ገፁ በአይኔ በብረቱ  አረጋግጫለሁ ይለናል። ለምሳሌ   በአመት እስከ 25 ሚሊዮን ደንበኞችን እንዲያስተናገድ በአዲስ አበባ ኤርፖርት እየተገነባ ያለው  ተጨማሪ  የማስፋፊያ ተርሚናል በዚሁ አመት በ2017 ተጠናቆ ደንበኞቹን ለማስተናገድ ክፍት ይሆናል የሚለን ድረ-ገፁ በተጨማሪም ሀገሪቷ  ሌሎች ተጨማሪ 19 የአየር  ጣቢያዎችን /terminals/ በመገንባት የነበረውን 49 የመዳረሻ ክልል   ወደ  68  ከፍ በማድረግ ለመኪና መዳረሻ ምቹ ያልሆኑ ተራራማና በረሀማ ቦታዎች ላይ ጭምር አዳዲስ የሀገር ውስጥ የመዳረሻ ተርሚናሎችን ለመገንባት በአምስት አመቱ እቅዷ መሰረት እየተንቀሳቀሰች ለመሆኗ  ምስክር ነኝ ይለናል ።


እንደሚታወቀው  ኢትዮጵያ ሰንሰለታማ ኮረብታዎች የሚጎረብጧት አገር ብትሆንም  ነገር ግን እስከ አሁን በ100ሺ ኪ.ሜ የሚሰፈሩ መንገዶችን በመገንባት ከዚህ ቀደም በመንገድ ችግር ከእያንዳንዱ የሀገሪቱ የግንኙነት  መረብ  ተነጥለው ለነበሩ ቦታዎች ሀገራዊ ትስስር እንዲኖራቸው መልካም የሚባል  እድሎችን ፈጥራለች።  ሌላው  ኢትዮጵያ  ፍፁም አዲስ የሆነ አለምአቀፋዊ  ኢርፖርት በፈረንጅ በ2025ቱ የአምስት አመት እቅዷ ላይ ይፋ በማድረግ  ግንባታውን ትጅምራለች ሲል CIA በተስፋ ጠብቁ ይለናል።


በዚሁ በያዝነው  ወር አጋማሺ፦ መጋቢት 14/2017 ላይ ደግሞ  https፡//en.m.Wikipedia.org  ድረ-ገፅ CIA WORLD FACTBOOk ን ምንጭ አድርጎ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በየደረጃው፣ በአይነት በአይነቱ በቁጥር አሰላስሎ  በድረ-ገፁ ላይ እንደሚከተለው አቅርቦታል።
ኢትዮጵያ  በ2016   ወደ 67 ነጥብ 43 ቢልዮን ዶላር ጠቅላላ /ኖሚኒያል/ GDP በማስመዝገብ 70ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። በ2014  የ10 ነጥብ 2 በመቶ፥ በ2016 ደግሞ የ6 ነጥብ 5 በመቶ የGDP እድገት እንዲሁም በ2015 ጥናት መሰረት ደግሞ የ10 ነጥብ 1 በመቶ የዋጋ ግዥፈት ተመዝግቦባታል። ሌላኛው  IMF በ2016 ባጠናው መሰረት ይህ አመታዊ GDP  ለ99 ነጥብ 4  ሚልዮን ህዝብ  አመታዊ የነፍስ ወከፍ ገቢ ሆኖ  ሲሰራ 739 ነጥብ 4 ዶላር ወይም  ብር 16 ሺ 266 ብር ከ8 ሳንቲም ይደርሰዋል ይለናል፡፡፡


የአገሪቱ አመታዊ  የGDP እድገት  በየዘርፉ ሲፈተሽ፦   ግብርናው 40 ነጥብ 5 በመቶ በመሸፈን ከፍተኛ ድርሻ ቢኖረውም የአገልግሎት ዘርፉ ደግሞ ከግብርናው በላይ ተራምዶ  43 ነጥብ 3  በመቶ በመሸፈን ለኢኮኖሚው እድገት  ዎሳኝ ሚና ማስመዝገቡን የ2015 ጥናት ያሳያል ። ኢንዱስትሪውም ቢሆን  16 ነጥብ 2 በመቶ በመሸፈን  ጅምሩ ጥሩ በሚባል ደረጃ ተመዝግቧል።
ነገር  ግን በ2014 ጥናት መሰረት 29 ነጥብ 6 በመቶ የሚሆነው  ኢትዮጵያዊ በቀን 1 ነጥብ 90 ዶላር  ወይም  በብር  41 ነጥብ 80 በማግኘት ከድህነት ወለል በታች ኑሮውን የሚገፋ ነው ሲል ጥናቱ ያሳያል።


በ2016 ጥናት መሰረት በሰው ሀይል አቅርቦት ኢትዮጵያችን 50 ነጥብ 97 ሚልዮን በመሽፈን 14ኛ ደረጃ ላይ  ተመዝግባለች። ነገር ግን በስራ  አጥ ቁጥር 17 ነጥብ 50 በመቶ  /እንደ 2012 ጥናት/  በመሸፈን 163ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። በተጨማሪም በ2016 ጥናት መሰረት  ኢትዮጵያ ውስጥ  ስራ /business/  ለመስራት ባለው ምቹ ያልሆነ  የቢሮክራሲ  ውጣ ውረድ ውጥንቅጥ ምክኒያት ሀገሪቱን በ159ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል።


ኢትዮጵያ  የ3 ነጥብ 163  ዶላር ቢልዮን ዶላር  ምርቶቿን፦ቡናን፥ ጫትን፥ ወርቅን፥ የቆዳ  ውጤቶችን፥ ከብቶችን እና የቅባት ምርቶችን  በውጭ ገበያ ትሸጣለች። በተቃራኒው ደግሞ አይሮፕላንና ማሺኖችን፣ ብረታብረቶችን፥ የኤሌክትሪክ ግብአቶችን፥ ነዳጅና ተሽከርካሪዎችን ኬሚካልና የማዳበሪያ ምርቶችን ጭምር  በ15 ነጥብ 87 ቢልዮን ዶላር ከውጭ ገበያ  ትገዛለች።


የኢትዮጵያን ምርቶች በመግዛቱ በኩል  ሲዉትዘርላንድ  14 በመቶ፥ ቻይና 11.7 በመቶ በመሸፈን ቀዳሚ ሲሆኑ አሜሪካ 9 ነጥብ 5 በመቶ ኔዘርላንድ  8 ነጥብ 8 በመቶ ሳውዲአረቢያ 5 ነጥብ 9 በመቶ እና  ጀርመን (2015 ጥናት መሰረት) 5 ነጥብ 7 በመቶ በመሸፈን ከ3 እስከ 6 ያለውን ደረጃ ይዘዋል።


በሌላ በኩል  ደግም ለኢትዮጵያ ምርቶቻቼውን  በማቅረቡ ረገድ  ቻይና 20 ነጥብ 4 በመቶ በመሸፈን በቀዳሚነት ደረጃ ምርቶቿን ለኢትዮጵያ ታቀብላለች። አሜሪካ 9 ነጥብ 2  በመቶ፥ ሳውዲአረቢያ 6 ነጥብ 5 በመቶ እና በ2015 ጥናት መሰረት  ህንድ 4 ነጥብ 5 በመቶ በመሸፈን ከ2 እስከ 4 ያለውን ደረጃ በመሸፈን ተቀምጠዋል።¾

ክፍል የኔ ሃሳብ

በአለም ፖለቲካ ስሟ በስፋት የሚነሳው ኢራን አሁን ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ አለምአቀፍ የሩጫ መድረክ የጎዳና ላይ ሩጫን በማካሔድ የአለምአቀፍ መገናኛ ብዙሀንን ትኩረት አግኝታለች። ሴቶች ከወንዶች ጋር በአንድ ጎዳና እንዳይሮጡ የተከለከለ ቢሆንም የቅጣት አደጋውን ተጋፍጠው የሮጡ መኖራቸው ታውቋል።

በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን አደባባዮች ለመጀመሪያ ጊዜ አለምአቀፍ የማራቶን ሩጫ ባለፈው ቅዳሜ ተካሒዷል። በሩጫው ላይም ኢራናውያንን ጨምሮ ከ40 የተለያዩ የአለማችን ሀገሮች የተውጣጡ 500 ተሳታፊዎች ተካፍለዋል። ከእነሱም መካከል 150 ኢራናውያን ሴቶች 50 ደግሞ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ሴቶች በጥቅሉ 200 ሴቶች ተሳታፊ መሆናቸው ተዘግቧል።

የውድድሩ መድረክ ከማራቶን በተጨማሪ የ10 ኪሎ ሜትር ርቀት ሩጫንም ያካተተ ነበር። የማራቶን ውድድሩ ላይ እንዳይሳተፉና ከአደባባይ ውጪ በሚካሔደው የ10 ኪሎሜትር ሩጫ ላይ እንዲሳተፉ በሀገሪቱ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን በኩል ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸው ነበር። ይሁንና ይህንን ማሳሰቢያ ችላ ብለው በማራቶን ሩጫው ላይ ከወንዶች ጋር በተመሳሳይ ጎዳና የሮጡ ጥቂት ሴቶች መኖራቸውን ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል።

ሴቶች ከወንዶች ጋር በስፖርታዊ መድረኮች ላይ መሳተፍ የለባቸውም የሚል ህግ ባይኖርም በዘልማድ ግን የተከለከለ መሆኑ ነው የሚታወቀው። ቅዳሜ እለትም ከወንዶች ጋር የሮጡ ሴቶች በቀጣይ ምን አይነት ቅጣት ሊጠብቃቸው እንደሚችል የታወቀ ነገር የለም።

የውድድሩ አዘጋጅ የሆኑት ኔዘርላንዳዊው የስራ ፈጠራ ባለቤት ሴባስቲያን ስትራተን እንደተናገሩት የሩጫ መድረኩ ዋነኛ አላማ በቴህራን አደባባዮች የኢራን ወጣቶች ሚሳተፉበት የጎዳና ላይ ሩጫን ለማስተዋወቅና ለማስለመድ ነው።

ክፍል ስፖርት

 

በደራሲ ታሪኩ ካሳሁን የተፃፈው “ከ - እስከ” የተሰኘ የአጫጭር ልቦለድ ስብስብ ተመርቆ ለንባብ በቃ። ስለማህበራዊ ህይወታችን፣ ስለፍቅርና ወጣትነት ስድስት የሚደርሱ ታሪኮችን ይዟል። “ከ - እስከ” የተሰኘው ይህ መፅሐፍ መጋቢት 24 ቀን 2009 ዓ.ም በኒያላ ሆቴል የተመረቀ ሲሆን፤ በ120 ገፆች ተቀንብቦ በ45፡00 ብር ዋጋ ለገበያ መቅረቡም ተጠቅሷል። 

 

በገጣሚና መምህር ሀቢብ ሙሃመድ የተዘጋጀው “የሐበሻ ቁጣ” የተሰኘ የግጥም መድብል ለንባብ በቅቷል። “ህልምና ግጥም እንደፈቺው ነው” የሚለው ገጣሚው፤ ግጥሞቼንም “ሲሳይ ነው!” እያላችሁ ብትፈቱልኝ ትችላላችሁ ይለናል። ሰባ አምስት የሚደርስ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ግጥሞችን የያዘው “የሐበሻ ቁጣ” የተሰኘው መድብል፤ በ95 ገፆች ተዘጋጅቶ በ47፡00 ብር ለገበያ ቀርቧል። 

         . ሞሮኮ የካፍን ድጋፍ አግኝታለች

         . አሜሪካ፣ ሜክሲኮና ካናዳ ተጣምረዋል

 

የዓለምአቀፉ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (ፊፋ) በየአራት አመቱ የሚያካሒደው የአለም ዋንጫ መድረክን ለማስተናገድ አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ ፍላጎት እንዳላት ሰሞኑን ማስታወቋ ይታወቃል። የሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር የአዘጋጅነት ፉክክሩን ብታሸንፍ ውድድሩን በስኬት የማዘጋጀት አቅም እንዳላት የካፍ ፕሬዝዳንት አህመድ አህመድ አረጋግጠዋል።

ኢሳ ሀያቱን በምርጫ አሸንፈው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴደሬሽን ፕሬዝዳንት ከሆኑ ሳምንታት ያስቆጠሩት አህመድ አህመድ ሰሞኑን እንደተናገሩት ሞሮኮ የ2026 የአለም ዋንጫን የማዘጋጀት ሙሉ አቅም አላት። ሀገሪቱ ከሌሎች ሀገሮች ጋር የምታደርገውን ፉክክር እንደታሸንፍም አስፈላጊውን እገዛ እንደሚደረግላት ተናግረዋል።

ሞሮኮ የካፍን ድጋፍ ብቻ ሳይሆን በፊፋው ፕሬዝዳንት ጂዮቫኒ ኢንፋንተኖ በኩልም አዎንታዊ ምላሽ ማግኘት ችላለች። ፕሬዝዳንቱ ሞሮኮ የአለም ዋንጫን ለማዘጋጀት የሚያስችል መሰረተ ልማትና ተቋማዊ አቅም እንዳላት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

ሞሮኮ የዓለም ዋንጫን ለማስተናገድ ዘንድሮ ለአምስተኛ ጊዜ የምታደርገውን ፉክክር እንደምታሸንፍ ተስፋ አድርጋለች። ወድድሩን ለማስናገድ አስፈላጊውን መሰረተ ልማት የምታሟላ ሀገር መሆኗን ብቻ ሳይሆን ለአውሮፓ ሀገሮች ጎረቤትነቷን ትጠቅሳለች።

ከዚህ በፊት ሞሮኮ የ1994፣ 1998፣ 2006 እና የ2010 የአለም ዋንጫን ለማዘጋጀት ተወዳድራ ሳይሳካለት ቀርቷል። የ2010 የአለም ዋንጫ አዘጋጅነት ደቡብ አፍሪካ በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ውድድሩ ወደ አፍሪካ አህጉር መምጣቱ ይታወሳል።

በተያያዘ ዜና የ2026 የዓለም ዋንጫን ለማዘጋጀት አሜሪካ፣ ሜክሲኮና ካናዳ መጣመራቸውን ይፋ አድርገዋል። ሶስቱ የሰሜን አሜሪካ ሀገሮች የአለም ዋንጫን የማስተናገድ እቅዳቸው በገንዘብ በኩል ታይቶ የማይታወቅ ጥቅም እንደሚኖረውም አስታውቀዋል።

የ2026 የዓለም ዋንጫን ለማስተናገድ ጥያቄ የማቅረቡ ሒደት የተጀመረ ሲሆን፤ ሶስቱ የሰሜን አሜሪካ ሀገሮች አስቀድመው ጥያቄ ካቀረቡት መካከል ተጠቃሽ ሆነዋል። የአሜሪካን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሱኒል ጉላኒ፣ የሜክሲኮው ዴሲዮ ደ ማሪያ እና የካናዳው ቪካቶር ሞንታጅሊያ ጋር በመሆን ሰኞ እለት በይፋ መግለጫ ሰጥተዋል።

“የ2026 የፊፋን አለም ዋንጫ ወደ አሜሪካ፣ ሜክሲኮና ካናዳ ለማምጣት ጥያቄ ማቅረባችንን ለማሳወቅ እንወዳለን። የአለም ህብረተሰብም ጥያቄያችንን በበጎ እንደሚቀበለው ተስፋ እናደርጋለን” ያሉት የአሜሪካው እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሱኒል ጉላኒ፤ ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቶ የአዘጋጅነት ፉክክሩን ካሸነፉ ፊፋ በታሪኩ ከፍተኛ የሚባለውን ገቢ እንደሚያገኝበትም አስታውቀዋል። 

ክፍል ስፖርት

 

በደራሲ ኃ/ኢየሱስ የኋላ የተፃፈውና “አትሚሽን” የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ልቦለድ መፅሐፍ ባሳለፍነው ሳምንት ለንባብ በቃ። መጽሐፉ የሰውን ልጅ ረጅም ዕድሜ የመኖር ሃሳብ ተንተርሶ የተፃፈ ሲሆን፤ ከገጸ ባህሪያቱ በተጨማሪ ለማጣፈጫነት የተጠቀመባቸው መላ ምቶች መኖራቸውን አስታውቆ፤ ድንቅነሽ (ሉሲን) እንደአንድ ምሳሌ ይጠቅሳል። መፅሐፉ በሰባት ምዕራፎችና በ174 ገፆች ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን፤ ዋጋው 65፡00 ብር መሆኑም ተጠቅሷል።

 

በኢትዮጵያ ዓመታዊውን የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያሳትፉ የሩጫ መድረኮችን በማዘጋጀት ለ16 ዓመታት የቆየው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሳምንቱ መጨረሻ ወደ ደቡብ ሱዳን አቅንቷል። በሀገሪቱ ዋና ከተማም ያዘጋጀው የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ በስኬት መጠናቀቁን አስታወቋል።

ከዚህ በፊት በላይቤሪያና በጋና የሩጫ መድረኮችን በማዘጋጀት ዓለምአቀፍ ተሞክሮ ያለው ሲሆን፤ ባለፈው እሁድ ደግሞ በደቡብ ሱዳን ጁባ ለመጀመሪያ ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በጋራ ያሳተፈ ሩጫን አዘጋጅቷል። በፕሮፌሽናል ሯጮች መካከል የተደረገውን ፉክክር በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያውያን ሲያሸንፉ፤ ኬንያውያን የሁለተኛ ደረጃን አግኝተዋል።

የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫኬርና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ ሀይሌ ገብረስለሴ ጋር ውድድሩን አስጀምረውታል።

በእርስ በእርስ ጦርነትና በርሀብ ህዝቦቿ የሚሰቃዩባት ደቡብ ሱዳን በታሪኳ የመጀመሪያ የሆነ የጎዳና ላይ ሩጫን አስተናግዳለች። የሩጫው ዋነኛ አላማም ሀገሪቱ ለገጠማት ርሀብ ድጋፍ የሚሆን ገቢ ለማሰባሰብ ነው።

በሩጫ መድረኩም የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ ከተለያዩ ተቋማት የተገኘው ገንዘብ መጠን 200ሺህ ዶላር መገኘቱን ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በድረ ገጹ ባሰፈረው መረጃ ላይ አስታውቋል።

“ርሀብና ድህነትን የመዋጊያ ገቢ ማሰባሰቢያ” በሚል መርህ የተዘጋጀው የጁባ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ከአምስት ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ተካፍለውበታል። ከደቡብ ሱዳናውያን በተጨማሪ በጁባ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያንም ተካፋይ እንደነበሩ ታውቋል።

በሴቶች መካከል የተደረገውን ፉክክር ደጊቱ አዝመራው ርቀቱን 33፡45 በማጠናቀቅ ስታሸንፍ፤ ኬንያዊቷ ፑሪቲ ቢዎት በ35፡25 ደቂቃ ሁለተኛ ሆናለች። ሌላዋ ኢትዮጵያዊት ደራርቱ ደበላ በ37፡25   በመግባት ሶስተኛ ደረጃን አግኝታለች።

በወንዶቹም ፉክክር የኢትዮጵያ አትሌት ነው ያሸነፈው። አትሌት ዳዊት ፈቃዱ ርቀቱን 29፡14 በመግባት ያሸነፈ ሲሆን፤ ኬንያዊው ቤንጃሚን ኬምቦይ በ29፡54 ሁለተኛ ሆኗል። ደቡብ ሱዳናዊው ዴቪድ ጎንጂ ርቀቱን በ30፡03 በማጠናቀቅ ሶስተኛ ሆኖ ገብቷል።

በጁባ ታላቁ ሩጫ ዋነኛ አላማ የደቡብ ሱዳን ለገጠማት ርሀብ ገቢ ማስገኛ ቢሆንም የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች የእርስ በእርስ ግንኙነት በማጠናከር በኩልም አስተዋጽኦ እንዳለው ተነግሯል።

ክፍል ስፖርት

 

በጋዜጠኛና ደራሲ ሙሉጌታ አለባቸው የተደረሰው “መሐረቤን ያያችሁ” መፅሐፍ ተመርቆ ለንባብ በቃ።

አጫጭር ትረካዎቹ እርስ በእርስ በቀጫጭን የትረካ መስመር እንደሚገናኙ የገለፀው ፀሐፊው፤ የአዳም ረታን “ሕፃናዊነት” የተባለ ልዩ የአጻጻፍ ስልት መጠቀሙን በመግቢያው አስታውቋል። በተለያዩ ጋዜጦች ላይ መጣጥፎችን፣ የትርጉም ስራዎችን እንዲሁም በሕጽናዊነት ዙሪያ ጥልቅ ትንታኔዎችን ሲያቀርብ የቆየው ደራሲው በተጨማሪም “ይሄን ስልት መጠቀሜ ሕጽናዊነትን የማስቀጠል ደፋር ሙከራዬ ነው” ብሏል። ማሕበራዊ፣ ታሪካዊና ፖለቲካዊ ሀሳቦችን የሚዳስሰው መጽሀፉ፣ መቼቱን በ1980ዎቹ መጨረሻ የኢትዮጵያ ማሕበራዊ ሕይወት ላይ አድርጎ በርካታ ርዕሰ ጉዳዮችን የሚያነሳ አስራ ሁለት ትረካዎችን ያካተተ ሲሆን በ215 ገፆች ተዘጋጅቷል። 

 

በብራዚሏ ከተማ በተካሔደው የ2016 የኦሊምፒክ ጨዋታዎች መድረክ በሴቶች ማራቶን አሸናፊ የነበረችው ኬንያዊቷ ጀሚማ ሰምጎንግ የተከለከለ አበረታች ንጥረነገር መጠቀሟን የሚገልጽ መረጃ በተደረገላት ምርመራ ውጤት ላይ ተገኝቷል። የአትሌቷ ውጤት መሰረዙ እርግጥ ከሆነም የኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ማሬ ዲባባ እና ትርፊ ጸጋዬ ውጤት ከፍ የሚል ይሆናል።

የ32 አመቷ ሯጭ ጀሚማ ሰምጎንግ በሪዮ ኦሊምክ ማራቶንን ስታሸንፍ በኦሊምፒክ መድረክ በሴቶች ለመጀመሪያ ጊዜ ለኬንያ የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳልያ በማስገኘት ስትወደስ ቆይታለች። ሰሞኑን ግን የተከለከለ አበረታች መድሀኒት መጠቀሟን የሚገልጽ ውጤት እንደተገኘባት የሚገልጸው ዜና ከመውጣቱ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ትችቶችና ዘለፋዎች እየተሰነዘሩባት ነው።

በአትሌቷ ላይ የተገኘው የተከለከለ አበረታች ንጥረነገር ከፍተኛ ሀይል የሚሰጠው ኢፒኦ የተባው ንጥረነገር ነው። በሁለተኛ ደረጃ ምርመራ የሚደረግባት ሲሆን፤ በዚህም ውጤቷ ተመሳሳይ ከሆነ ከውድድር መድረክ የመታገድና ያገኘቻቸውን እውቅናዎች፣ የሜዳልያና የገንዘብ ሽልማቶች እንድትመልስ የሚያደርግ ቅጣት ይጣልባታል።

አትሌቷ ከሪዮ ኦሊምፒክ በፊት የለንደን ማራቶንን ማሸነፍ የቻለች ሲሆን፤ ዘንድሮም በውድድሩ መድረክ ለአሸናፊነት የምትጠበቅ ነበረች። ይሁንና የዶፒንግ ምርመራ ውጤቷ ይፋ መሆኑን ተከትሎ የለንደን ማራቶን አዘጋጆች በሰጡት መግለጫ አትሌቷ እንደማትወዳደር አስታውቀዋል። ባለፈው አመት አሸናፊ በመሆኗ ያገኘችውን የ200ሺ ዶላር ሽልማት እንድትመልስ ህጋዊ አካሔድ እንደሚከተሉም ገልጸዋል።

በሪዮ ኦሊምፒክ በማራቶን ፉክክር ኬንያ በወንዶች በኡውድ ኪፕቾጌ፤ በሴቶች በጀሜማ ሰምጎንግ የወርቅ ሜዳልያዎችን መውሰዷ ይታወሳል። በሴቶቹ ፉክክክር ጀሚማ ሰምጎንገ በመከተል ለባህሬን የምትሮጠው ትውልደ ኬንያዊቷ ኢዩንስ ጄፕኪሩ ሁለተኛ ሆና ስትገባ፤ ኢትዮጵያውያኑ ማሬ ዲባባ እና ቲርፊ ጸጋዬ ሶስተኛና አራተኛ ደረጃን ይዘው መግባታቸው ይታወሳል።

ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ የተከለከለ አበረታች ንጥረነገር መጠቀማቸው የተረጋገጠባቸው ኬንያውያን አትሌቶች ቁጥር ከ40 በላይ ነው። ባለፈው አመት የአራት አመት ቅጣት ከተጣለባት ከማራቶን ሯጯ ሪታ ጄፕቱ ቀጥሎም በዶፒንግ በመከሰስ ጀሚማ ሰምጎንግ የመጀመሪያዋ  ስመ ጥር አትሌት ናት። 

ክፍል ስፖርት
Wednesday, 12 April 2017 12:18

“ተፈፀመ” በሉን!!!

 

ትንሽ ቤት ሰራሁ እንዳቅመኛ

 ሁለት ሶስት ሰው የሚያስተኛ

አላስገባ አለች እሷም ጠባ

ሰው በሰው ላይ እየገባ።

     (ከአርቲስት ቴዎድሮስ ታደሰ “ዘለሰኛ” የተወሰደ)

እንኳን ለፋሲካ በዓል አደረሳችሁ!!!. . . የበዓሉ ሽር-ጉድ እንዴት ይዟችኋል?. . . መቼም የፋሲካ በዓል በህዝበ ክርስትያኑ ዘንድ ብዙ ትርጉም አለው። ከውርስ ኃጢያታችን ይቅር የተባልንበት፤ ክርስቶስ በሞቱ ሞታችንን ድል የነሳበት፤ የኃጢያት ዘመናችንን ሁሉ በቃችሁ የተባልንበትና ነገራችን የተፈፀመበት ወቅት ነው።. . . የክርስትና መስረት የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዓለም የመጣበትን ተልዕኮ ሁሉ እንደተናገረው ፈፅሟል።

መፅሐፍ ቅዱስ የክርስቶስ መከራ መቀበልና ፍፃሜ በተመለከተ እንዲህ ይላል፤ “ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉ እንደተፈፀመ አውቆ የመፅሐፉ ቃል ይፈፀም ዘንድ ተጠማሁ አለ፡፤ በዚያም ሆምጣጤ የሞላበት ዕቃ ተቀምጦ ነበር፤ እነርሱም ሆምጣጤውን በስፍነግ ሞልተው በሁሶፕም አድገው ወደ አፉ አቀረቡለት። ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ “ተፈፀመ” አለ። ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ። (ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 19÷18-20)

ይህ የክርስቶስ ተግባር በህይወታችን በእጅጉ ሊገለጥ የሚገባው ነው። ሂደቱ መራራም ቢሆን በቃሉ መሰረት ህይወቱን ለኛ አሳልፎ በመስጠት “ተፈፀመ” ብሎናል። .  . . እኛ ግን ይህው ከዘመናት በኋላም ቢሆን ሊፈፀሙ የሚገባቸው ብዙ እቅዶችን በእንጥልጥል ወይም በጅምር አስቀርተን “ተፈፀመ” የሚለንን እንናፍቃለን። እናም በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮቻችን ዙሪያ “ተፈፀመ” የሚለን ተቋም እንፈልጋለን። ተደጋግመው የሚሰሙ የመልካም አስተዳደና የፍትህ ችግሮች አሉብን፤ አቤት ባልነው ልክ ሰምቶ ችግሮቻችን “ተፈፀመ” የሚለን አመራር እንፈልጋለን። ብዙ አይነት በሽታዎች አሉብን። ከምርመራ፣ ከመርፌና ከመድሃኒት በኋላ (ብዙ ገንዘባችንን ወስዶብን ቢሆንም እንኳን) የህመማችንን  ነገር “ተፈፀመ” “ከህመማችሁ ተፈውሳችሁ” የሚለን ሀኪምና የህክምና ተቋማት እንፈልጋለን። ይቅር ባይነትንና መቻቻልን የሚያሳውቁ የሃይማኖት አባቶችና ተቋማት እንፈልጋለን። ያኔ የግጭት መንገዳችን ሳይረዝም “ተፈፀመ” የምንልበት ጊዜ ይመጣል። . . . እናላችሁ እንደ ኢየሱስ ነፍስን እስከመስጠት ባይደርስ እንኳን ቃል የተገቡልን የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅዶች በተግባር መሬት ወርደው ችግሮቻችንን “በቃችሁ” የሚለን እንፈልጋለን።

እኛው ራሳችን ተጋግዘን ይህን ክፉ ጊዜ ማለፍ እስካልቻልን ድረስ የባሰው ይመጣና ለሁላችንም የማይጥም፤ ለሁላችንም የማይመጥን ህይወት ሊገጥመን ይችላል። በግፍ የተጫነው ሁሉ ሲወርድ ገፈቱ ለናንተም ነውና።. . . እናም “ፋሲካውን” ምክንያት አድርገን አንድዬ “ተፈፀመ” እንዲለን ሁሉ እኛም እርስ በእርሳችን ክፋትና ተንኮል፣ ቂምና በቀልን “በቃን” ብንባባል ምን ይለናል ጎበዝ!?

ይህቺን ታሪክ የምታጎላ አንዲት ወግ ከኤዞፕ ተረቶች መካከል የምትከተለዋን እንመዛለን።. . . በአንድ ሀገር የሚኖር ከበርቴ ነጋዴ ነበር። እሱም አንድ ፈረስና አህያ ነበሩት። በሁለቱም እንስሳት እየጫነም ይገለገል ነበር። ሆኖም ብዙ ብጭናቸው ብዙ አገኛለሁ በማለት ከባድ ዕቃ ይጭናቸዋል። ወጪ ለመቀነስ ሲልም በቂ ጥራጥሬ በማቅረብ ፈንታ ወደሜዳ ወስዶ ሳር እንዲመገቡ ያደርጋቸዋል።

ከዕለታት አንድ ቀን ከአቅም በላይ ጭኗቸው ወደገበያ ሄደ። አህያውና ፈረሱ በሜዳው ላይ ያለምንም ችግር ተጓዙ። መንገዱ ዳገትና ቁልቁለት እንዲሁም ኮረኮንች ሲሆን ግን በተለይ አህያው ደከመ። መሄድ ሳያቅተውም ወደፈረሱ ጠጋ አለና ከጭነቱ ትንሽ ወስዶ እንዲያግዘው ጠየቀው። ፈረሱ ግን፣ “ትቀልዳለህ እንዴ ለራሴ ከብዶኛል አንተ ደግሞ አግዙኝ ትላለህ። እባክህ ራስህን ቻል” ሲል መለሰለት።

አህያው እንደገና “በእርግጥ የተሸከምከው ዕቃ ከባድ ነው። ነገር ግን እንደኔ አልከበደህም። ከኔ ትንሽ ወስደህ ብታግዘኝ ደግሞ እንደኔ አትደክምም” ሲል ለመነው። ፈረሱ ግን በጭራሽ አይሆንም አለ። ነጋዴውም ቢሆን አህያው መድከሙን እያየ አልረዳውም። እንዲያውም ወደፊት እንዲሄድ እየመታ ገፈተረው። በመጨረሻም አህያው ተደናቀፈና ወደቀ። ከወደቀበት ሳይነሳ ቀረ፤ ሞተ።

ባለአህያው በጣም ተናደደ። ነገር ግን ምንም ለማድረግ አለመቻሉን ሲረዳ የአህያውን ጭነት አወረደና በፈረሱ ላይ ጫነው። ቆዳውንም ለመሸጥ ገፈፈና ከሁሉም ጭነቶች በላይ ደረበው። ትንሽ አግዘኝ ብሎ ቢለምነው አይሆንም ብሎ ሁሉንም በመጫኑና ከዚያም በላይ እርጥብ ቆዳው የተጨመረበት ፈረስ፣ “ይበለኝ ዋጋዬን ነው ያገኘሁት። በመጀመሪያ ሲደክም ትንሽ ወስጄ ባግዘው ኖሮ እሱም አይሞትም። እኔም የሱን ሸክም በሙሉ አልጫንም ነበር” እያለ በፀፀት ተጓዘ ይባላል። . . . እናላችሁ ጎበዝ ኑሮ አድክሞናልና ብንተጋገዝ ምን ይለናል?. . .

እናም የኑሮ ክብደት እያንገዳገደን ነውና ከልብ በላይ ተጨነናልና ብንተጋገዝ መልካም ነው። ፈጣሪ ኃጢያታችንን “በቃችሁ” እንዳለን፤ መከራችሁም “ተፈፀመ” እንዳለን ሁሉ በመልካም አስተዳደርና በሥነ-ምግባር ጉድለት ምክንያት ተጀምረው ያልተፈፀሙ ፕሮጀክቶችን ሸክሙ የከበደብንን ኑሮ ፈፅሙልንና በማቅለል “ተፈፀመ!!!” በሉን። መልካም የትንሳኤ በዓል፤ ቸር እንሰንብት!!!

Page 1 of 4

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • Advertt11.jpg
  • Advertt22.jpg
  • Advverttt.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 129 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us