የግብፅ የውጭ ብድር 53 ቢሊዮን ዶላር ደረሰ

Wednesday, 24 August 2016 13:59

አህራም ኦንላይን ባሰራጨው ዘገባ በአሁኑ ሰዓት የግብፅ የውጭ ብድር 52 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። የግብፅን ማዕከላዊ ባንክ ምንጭ ያደረገው ይኸው ዘገባ በ2015 የሀገሪቱ የውጭ ብድር 48 ቢሊዮን ዶላር የነበረ መሆኑን አሳታውሷል። እንደ ዘገባው ከሆነ መንግስት አሁንም ቢሆን ከአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ተጨማሪ 12 ቢሊዮን ዶላር የሚፈልግ መሆኑ ተመልክቷል

ከአዲሱ የግብፅ የብድር ጥያቄ ጋር በተያያዘ ማብራሪያ የሰጡት የአለም አቀፉ ገንዘብ ድርጅት ቃል አቀባይ ዊሊያም ሙሪ የገንዘብ ድርጅቱ ለግብፅ የሚለቀው ገንዘብ የገንዘብ ድርጅቱ በሚያደርገው ጥናትና ግብፅ በምታካሂዳቸው የለውጥ ፕሮግራሞች ይወሰናል።

በዚሁ ዙሪያ ማብራሪያ የሰጡት የግብፅ የገንዘብ ሚኒስትር አመር ኤልጋህሪ የገንዘብ ድርጅቱ ለግብፅ በሚለቀው የብድር ገንዘብ ላይ የሁለትዮሽ ውይይት በመካሄድ ላይ ነው። ግብፅ አሁን ያለባት ከፍተኛ የብድር ጫና በቀጣይ የመበደር አቅሟን ሊያወርደው ይችላል የሚል ስጋትም አለ።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
419 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us