ሀበሻ ዊክሊ አዳዲስ ፕሮግራሞቹን አስተዋወቀ

Wednesday, 31 August 2016 12:08

 

በተለያዩ የንግድ ትርኢትና ባዛር ዝግጅቶቹ የሚታወቀው ሀበሻ ዊክሊ ፕሮሞሽን በመጪው ዓመት ሊያከናውናቸው ያሰባቸውን አዳዲስ ፕሮጀክቶች ይፋ አደረገ። ይህ የተገለፀው የሀበሻ ዊክሊ የስራ ኃላፊዎች ባሳለፍነው ረቡዕ ነሐሴ 18 ቀን 2008 ዓ.ም በሳሮማሪያ ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ነው። ይህ የተገለፀው ሀበሻ ዊክሊ ሊተገብራቸው የተዘጋጀባቸው አዳዲስ ፕሮጀክቶች መካከል በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚዘጋጀው “የአፍሪካ ኢንተርናሽናል ማኑፋክቸሪንግ ኤክስፓና ኮንፈረንስ”፤ የመዝናኛና የመረጃ ፕሮግራችን የያዘው “ሀበሻ ዊክሊ ሚዲያ ስምንት ማዕዘን” እና ከህዳር 17 ቀን እስከ ታህሳስ 2 ቀን 2009 ዓ.ም በሀረር ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚከናወነውን የ11ኛው የኢትዮጵያ ብሔራር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን የልማት ኤግዚቢሽን የንግድ ትርኢትና ባዛር” ይጠቀሳሉ።

በሚሊኒየም አዳራሽ ከጥር 15 እስከ 17 ቀን 2009 ዓ.ም በሚካሄደው “የአፍሪካ ኢንተርናሽናል ማኑፋክቸሪንግ ኤክስፖና ኮንፈረንስ” ላይ ለመታደም በአስራ አምስት ሴክተሮች የሚካተቱ ከአፍሪካና ከተቀረው ዓለም የተውጣጡ ተቋማት ይገኛሉ ተብሏል። ከ10ሺህ በላይ ጎብኚዎችም ይታደሙበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ አዘጋጆቹ ተናግረዋል። በዚህም የዘርፉ ባለሙያዎች የልምድ ልውውጥ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ አዘጋጆቹ ተናግረዋል።

የመረጃና የመዝናኛ ፕሮግራሞችን ያቀረቡ “ሀበሻ ዊክሊ ሚዲያ በስምነት ማዕዘን” የተሰኘው ፕሮጀክት ደግሞ ሳምንታዊ የቲቪ ፕሮግራምን፣ የሬዲዮ ፕሮግራምን፣ የተደራጀ የመረጃ ቋት ያለውን “8022” የጥሪ ማዕከልን፤ የድረ-ገፅና የፅሁፍ መልዕክትን ለፈላጊዎች የሚያደርስ ነውም ብለዋል። በእነዚህ የመረጃና የመዝናኛ መለዋወጫ መስመሮች ከሀገሪቱ ውስጥ እስከ ዓለም አቀፍ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ይረዳልም ብለዋል።

በቀጣዩ ዓመት በሚከናወነው የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ በህዳር 17 እስከ ታህሳስ 2 ቀን 2009 ዓ.ም የልማት ኤግዚቪሽን የንግድ ትርኢትና ባዛር መዘጋቱን አዘጋጆቹ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። በፕሮግራሙም ላይ በርካታ ድርጅቶችንና ምርት አቅራቢዎች ይገኛሉ ተብሏል። ለአስራ አምስት ቀናት በሚከናወነው በዚህ የንግድ ትርኢትና ባዛር ላይ የሀገርን ታሪክ በሚያሳይና የአካባቢውን ከተሞችም ተሳታፊ በሚያደርግ መልኩ አዝናኝ ፕሮግራሞች እንደሚዘጋጁ አዘጋጆቹ አስረድተዋል።

ሀበሻ ዊክሊ ከዚህ ቀደም በስኬት ያጠናቀቃቸው “ላቢሲን እና በሀበሻ አዲስ ዓመት ኤክስፒ ዝግጅቶቹ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ህዝብ እንደጎበኘው አዘጋጆቹ አስታውሰዋል።     

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
453 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us