ሰለስት ሆቴል ተመርቆ ስራ ጀመረ

Wednesday, 07 September 2016 13:39

 

የከተማችንን ተመራጭ ሆቴሎች የተቀላቀለው ሰለስት ሆቴል ባሰለፍነው ቅዳሜ ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም በይፋ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ። የህይወት ኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርጅት እህት ኩባንያ የሆነው ይህ ሆቴል በ436 ካሬ ሜትር ላይ ተገንብቶ አጠቃላይ ካፒታሉ 48 ሚሊዮን ብር ሲሆን፤ ተገንብቶ ለመጠናቀቅም 3 ዓመት ወስዶበታል ሲሉ የሆቴሉ ስራ አስኪያጅ ወ/ት ኤደን ሙሉወርቅ ተናግረዋሰል።

ባለ አራት ወለል የሆነው ይህ ሆቴል የሚገኘው ወሎሰፈር አካባቢ ሲሆን፤ አስራ ዘጠኝ ምቹ የመኝታ ክፍሎችና ድምጽ ወደውስጥ የማያስገቡ ክፍሎች እንዳሉት ተነግሯል። ለስብሰባ የሚሆንና 70 ሰዎችን የሚያስተናግድ አዳራሽ ያለው ነው ተብሏል።

ስለስት ሆቴል ሶሊድ ቢሮች፣ ድምጽ የማያስገቡ ክፍሎ፣ የሀገራችንን ባህልና ቅርስ በሚያንጸባርቁ ምስሎች ተዋበ ሲሆን፤ ከኤርፖት የሚወስደው ጊዜ አምስት ደቂቃ መሆኑ ለእንግዶች ተመራጭ ያደርገዋል ተብሏል። በአሁኑ ወቅት ለ60 ሰዎች ቋሚ የስራ እድልን መፍጠሩንም ስራ አስኪያጇ ተናግረዋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
767 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us