ወደ ኢንዱስትሪው ዘርፍ ለመግባት ጥረት እያደረገ ያለው በጎ አድራጎት ድርጅት

Wednesday, 28 December 2016 13:50

 

ለችግረኛ ተማሪዎች የዩኒፎርም ድጋፍ በማድረግ ዓመታትን ያሳለፈው ራዕይ ለትውልድ ሀገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት እስከ ዛሬ ድረስ ከኢትዮጵያውያን ገንዘብን አሰባስቦ ለችግረኛ ተማሪዎች ዩኒፎርም ገዝቶ ሲያድል የቆየ ሲሆን በቀጣይ ግን የልብስ ፋብሪካን በመገንባት ስራውን በአስተማማኝነት ለማከናወን እንቅስቃሴ የተጀመረ መሆኑን አሳታውቋል።

የልብስ ፋብሪካውን ለመገንባት የታቀደው በኦሮሚያ ክልል አዲስ አበባ ዙሪያ  ከመንግስት በሚገኝ አስር ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ መሆኑንየራዕይ ለትውልድ መስራችና ቦርድ ሰብሳቢአቶ ያሬድ ግርማ አስታውቀዋል። ግንባታውን በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥም ለማጠናቀቅ ታስቧል። ግንባታውን በማከናውኑ ሂደትም የተለያዩ ድርጅቶች እገዛ ለማድረግ ቃል የገቡ መሆኑ ተመልክቷል። “ማሽነሪ ቃል ተገብቶልናል፤ ሲሚኒቶ አግኝተናል፤ ጥናትና የማማከሩን ስራ የሚሰራልን ድርጅትም አግኝተናል”። ያሉት ኃላፊው፤ የልብስ ስፌቱ ፋብሪካ ሰራተኞች የሚሆኑትም የአስር ሺህ የችግረኛ ተማሪዎች እናቶች መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ሰራተኞቹንም ለማሰልጠን የኢፌድሪ መከላከያ ቃል የገባ መሆኑ ታውቋል።  ሲሚንቶ ለማቅረብም ደርባ ሚድሮክ ቃል የገባ መሆኑ አቶ ያሬድ ጨምረው ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም እገዛ እያደረገ ሲሆን ቁርስ ሳይበሉ ትምህርት ቤት እየሄዱ ተዝለፍልፈው እስከ መውደቅ የደረሱ ተማሪዎች እዚያው ትምህርት ቤት ቁርስ እንዲያገኙ በማድረጉ ረገድ ከራዕይ ለተውልድ ጋር የኢትዮጵያ አየር መንገድም እየሰራ መሆኑ ታውቋል። ፕሮጀክቱ ይፋ በሆነበት ባሳለፍነው ሀሙስ በተለያዩ ጊዜያት ለድርጅቱ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ ታዋቂ ሰዎችም የድርጅቱን አምባሳደር እንዲሆኑ ተደርጓል።

 ፋብሪካው ተገንብቶ ወደ ስራ ሲገባ ለችግረኛ ተማሪዎች በነፃ የደንብ ልብስ ከማቅረብ በተጨማሪ ትርፍ የተማሪዎችንም ዩኒፎርም ለገበያ በማቅረብ የድርጅቱን የልገሳ አድማስ ለማስፋትና አስተማማኝ ለማድረግ ጥረት የሚደረግ መሆኑን አቶ ያሬድ አመልክተዋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
414 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us