የሱዳን የኢኮኖሚ ግሽበት እየተባባሰ ነው

Wednesday, 19 April 2017 12:27

 

ሱዳን በከፍተኛ የኢኮኖሚ ግሽበት ውስጥ ከገባች በርከት ያሉ ዓመታት የተቆጠሩ ሲሆን በዘንድሮው የፈረንጆች ዓመትም ይህ ግሽበት ተባብሶ መቀጠሉን የሰሞኑ የሱዳን ትሪብዩን ዘገባ አመልክቷል።


እንደ ዘገባው ከሆነ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት የካቲት ወር የነበረው የግሽበት መጠን 33 ነጥብ 53 የነበረ ሲሆን በያዝነው ወር ይህ አሃዝ ወደ 34 ነጥብ 68 ከፍ ብሏል። ለዚሁ ግሽበት መባባስ አይነተኛውን ሚና የተጫወቱት የምግብና የነዳጅ ምርቶች መሆናቸውን የሱዳንን ስታትስቲክስ ቢሮን ዋቢ ያደረገው ይሄው ዘገባ አመልክቷል። የሱዳን መንግስት አሁን ለገጠመው የኢኮኖሚ ግሽበት መፍትሄ ለመስጠት ገንዘብ ነክና ገንዘብ ነክ ያልሆኑ እርምጃዎቹን በመውሰድ ላይ ሲሆን በተለይ ከዓመታት በፊት በአሜሪካ የተጣለበትን ማዕቀብ ለማስነሳት የተቻለውን ሁሉ በማድረግ ላይ መሆኑን ዘገባዎች ያመለክታሉ።


ሀገሪቱ የገጠማት የኢኮኖሚ ፈተና እየተባባሰ በመሄዱ ከግሽበቱ ባሻገር የባጀት ጉድለት መስፋት እንደዚሁም የውጭ ምንዛሪ እጥረትም ጭምር እያጋጠማት ነው።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
314 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ ፀጋው መላኩ

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us