ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ 16ኛውን መልቲ ዲሲፕሊነሪ የጥናት ኮንፍረንስ አካሄደ

Wednesday, 21 June 2017 13:31

 

ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ 16ኛውን መልቲ ዲሲፕሊነሪ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ ከሰኔ ሰኔ 9 እና 10 ቀን 2009 ዓ.ም  ሳርቤት አካባቢ በሚገኛው የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ዋና መ/ቤት አዳራሽ አካሂዷል። በዚሁ ዓመታዊ ኮንፍረንስ ላይ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ እህት ኩባንያ የሆነው ዩኒቲ ዩኒቨርስቲን ጨምሮ የተለያዩ መንግስታዊ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተሳታፊ ሆነዋል። በኮንፍረንሱም ላይ በርካታ የተለያዩ የጥናት ወረቀቶች ቀርበው ጥልቀት ያለው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

 

ከቀረቡት የጥናት ወረቀቶች መካከል የአዲስ አበባ መንገድና ትራፊክ አደጋ እያስከተለ ስላለው የጤና፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የሚዳስሰው ጥናት ይገኝበታል። ከዚህም በተጨማሪ በግብርናው፣ በጤናው፣ በኢንቨስትመንቱና በፋይናንሱ ዘርፍ ዙሪያ ያጠነጠኑ የጥናት ወረቀቶችም በኮንፍረንሱ ላይ ቀርበዋል።

 

 በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሲኢኦና የዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር አረጋ ይርዳው፤ ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ላለፉት 16 ተከታታይ ዓመታት አንድም ጊዜ ሳያቋርጥ ዓመታዊ የጥናት ኮንፍረንሱን ጊዜውን ጠብቆ ሲያካሂድ የነበረ መሆኑን አመልክተዋል።  ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ በኮንፍረንሱ ላይ የቀረቡትን የጥናት ወረቀቶች ለህትመት በማብቃት ለሚመለከታቸው አካላት በማሰራጨት መሬት ወርደው ስራ ላይ የሚውሉበት ሁኔታ እንዲኖር ቀጣይ ስራዎችንም የሚሰራ መሆኑንም ዶክተር አረጋ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቆይታ ጨምረው አመልክተዋል።

 

በኮንፍረንሱ ቅድመ ዝግጅት ወቅት የመንግስትም ሆነ የግል ዩኒቨርስቲዎች በኮንፍረንሱ በተለያዩ ጥናቶችን እንዲያቀርቡ የግብዣ ጥሪ የሚደረግላቸው መሆኑን ያመለከቱት ፕሬዝዳንቱ፤ በርካታ የጥናት ወረቀቶች ከቀረቡ በኋላ ዓመታዊ የጥናት ኮንፍረንሱን ይመጥናሉ ተብለው የተለዩት የጥናት ወረቀቶች እንዲመረጡ ተደርጎ ከእነዚህም ውስጥ የተወሰኑት ለኮንፍረንሱ መድረክ የሚበቁ መሆኑን ገልፀዋል። ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ እንደዚሁም በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት በመስጠት ላይ ይገኛል።

 

 በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ከሚሰጥባቸው ዘርፎች መካከል ጤና፣ኮምፒዩተር ሳይንስ፣ ግብርና እና የተለያዩ የኢንጂነሪግ ፕሮግራሞች ይገኙበታል። ዩኒቨርሲቲው በቢዝነስ፣ በሊደርሺፕ፣ በኢኮኖሚክስ በአካውንቲግና በፋይናንስ ዘርፎች የመጀመሪያ ዲግሪ እንደዚሁም የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን የትምህርት ጥራቱንም ከስር ጀምሮ ለማስጠበቅ ከመዋዕለ ህፃናት ጀምሮ እስከ ዩኒቨርስቲ ድረስ የተዘረጋ ትምህርትን በመስጠት ላይ ይገኛል።  

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
362 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 880 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us