ዘመናዊ የታክሲ መጥሪያ የተገጠመላቸው 43 አቫንዛዎች ወደስራ ገቡ

Wednesday, 09 August 2017 12:26

 

የትራንስፖርት አገልግሎቱን ማቀላጠፍ የማያስችል የስልክና የርቀት መጠቆሚያ መሣሪያ የተገጠመላቸው 43 ዘመናዊ አቫንዛ ታክሲዎች ስራ ጀመሩ። የታሲን አገልግሎት በማቀላጠፍ ረገድ ከሚሰራው ኢታ (ኢትዮጵያ ታክሲ) ድርጅት ጋር ተባብሮ ለመስራት ተስማምቶ ወደገበያው የገባው ኮንፈርት ሳሎን ሜትር አውቶሞቢል ታክሲ ማህብ ባሳለፍነው ቅዳሜ ሐምሌ 29 ቀን 2009 ዓ.ም ታክሲዎችን ከሞይንኮ ኩባንያ ተረክቧል።

ከዚህ ቀደም ለሶስት የታክሲ ማህበራት በመንግስት በፈቀደው ከቀረጥ ነፃ የሚገቡ ታክሲዎችን አስመጥቶ ያስረከበው ሞይንኮ በተመሣሣይ ከኮንፈርት ሳሎን ሜትር አውቶሞቢል ታክሲ ማህበር ጋር የተሳካ ስራ መስራቱ እንደሚያስደስታቸው የተናገሩት የኩባንያው የጨረታና ሽያጭ ክፍል ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ሰይፉ ናቸው። ሞይንኮ ኩባያ ከአሁን ቀደም ለግሬይ ታክሲ ማህበር 35፤ ለቲዮ የታክሲ ማህበር 35 እንዲሁም ለቦሌ ኤርፖርት እና ሆቴል ታክሲ ማህበር 79 ታክሲዎችን አስመጥቶ ማስረከቡ ተገልጿል። በዕለቱ የተረከቡት ታክሲዎችን ጨምሮ ሁሉም ታክሲዎች “ቲዮታ አቫንዛ” የሚባሉ መሆናቸውን እና በአንድ ጊዜ ሰባት ያህል ሰዎችን ማስተናገድ እንደሚችሉም ተነግሯል። ታክሲዎቹ አውቶማቲክ ማርሽ፣ የአቅጣጫ መጠቆሚያ እና ሜትር ማሽን የተገጠመላቸው ዘመናዊ ተሽከርካዎች መሆናቸውንም ሰምተናል።

ከስድስት ወራት በኋላ 43 ታክሲዎችን የተረከበው ኮንፈርት ሳሎን ሜትር አውቶሞቢል ታክሲ ማህበር በበኩሉ፤ ከቀረጥ ነፃ ታክሲን ለማስገባት በ2008 ዓ.ም ከተመዘገቡት 26 የታክሲ ማህበራት አንዱ መሆኑን የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሐንስ ባልቻ አስታውሰዋል። እስካሁንም የቆዩት “ቶዮታ አቫንዛ” ታክሲዎችን በመምረጣቸው እንደሆነ አስታውቀው፤ 70 በመቶ የሚሆነውን ገንዘብ ብርሃን ባንክ ዝቅተኛ በሚባል የብድር ማመቻቸቱንም ተናግረዋል። ብድሩ የሚመለሰው በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሲሆን፤ ከቀረጥ ነፃ የገባው የአንዱ መኪና ሂሳብም 485 ሺህ ብር እንዲሆነም ሰምተናል።

በአጠቃላይ ሞይንኮ ኩባንያ ለሚያስመጣቸው ተሽከርካሪዎች የሶስት ዓመት ዋስትና እና የ100 ሺህ ኪሎ ሜትር የዋስትና አገልግሎት መኖሩን የጠቀሱት አቶ ሙሉጌታ በበኩላቸው፤ ሞይንኮ ወደሀገር ውስጥ ለሚገቡ ማንኛውም አይነት የቶዮታ ተሸከርካሪዎች ሙሉ የመለዋወጫ አቅርቦት እንሰጣን ብለዋል።

ኮንፈርት ሳሎን ሜትር አውቶሞቢል ታክሲ ማህበር የተቀበላቸው 43 አቫንዛ ታክሲዎች ካሳለፍነው ሰኞ ጀምሮ ወደስራ መግባታቸው ይፋ የሆነ ሲሆን፤ ከኢታ (ETTA) ጋር በተስማማው የቴክኖሎጂ አሰራር መሠረት ከመነሻው 30 ብር ሆኖ በእያንዳንዱ ኪሎ ሜትር የ13 ብር ዋጋን እያስከፈለ አገልግሎቱን እንደሚሰጥም ተነግሯል።

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
272 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1019 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us