አድማስ ዩኒቨርስቲ ከ4 ሺ 5 መቶ በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ

Wednesday, 09 August 2017 12:30

 

አድማስ ዩኒቨርስቲ ባለፈው ቅዳሜ በኤግዚብሽን ማዕከል ከ4 ሺህ 6 መቶ በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ። ከምሩቃኑ መካከልም 1 ሺህ 2 መቶ 96 የሚሆኑት  በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ትምህርታቸውን በዲግሪ መርሀ ግብር ያጠናቀቁ ናቸው። ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን በዲግሪ መርሀ ግብር ተከታትለው የተመረቁት በአካውንቲግ፣በማኔጅመንት፣ በማርኬቲግ ማኔጅመንት፣ በኮምፒዩተር ሳይንስና በሆቴል ማኔጅመንት ነው። በሆቴል ማኔጅመንት የዚህ የ2009 ምሩቃን በዩኒቨርስቲው ታሪክ የመጀመሪያዎቹ ናቸው ተብሏል።

 

ከዲግሪ መርሃ ግብሩ ባሻገር ቀሪዎቹ 3 ሺህ 224 የሚሆኑት ተመራቂዎች ደግሞ ከ20 በላይ በሚሆኑ የቴክኒክና ሙያ ዘርፎች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ መሆናቸው ተመልክቷል። እንደ ዩኒቨርስቲው መረጃ ከሆነ በዚህ ዓመት ለምርቃት ከበቁት ተማሪዎች መካከል 65 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።  አድማስ ዩኒቨርስቲ በሀገር ውስጥ ከሚሰጠው የትምህርት አገልግሎት ባሻገር በሶማሌላንድ እንደዚሁም በፑንትላንድ ጭምር ካምፓሶቹን በመክፈት ትምህርት እየሰጠ መሆኑ ታውቋል። እንደ ዩኒቨርስቲው መረጃ ከሆነ ዩኒቨርስቲው ባሉት ከአስር በላይ ካምፓሶች ከሥልሳ በላይ የርቀት ትምህርት ማዕከላት እስከ ዛሬ ድረስ ከ40 በላይ ሰልጣኞችን አስመርቋል። በዕለቱ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳት ዶክተር ሞላ ፀጋዬ ዩኒቨርስቲው በአሁኑ ሰዓት በሀገር ውስጥና በውጭ ከ20 በላይ ተማሪዎችን በልዩ ልዩ የሙያ ዘርፎች እያሰለጠነ መሆኑን አስታውቀዋል።

 

 ከዚህም በተጨማሪ በዚህ ዓመት በመካኒሳ እንደዚሁም በመቀሌ አዳዲስ ካምፓሶችንም በመክፈት በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በዲግሪ እንደዚሁም በቴክኒክና ሙያ ዘርፎች ሥልጠና የጀመረ መሆኑ ታውቋል። ይህ ብቻ ሳይሆን በአራት የሥልጠና ዘርፎችም በቅርቡ በማስተርስ ደረጃ ተማሪዎችን ተቀብሎ  ለማስልጠን ዝግጅቱን ያጠናቀቀ መሆኑን ከዩኒቨርስቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
213 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 948 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us