ዳሸን ባንክ ለደንበኞቹ የማበረታቻ ሽልማትን ሰጠ

Wednesday, 16 August 2017 12:06

 

ዳሸን ባንክ ከዓለም አቀፍ የሀዋላ አገልግሎት ጋር በተያያዘ አሸናፊ ለሆኑ እድለኞች በትላንትናው ዕለት በፍሬንድሺፕ ሆቴል በተካሄደ ሥነ ስርዓት በርካታ ሽልማቶችን ሰጠ። በዕለቱም ለእድለኛ ደንበኞች ከቤት መኪና ጀምሮ ፍሪጆች፣ላፕቶፖችና ሶላር ፓኔሎችበሽልማትነትተበርክተዋል። ባንኩ፤ 12 ፍሪጆች፣12 ላፕቶፖች፣24 የሚሆኑ ሶላር ፓኔሎችና አንድ የቤት መኪናን በሽልማት ያበረከተ መሆኑን የባንኩ ማርኬቲግና ኮርፖሬት ኮሙኑኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ አለባቸው አመልክተዋል።

 

ከዚሁ ሥራ ጋር በተያያዘም ባንኩ እስከ 4 ነጥብ5 ሚሊዮን ብር ወጪ ያደረገ መሆኑን ሀላፊው ጨምረው አመልክተዋል። ይህንንም ሽልማት በመጀመሩ ባንኩ ያቀደውን ሃሳብ ያሳካ መሆኑ ተመልክቷል። የባንኩየመኪና ሽልማት እድለኛ የሆኑትከጋምቤላ አቶ ኦኬሎ ካም ናቸው። መኪናዋ ሰባት መቶ ሺብር ዋጋ ያላት መሆኑን አቶሙሉጌታ ካደረጉት ገለፃ መረዳት ችለናል።

ሽልማቱ ለአሸናፊ እድለኞች የተበረከተው ከመጋቢት 18 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 17 ቀን 2009 ዓም ድረስ የቆየውን የሀዋላ ሎተሪ መጠናቀቅ በማስመልከት ነው።

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
203 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us