የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተቀናጀ የበረራ ሥርዓት እንዲኖረው የሚያስችለውን ሥምምነት ተፈራረመ

Wednesday, 13 September 2017 12:05

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተቀናጀ የበረራ ስርዓት እንዲኖረው የሚያስችለውን ቴክኖሎጂ ለማግኘት ሴበር ከተባለ አንድ የአሜሪካ ኩባንያ ጋር ተፈራረመ። በዚህ ስምምነትም መሰረት ኩባንያው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ በርካታ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ማቅረብ ይጠበቅበታል። እንደ ኢትዮጵያ የአየር መንገድ አለም አቀፍ አገልግሎቶች ማኔጂግ ዳይሬክተር አቶ ኢሳያስ ወልደማርያም ገለፃ ከሆነ አየር መንገዱና ሴበር ላለፉት አስራአንድ ዓመታት በጋራ የሰሩ ሲሆን፤ አሁን በታደሰው የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት ሴበር ኩባንያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኦንላይን ትኬት ጀምሮ በርካታ አገልግሎቶችን በዘመናዊ ኢንፎርሜሽን በተደገፈ መልኩ እንዲያገኝ የሚያደርግ ይሆናል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
128 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us