በጨርቃጨርቅ፣ አልባሳትና በኢንዱስትሪው ዙሪያ ትኩረቱን ያደረገ ኤግዚብሽን እየተካሄደ ነው

Wednesday, 04 October 2017 12:25

 

በጨርቃጨርቅ፣ አልባሳትና በኢንዱስትሪው ዙሪያ ትኩረቱን ያደረገው አፍሪካ ሶርሲግና የፋሽን ሳምንት 2017 ኢትዮጵያ ኤግዚብሽን በሚሊኒየም አዳራሽ ተከፈተ። ኤግዚብሽኑ የተከፈተው ረቡዕ መስከረም 23 ቀን 2010 ሲሆን እስከ መስከረም 26ቀን 2010 ዓ.ም ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ የሚቆይ መሆኑ ታውቋል።

   በኤግዚብሽኑ ላይ ልዩ ልዩ ምርቶቻቸውን ይዘው የሚቀርቡ ኩባንያዎች ከ25 ሀገራት በላይ የተውጣጡ መሆናቸው ተመልክቷል። የኤግዚብሽኑ አዘጋጆች ከ 3 ሺህ 5 መቶ በላይ ከዓለም ዙሪያ የሚመጡ ከፍተኛ ተሳታፊዎችን የሚጠብቁ መሆናቸውን አመልክተዋል። ከዚህም በተጨማሪ ኤግዚብሽኑ በኢትዮጵያን በዘርፉ ያለውን የኢንቨስትመንት እምቅ ሀብት ለውጭ ባለሀብቶች ለማስተዋወቅ ብሎም፤ኢትዮጵያዊያን ባለሀብቶች ከውጭ ባለሀብቶች ጋር የቢዝነስ ለቢዝነስ ግንኙነትን ለመፍጠር መልካም አጋጣሚን ይፈጥርላቸዋልም ተብሏል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
81 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us