አዲስ ቢዩልድ ኤግዚብሽን በመጪው አርብ ይከፈታል

Wednesday, 11 October 2017 12:40

 

በየዓመቱ የሚካሄደው አዲስ ቢዩልድ ዓለም አቀፍ ኤግዚብሽን ከጥቅምት 3 እስከ 6 ቀን 2010 ዓ.ም ለስምንተኛ ጊዜ በሚሊየም አዳራሽ የሚካሄድ መሆኑን የኤግዚብሽኑ አዘጋጆች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አመልክተዋል።

በዚሁ ኤግዚብሽን ላይ ከ12 ሀገራት የሚገኙ 125 የሚሆኑ ኩባንያዎች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ የሚጠበቅ መሆኑ ተመልክቷል። በኤግዚብሽኑ ተሳታፊ ይሆናሉ ከተባሉት ሀገራት ኩባንያዎች መካከልም ኢትዮጵያን ጨምሮ ከቱርክ፣ ከጀርመን፣ ከጣሊያን፣ ከህንድ፣ ከቤልጂየም፣ ከቻይና፣ ከቱኒዚያ፣ ከሳዑዲአረቢያ፣ ከተባበሩት አረብ ኤሜሬት፣ ከአሜሪካና ከቡልጋሪያ የመጡ ተሳታፊዎች ይገኙበታል። ኤግዚብሽኑ በዘርፉ ያሉ አገር በቀል ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ መድረክን ይከፍታል ተብሏል። ከዚሁ ጎን ለጎን ከዘርፉ ጋር በተያያዘ የፓናል ውይይት የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል። ዓመታዊው ኤግዚብሽን በቱርክ መንግስት ድጋፍ የሚካሄድ ነው።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
113 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 895 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us