ኢትዮ ቴሌኮም በደንበኞች ቁጥር በአፍሪካ ግዙፉ ኩባንያ ተባለ

Wednesday, 15 November 2017 12:26

 

ኢትዮ ቴሌኮም እ.ኤ.አ በ2017 ዓ.ም መጨረሻ የደንበኞቹ ቁጥር 57 ነጥብ 43 በመድረሱ በአፍሪካ የግዙፍነት ድርሻ መያዙን እንደ መግለጫው ከሆነ ኢትዮ ቴሌኮም በአፍሪካ ግዙፍ ኩባንያ ሊሆን የቻለው የናይጄሪያውን  ኤምቲኤን ቴሌኮም ኩባንያ በመቅደም ነው። የናይጄሪያው ኤምቲኤን ኩባንያ ለረጅም ዓመታት በሞባይል ደንበኞቹ ብዛት በአፍሪካ ትልቁና ቀዳሚው ሆኖ መቆየቱን ይኸው መረጃ ጨምሮ ያመለክታል። ኩባንያው በመግለጫው ከ62 ሚሊዮን በላይ የሞባይል ኔትወርክ፣ ከ21 ኪሎ ሜትር በላይ የኦፕቲካል ፋይበር መስመር፣ ከ3 ሚሊዮን በላይ የመደበኛ መስመር አቅም እንደዚሁም ከ42 ነጥብ 6 በላይ ጂፒኤስ ዓለም አቀፍ ሊንክ  አቅም የፈጠረ መሆኑን አመልክቷል።

ኢትዮ ቴሌኮም አቅሙን ማሳደግ የቻለው በነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር  ባካሄደው የማስፋፊያ ፕሮጀክት ሲሆን ይህም ኩባንያው በአፍሪካ ግዙፍ የቴሌኮም መሰረተ ልማት ባለቤት ያደረገው መሆኑን መረጃው ጨምሮ ያመለክታል።

ኢትዮ ቴሌኮም ባካሄደው ሰፊ የመሰረተ ልማት ግንባታ ሥራ በአፍሪካ ቀዳሚውን ስፍራ መያዙ ይነገር እንጂ በአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት በኩል ግን አሁንም ቢሆን በደንበኞቹ ቅሬታ የሚቀርብበት ኩባንያ ነው።

በኔትወርክ መቆራረጥ፣ በኢንተርኔት አገልግሎት ታሪፍ ውድነትና በመሳሰሉት ያልተቀረፉ ችግሮቹ አሁን ድረስ በደንበኞቹ ተደጋጋሚ ቅሬታዎች ይቀርቡበታል። ኩባንያው ከዚህም በተጨማሪ በቴሌኮም ማጭበርበር በኩል ሀገሪቱ እያጣች ያለውን ገቢ መፍትሄ እንዲያገኝ ማድረግ አልቻለም። በቅርቡ እየወጡ ያሉት መረጃዎች እንደሚያመለከቱት ከሆነ ደግሞ ኩባንያው በገጠመው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ሥራዎቹን በአግባቡ ማከናወን አልቻለም።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
102 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 152 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us