የቻይና የባህር ማዶ የሪል ኢስቴት ከፍተኛ እድገት እያሳየ ነው

Wednesday, 15 November 2017 12:34

 

­­­

በፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ውስጥ የምትገኘው ቻይና በውጪ የሪል እስቴት ግንባታም ከፍተኛ ለውጥ እያስመዘገበች መሆኗን ደይሊ ኔሽን ባሰራጨው ዘገባ አመልክቷል። እንደዘገባው ከሆነ በሪል እስቴት ኢንቨስትመንት የቻይናዊያን አለም አቀፍ የኢንቨስትመንት መጠን 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ደርሷል። በአሁኑ ሰዓት የቻይናዊያን ሪል እስቴት ኩባንያዎች መዳረሻ በመሆን በዋነኝነት የተጠቀሱት እንግሊዝ፣ አሜሪካና አውስትራሊያ ናቸው።

 በከተማ ደረጃም ለንደን፣ ሲድኒ፣ ሎሳንጀለስና ቺካጎ የቻይናዊያን የሪል እስቴት ባለሀብቶች ዋነኛ መዳረሻ መሆናቸውን ይሄው ዘገባ ጨምሮ ያመለክታል። በቻይና የተፈጠረውን የመካከለኛ ገቢ ዜጋ ተከትሎ የመኖሪያ ቤት ፍላጎት በማደጉ በሀገሪቱ በሰፊ የግንባታ ሥራ ውስጥ የነበሩት የቻይና ሪል እስቴት ኩባንያዎች ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ ግን ፊታቸውን ወደ ዓለም አቀፉ ገበያ አዙረዋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
87 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 152 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us