የኮንስትራክሽን የኬሚካል ግብአቶችን የሚያመርት ኩባንያ ወደ ሥራ ገባ

Wednesday, 15 November 2017 12:35

 

ልዩ ልዩ የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን የሚያመርተው የስዊዝ ኩባንያ  የፋብሪካ ግንታውን አጠናቆ ወደ ሥራ ገባ። ሲካ አቢሲኒያ የሚል መጠሪያ ያለው ይሄው የሚያመርተው ኩባንያ የኮንስትራክሽን ግብዓት የሆኑ የኬሚካል ምርቶችን ነው። ፋብሪካው ባሳለፍነው ቅዳሜ ህዳር 2 ቀን 2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍፁም አረጋ በክብር እንግድነት በተገኙበት ተመርቋል። ፋብሪካው የሚገኘው በአለም ገና ሲሆን ሀገሪቱ እስከዛሬ በውጭ ምንዛሪ ከውጭ ታስገባቸው የነበሩትን የተለያዩ የኮንስትራክሽን የኬሚካል ግብዓቶችን ለመተካት ከፍተኛ እገዛ የሚያደርግ መሆኑ ተመልክቷል። ከፋብሪካው ምርቶች መካከል የሲሚንቶ ኮንክሪቶች በቀላሉ ለማድረቅ የሚያስችሉ እንደዚሁም የውሃ ሥርገትን የሚከላከሉ ይገኙበታል።

የምርቶቹ ባለቤት የሆነው ሲካ አቢሲኒያ በቀጣይም የፋብሪካውን የማምረት አቅም በማሳደግ ተጨማሪ የኮንስትራክሽን ኬሚካል ግብዓቶችን ለማምረት እቅድ የያዘ መሆኑ ተመልክቷል። ከዚህም በተጨማሪ ከሀገር ውስጥ አቅርቦቱ ባለፈ ምርቶቹ ወደ ጎረቤት ሀገራት ሳይቀር የመላክ እቅድም ያለው መሆኑን በዕለቱ በኃላፊዎቹ ከተደረገው ገለፃ መረዳት ችለናል። የኩባንያው ባለቤቶችና ኃላፊዎች በኢትዮጵያ ፋብሪካውን ለመክፈት ያነሳሷቸው የተለያዩ ምክንያቶች መኖራቸውን አመልክተዋል።

ከእነዚህም ምክንያቶች መካከል የሀገሪቱ የህዝብ ቁጥር ከፍተኛ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ያለውን የፍላጎት ገበያ ለመጠቀም፣ በሀገሪቱ የኮንስትራክሽኑ ዘርፍ ያለው እድገት ከፍተኛ መሆኑና የሀገሪቱም አጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገት ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ካላቸው ሀገራት ተርታ የሚመደብ መሆኑ ተጠቅሷል።

በእለቱ በምረቃው ሥነስርዓት ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር አቶ ፍፁም አረጋ በበኩላቸው ኩባንያው በኢትዮጵያ የሚያመርታቸው የኮንስትራክሽን ግብዓቶች ሀገሪቱ በዘርፉ እያወጣች ያለውን የውጭ ምንዛሪ በማዳኑ በኩል የሚኖረው ሚና ቀላል አለመሆኑን አመልክተዋል። ከዚህም በተጨማሪ በእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር በኩል የሚኖረው አስዋፅኦም ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

ኩባንያው በኢትዮጵያ የማምረት ሥራውን ከመጀመሩ በፊት ባለፉት አስር ዓመታት በአገናኝ ቢሮዎች እና በአከፋፋዮች አማካይነት ምርቶቹን ለኢትዮጵያ ገበያ ሲያደርስ የነበረ መሆኑን የኩባንያው ዋና ሥራ አስኪያጅ ፔትሬዘር ግሪንዴኑ አመልክተዋል። ኩባንያው ከሚያመርታቸው መካከል አድሚክሲቸር (Admixture) እና ወተርፕሩፊንግ (Waterproofing) የተባሉ የምርት አይነቶች ይገኙበታል። ሲካ በኬሚካል የኮንስትራክሽን ግብአቶች ምርት ከመቶ ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ልምድ ያለው መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።  

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
129 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 142 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us