የግብፅ ህዝብ 104 ሚሊዮን ደረሰ

Wednesday, 22 November 2017 12:00

 

የግብፅ ህዝብ ቆጠራ ሰሞኑን ይፋ የሆነ ሲሆን በዚህም ይፋ በሆነው ቆጠራ መሰረት የሀገሪቱ ህዝብ 104ነጥብ 2 ሚሊዮን መድረሱን የአህራም ኦንላይን ዘገባ አመልክቷል።  በዚህም የቆጠራ ውጤት መሰረት ከ15 እስከ 20 ባለው እድሜ ውስጥ የሚገኙ ግብፃዊያን 18 ነጥብ 2 በመቶውን ይዘዋል።በዚህ ህዝብ ቆጠራ በትዳር ውስጥ ያሉ ግብፃዊያንን ድርሻ 68 በመቶ አድርሶታል። የሀገሪቱ ስታትስቲክስ አጀንሲ የህዝቡን አጠቃላይ ቁጥር ይፋ ባደረገበት በፓርላማ ስብሰባ ላይ ፕሬዝዳንት አልሲሲ በመገኘት መንግስት አሁን ያለውን የህዝብ ቁጥር ለልማት ግብዓትነት የሚጠቀምበት መሆኑን አመልክተዋል። ይህ ቆጠራ ከአስሩ ግብፃዊያን አንዱ ከግብፅ ውጭ የሚኖሩ መሆናቸውን ያመለክታል።

 

 

ይህም ቁጥር የግብፅ ህዝብ በ30 ዓመታት ጊዜ ውስጥ በእጥፍ መጨመሩን የሚያሳይ ነው ተብሏል። በዚሁ የህዝብ ቁጥር ውጤት መሰረት ከፍተኛውን የህዝብ ቁጥር እድገት የያዙት የገጠር ነዋሪዎች ናቸው። ከዚሁ ጋር በተያያዘም በስነተዋልዶ ግንዛቤ ማስጨበጫ ረገድ በገጠሩ የግብፅ ህዝብ ውስጥ ብዙ ሊሰራ የሚገባ መሆኑ ተመልክቷል። የቀደሙ መረጃዎች የሚያመለክቱት የግብፅ ህዝብ ቁጥር ዓመታዊ  እድገት 3 ነጥብ 5 በመቶ ነው። ይህም ሀገሪቱ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር እየተመዘገበባቸው ካሉት ሀገራት ተርታ ውስጥ ያስመድባታል።

 

 

ግብፅ የህዝብ ቁጥር እድገቷን ለመግታት መስራት ካልቻለች በሀገሪቱ እድገት ላይ የራሱን የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖን እንደሚያሳድር የሀገሪቱ የልማት አጋር ድርጅቶች በተደጋጋሚ እየተናገሩ ነው።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
139 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 896 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us